የኢትዮጵያ ወጣቶች ጥሪ አቀረቡ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ትግሉን በመቀላቀል ነጻነታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል።
መንግስት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ጥረት ወጣቱ በንቃት ሊከታተለው እንደሚገባም ወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል። የተለያዩ ወጣቶች የሰጡዋቸውን አስተያየቶች በወጣቶች ዝግጅት ላይ እንደምናቀርብ እንገልጻለን።