.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ ወጣቶች ጥሪ አቀረቡ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ትግሉን በመቀላቀል ነጻነታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል። መንግስት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ጥረት ወጣቱ በንቃት ሊከታተለው እንደሚገባም ወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል። የተለያዩ ወጣቶች የሰጡዋቸውን አስተያየቶች በወጣቶች ዝግጅት ላይ እንደምናቀርብ እንገልጻለን።

Read More »

በሶማሊያ አንድ የኢትዮጵያ የደኅንነት ሹም ተገደለ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህነት ሹሙ በሶማሊላንድ ራስገዝ ሃርጌሳ ከተማ ውስጥ ዋቃዮ ጋልቤድ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። እስካሁን ለግለሰቡ ሞት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩንም ራዲዮ ኩሊሜይን ጠቅሶ አይኤችኤስ ዘግቧል።

Read More »

በኦሮምያ ዛሬም ተቃውሞው ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ከባድ ማስጠንቀቂያ በሰጠ ማግስት በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች መንግስትን የሚቃወሙ ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል። ህዝባዊ አመጾቹ በሃረርጌ አሰቦት፣ በምእራብ ወለጋ ባቡ ገምበሌና ነጆ፣ በሆድሮጉድሩ በጋጨቲ እንዲሁም በአሰላ የተካሄዱ ሲሆን፣ በቡራዩ ፣ አምቦና አወዳይ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰማርተው ቅኝት እያደረጉና የሚጠረጥሩት ወጣት እየያዙ እያሰሩ ነው። ታህሳስ 5 በአወዳይ የነበረውን ተቃውሞ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ከመንግስት ወታደሮች ጋር ተከታታይ ውጊያ እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የንቅናቄው ከፍተኛ የአመራር አባል የሆነው እንደገለጸው የንቅናቄው ሰራዊት ዋልድባ አካባቢ የነበረውን ወታደራዊ ቀለበት በመስበር በአድርቃይ ላይ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ29 በላይ ወታደሮችን ገድሏል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሎአል። በግንባር የተሰለፉ 6 አብሪዎች ወይም በቅኝት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አባሎቻቸው ከፍተኛ ውጊያ አድርገው ጥይታቸው ማለቁን ተከትሎ በወያኔ እጅ ወድቀዋል ሲል ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በመከላከያ ምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አሳወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለምስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን የሚል ደብዳቤ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4 ቀን 2008 ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ብቻ ከ11 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በገዢው ፓርቲ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። በጊንጪ በወታደሮች የተገደለውን ሰይፉ ቱራን ለመቅበር የወጡ ነዋሪዎች፣ ባስነሱት ተቃውሞ በጋሌሳ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የመንግስት ሹመኞች የለኮሱት ግጭት ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች። ታጣቂዎቹ ባል ወይም ሚስት አማራ ከሆኑ ...

Read More »

በኦሮምያ የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ አድማሱን እየሰፋ ነው

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ ላለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየው ህዝባዊ ተቃውሞ ዛሬም መቀጠሉን ከተለያዩ አካባቢዎች የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ገዢው ፓርቲ ተቃውሞውን ለመከላከል መከላከያ ሰራዊቱን ሳይቀር አሰማርቶ በወሰደው እርምጃ ከ45 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ቆስለዋል። በመላ ኦሮምያ በሚገኙ ከተሞች የፀጥታ ሃይሎች እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥረት ያደርጋሉ።የመንግስት ባለስልጣናት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ተግባራዊ አይደረግም ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የተነሳው ግጭት እንዳልበረደ ነዋሪዎች ተናግሩ

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ገዢው ፓርቲ ሆን ብሎ እንዳስነሳው በሚነገረው ግጭት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መገደላቸውን የአይን እማኞች ተናግረዋል። በአማራና ቅማንት ህዝብ መካከል ለዘመናት የቆየውን አንድነትና ዝምድና በማፍረስ አካባቢውን ወደ ግጭት ለመቀየር ገዢው ፓርቲ አስታጥቆ ያሰማራቸው ሚሊሺያዎች ግድያ እየፈጸሙ መሆኑን ነዋሪዎች ለኢሳት ተናግረዋል። እንዲህ አይነት ድርጊት ተፈጽሞ አያውቅም የሚሉት ነዋሪዎች ግጭቱ እየተስፋፋ የተለያዩ ወረዳዎችንና ቀበሌዎችን እያካተተ ...

Read More »

በሃዋሳ እና ሻሸመኔ መግቢያ አካባቢ ቦንብ ፈንድቶ ሁለት ሰዎች ተገደሉ

ታኀሳስ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን በአንዋር መስጊድ የደረሰውን የቦንብ ጥቃት ተከትሎ ፣ ዛሬም በአዋሳና ሻሸመኔ ድንበር አካባቢ ተመሳሳይ ፍንዳታ ተከስቶ 2 ሰዎች ተገድለዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ፣ ጥቃቱ በኦሮምያና ደቡብ ክልሎች መካከል መካሄዱ የሁለቱን ክልሎች ህዝቦች ለማጋጨት ሊሆን ይችላል ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

Read More »