.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በደረሰበት የቴክኒክ ችግር ምክንያት ሴኔጋል ለማረፍ ተገደደ

ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መነሻውን ከአዲስ አበባ በማድረግ ወደ ማሊ ባማኮ 139 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረው ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነው አውሮፕላን አየር ላይ እያለ በአውሮፕላኑ ክንፍ ላይ በደረሰበት ድንገተኛ የቴክኒክ ብልሽት ከ45 አቂቃ በረራ በኋላ ሴኔጋል ዳካር አውሮፕላን ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል። አውሮፕላኑ በሰላም በማረፉ በመንገደኞች ላይም ሆነ በንብረት ላይ ምንም ዓይነት ጉዳት አለመድረሱን ...

Read More »

በዚንባቡዌ ሶስት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በመኪና አደጋ ሕይወታቸውን አጡ

ኀዳር ፳፱ (ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመግባት የሚጓዙ 22 ኢትዮጵያዊያን ስደተኛችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ አንድ ተሽከርካሪ በደረሰበት አደጋ የመኪናውን አሽከርካሪ ጨምሮ 3 ኢትዮጵያዊያን ወዲያውኑ ሕይወታቸውን ሲያጡ፣ 19 የሚሆኑት ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአገሪቱ የፖሊስ አዛዥ ፓውል ኒያቲ እንዳሉት የስደተኞቹን አገባብና የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ በማጣራት ላይ መሆኑንና ጉዳተኞቹ ለሕክምና ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን መግለጻቸውን ...

Read More »

በኦሮምያ ህዝቡ የተማሪዎችን ጥያቄ ደግፎ ወደ አደባባይ ወጣ

ኀዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባን አዲሱን ማስተር ፕላን በመተቸት በተማሪዎች የተጀመረው ተቃውሞ እያደገ፣ ህዝቡን በማሳተፍ በተለያዩ አካባቢዎች የቀጠለ ሲሆን ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላት በሚወስዱት እርምጃ የታዳጊወጣቶች ህይወት ተቀጥፏል። በቦረና ዞን ዱጋዳዋ ወረዳ ፍንጭ ውሃ ከተማ ላይ ተነስቶ በነበረው ተቃውሞ ተማሪ ቢፍቶ ኮንሶ የተባለች የ10ኛ ክፍል ተማሪ ፖሊሶች የተኮሱት አስለቃሽ ጭስ አፍኗት ስትወድቅ ፣ ...

Read More »

የሰቆጣ አርሶ አደሮች እየተሰደዱ ነው

ኀዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሚታየውን ከፍተኛ ረሃብ ተከትሎ መንግስት አርሶ አደሩ ቀየውን እንዳይለቅ ከፍተኛ ጥበቃ እያደረገ ቢሆንም፣ አርሶአደሮች ግን በሌሊት እየጠፉ በመሰደድ ላይ ናቸው። በፎቶ ግራፍ የተደገፉ መረጃዎች እንደሚያሳዩት የሰቆታ አርሶአደሮች በቡድን በቡድን በመሆን ወደ ጎንደር የተለያዩ ከተማዎች ተሰደዋል። በሊቦ ከምከም ወረዳ በአዲስ ዘመን እና ይፋግ ከተማዎች በርካታ ስደተኞች የገቡ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎችም ተቀብለው ...

Read More »

ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ባለፈው ግንቦት ወር ተካሂዶ በነበረው ምርጫ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቦላቸው እንደነበር አና ጎሜዝ ተናገሩ

ኀዳር ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ በአሸባሪነት የሚፈርጃቸው የአርበኞች ግንቦት7 ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ አገር ቤት ተመልሰው ግንቦት ወር ተካሂዶ በነበረው ምርጫ እንዲሳተፉ፣ በእርሳቸው በኩል መልክት እንዲያስተላልፉ ተነግሮአቸው እንደነበር የአውሮፓ ህብረት የፓርላማ አባል እና የኢትዮጵያ የምርጫ 97 የህብረቱ የምርጫ ታዛቢ ልኡካን መሪ ሚስ አና ጎሜዝ ተናግረዋል። ሚስ አና ጎሜዝ ይህን የተናገሩት ባለፈው ሳምንት ተዘጋጅቶ በነበረው ...

Read More »

ኢትዮጵያውያን በጋራ መታገል እንዳለባቸው ዶ/ር በያን አሰቦ ገለጹ

ኢሳት (ህዳር 27 ፣ 2008) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ከፍተኛ አመራር የሆኑት ዶ/ር በያን አሶባ፣  ዜጎች በአንድነት ተባብረው የህዝቦችን የነጻነት ፍላጎት ከዳር እንዲያደርሱ ለመላው ኢትዮጵያውያን ጥሪ አቅርበዋል። ቀድሞ የኦነግ የአመራር አባል የነበሩት ዶ/ር በያን፣ የአገሪቷ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ ግለሰቦችና ቡድኖች በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም ማዕዘናት የነጻነት እንቅስቃሴያቸውን በጋራ ማካሄድ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል። ተነጣጥሎ የሚደረግ አመጽና እምቢተኝነት በምንም መልኩ ሊሳካ እንደማይችል፣ ህዝቡ በጋራ ለነጻነትና ...

Read More »

በኦሮምያ የሚታየው ተቃውሞ እንደቀጠለ መሆኑን ከተለያዩ አካባቢዎች የሚደርሱን መረጃዎች ይጠቁማሉ።

ኀዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ሳምንት ፖሊሶች በወሰዱት እርምጃ ግቢያቸውን ጥለው ወጥተው የነበሩት የሁሌቦራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ ወደ ግቢያቸው ተመልሰው ከገቡ ቡዋላ እሁድ ለሰኞ አጥቢያ ሌሊቱን ተቃውሞ ሲያሰሙ አድረዋል። ዛሬ ጠዋት ፖሊሶች ወደ ግቢ በመግባት በተማሪዎች ላይ አስለቃሽ ጭስና ድብደባ በመፈጸማቸው በርካታ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል ገብተዋል። ቲቲሲ ኮሌጅና የቴክኒክና ሙያ ተማሪዎችም እንዲሁ ዬዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ተቀላቅለው ...

Read More »

የገጠር ነዋሪዎች በረሃብ የተነሳ ወደ ባቢሌ መሰደድ ጀምሩ

ኀዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት ድርቁን ተከትሎ በምስራቅ ሃረርጌ አካባቢ በዘንድሮው አመት 75 በመቶ የሚሆነው ህዝብ በርሃብ መጋለጡን የአካባቢው ባለስልጣናት እየገለጹ ሲሆን፣ በሚቀጥሉት ሳምንታት ዘናብ ካልዘነበ፣ ህዝቡ ሙሉ በሙሉ ፈልሶ ወደ ሀረር ከተማ ሊገባ ይችላል የሚል ስጋት ደቅኗል። አንዳንድ ሴቶችና ህጻናት ረሃቡን በመሸሽ ባቢሌ ከተማ መግባት ጀምረዋል። የአካባቢው ባለስልጣናት እንዲህ አይነት ድርቅ ...

Read More »

ሰማያዊ ፓርቲ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ላይ የሚወሰደውን የኃይል እርምጃ አወገዘ

ኀዳር ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በገዛ አፈሙዙ መቃብሩን የሚቆፍር የሽንፈትን ጽዋ ይጎነጫል በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ አዲሱ ማስተር ፕላንን በመቃወም ሰላማዊ ተቃውሟቸውን የሚያሰሙ ዜጎች ላይ በኃይልና በጠብመንጃ ለመመለስ የሚደረገውን አግባብነትና ኃላፊነት የጎደለው ጭፍን ተግባር እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ድርጊቱን ኮንኖ የአቋም መግለጫ አውጥቷል። ኢህአዲግ መራሹ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር ላይ የተከለው የጎሳ ፌዴራሊዝም ...

Read More »

በኦሮምያ የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

ኀዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ተከትሎ ተማሪዎች የሚያሰሙት ተቃውሞ ዛሬ በቦረና ዞን በቡሌሆራ ዩኒቨርስቲ ተቃውሞ ተነስቶ ታምሩ አኖሌ የተባለ መምህር ጉዳት ደርሶበታል። በተማሪዎች ላይ በተወሰደው እርምጃም የተወሰኑ ተማሪዎች ሳይጎዱ እንዳልቀረ የአካባቢው ምንጮች ግልጸዋል። ተቃውሞው በነቀምቴ፣ ወሊሶ፣ በምስራቅ ሃረርጌ አወዳይና በምእራብ ወለጋ ግዳሚ ከተማ በሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተካሄደ ሲሆን፣ በተቃውሞው ...

Read More »