በሶማሊያ አንድ የኢትዮጵያ የደኅንነት ሹም ተገደለ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህነት ሹሙ በሶማሊላንድ ራስገዝ ሃርጌሳ ከተማ ውስጥ ዋቃዮ ጋልቤድ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል።
እስካሁን ለግለሰቡ ሞት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩንም ራዲዮ ኩሊሜይን ጠቅሶ አይኤችኤስ ዘግቧል።