የካቲት ፲፩ (አስራ አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በምእራብ አርሲ በሚገኙ የተለያዩ ከተሞች ተቃውሞው ተጠንከሮ የቀጠለ ሲሆን፣ በዶዶላ ትናንት እና ዛሬ በነበረው ተቃውሞ ከ10 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። ሆስፒታል በርካታ ሰዎች ተመትተው የተኙ ሲሆን፣ አብዛኞቹ በህይወት የመትረፍ እድላቸው አነስተኛ ነው ተብሎአል። ትናንት በነበረው ተቃውሞ የሞቱ 2 ሰዎችን ለመቅበር የወጣው ህዝብ፣ ሟቾቹን መቅበር አትችሉም በመባሉ፣ ተቃውሞውን ጀምሯል። መብታችን ይከበር፣ የታሰሩት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ለድርቅ አደጋ የተሰጠው ምላሽ ከሚጠበቀው በታችና ነው ተባለ
ኢሳት (ጥር 20 2008) አለም አቀፍ ማህበረሰብ ለኢትዮጵያ የድርቅ አደጋ የሰጠው ምላሽ ከሚጠበቀው በታችና አስከፊ መሆኑ አንድ አለም አቀፍ የእርዳታ ተቋም አርብ አስታወቀ። በቀጣዩ ወር ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች 500 ሚሊዮን ዶላር ማሰባሰብ ካልተቻለም በርካታ ሰዎች ለከፋ ችግር እንደሚጋለጡ የህጻናት አድን ድርጅቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ በሃገሪቱ ታሪክም ሆነ በሌሎች ሃገራት ካሉት ጋር ሲነጻጸር አስከፊ ቢሆንም ዓለም ...
Read More »በጋምቤላ ክልል በብሄር ግጭት የብዙ ሰው ህይወት ጠፋ፣ ክልሉ በፌዴራል መንግስት ቁጥጥር ስር ውሏል
ኢሳት (ጥር ፥ 20 2008) በጋምቤላ ክልል በተነሳ የብሄር ግጭት በክልሉ የትራንስፖርት ቢሮ ምክትል ሃላፊን ጨምሮ ከ12 ሰዎች በላይ መገደላቸው ተሰማ። በትናንትናው ዕለት በጋምቤላ ከተማ መምህራን ኮሌጅ አካባቢ ቦምብ ፈንድቶ ባሮ ወንዝ የሚሄድ የአኝዋክ ብሄር ተወላጅ ላይ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በከተማዋ በአኙዋክና ኑዌር ብሄር ተወላጅ ተማሪዎች መካከል ከፍተኛ ግጭት ተከስቶ እንደነበረ የኢሳት ምንጮች ከስፍራው ዘግበዋል። ግጭቱን ተከትሎ የታጠቁ የክልሉ ልዩ ...
Read More »የጋምቤላ ክልል በፊዴራል መንግስት ስር ወደቀ
በጋምቤላ ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መንግስት ቁጥጥር ስር ወደቀች። ከአርብ ጥር 20 2008 ጀምሮ ፕሬዚደንቱን ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ከስራ ውጭ መሆናቸውን የተረጋገጠ ሲሆን፣ የክልሉንም ጸጥታ የፌዴራል መንግስት ተረክቧል። በአካባቢው የተቀሰቀሰውን የጎሳ ግጭት ተከትሎ በክልሉ ውጥረት የጨመረ ሲሆን የጋምቤላ ወህኒ ቤት ዛሬ መሰበሩ ታውቋል። በርካታ ሰዎች በዛሬው የወህኒ ቤት ጥቃት መገደላቸው ተገልጿል። የፌዴራል መንግስት የክልል ባለስልጣናትን ከስራ ውጭ ያደረገው የጸጥታን መቆጣጠር አልቻላችሁም ...
Read More »በጋምቤላ በቀጠለው ግጭት 7 ሰዎች ተገደሉ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሰርቫይቫል ኢንተርናሽናል ዳይሬክተር አቶ ኒካው ኦቻላ ለኢሳት እንደገለጹት የንዌር ተወላጆች የጋምቤላ እስር ቤትን ሰብረው በመግባት 7 የአኝዋክ ተወላጆችን ሲገድሉ፣ 7ቱን ደግሞ አቁስለዋል። 4 የሌሎች ብሄረሰቦች አባላት መቁሰላቸውምን ዳይሬክትሩ ገልጸዋል። በሁለቱ ብሄረሰቦች መካካል እንዲህ አይነት ደም የሚያፋሰስ የመረረ ግጭት ተቀስቅሶ እንደማያውቅ የገለጹት አቶ ኒካው፣ ለአሁኑ ግጭት መባባስ የሪክ ማቻር ወታደሮችንና ከደቡብ ሱዳን ...
Read More »በደቡብ ጎንደር በመቶወች የሚቆጠሩ ሰዎች ከርሃብ ጋር በተያያዘ በሽታ መሞታቸው ተሰማ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በላይጋይንት ወረዳ ከታች ነጋላ ነዋሪዎች መካከል በቀበሌ 23፣24 እና 26 በከፍተኛ ሁኔታ በድርቅ ከመጎዳታቸው ጋር ተያይዞ በተነሳ በሽታ ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አባዎራዎች ለሞት መዳረጋቸውን በርካቶችም የበሽታ ሰለባ ሆነው እንደሚገኙ የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከ1100 በላይ የቤት እንስሳት ማለቃቸውንም አክለው ተናግረዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች ሰሞኑን እርዳታ ለመጠየቅ ...
Read More »የመሬት መንቀጥቀጥ ሸሽተው ወደ ቤተሰቦቻቸው ሲሄዱ የነበሩ የሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች የመኪና አደጋ ደረሰባቸው
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሃዋሳ ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ለአስራ አምስት ቀናት ትምህርት መቋረጡን የዩንቨርሲቲው አስተዳደር መግለጹን ተከትሎ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል። በአንድ ተሽከርካሪ ላይ ተጭነው ከግቢው በመውጣት ወደ ወላጆቻቸው በመሄድ ላይ ከነበሩት ተማሪዎች ውስጥ ወደ በመቂ እና ሞጆ ከተሞች መዳረሻ አካባቢ የመኪና አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤ የሚጓዙበት ተሽከርካሪ ከአዲስ አበባ ወደ ሀዋሳ ሲጓዝ ከነበረ ኤፍ ኤስ አር ...
Read More »በኢትዮጵያ በአዮዲን የበለጸገ ጨው የሚጠቀመው ህዝብ እጅግ ዝቅተኛ ነው ተባለ
ጥር ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያ በአዮዲን የበለጸገ ጨው የሚጠቀመው ህዝብ 23 በመቶ ያህል መሆኑን ከኢትዮጵያ የምግብ መድሀኒትና ፋርማሱዪቲካል ልማት ኢንስቲትዪት የተገኘ ጥናት አመልክቷል። አብዛኛው ህዝብ በአዮዲን የበለፀገ ጨው ማግኘት ባለመቻሉ የእንቅርት በሽታን ጨምሮ የህጻናት አእምሮና እድገት ዝግመትን፣ ነፍሰጡር ሴቶች ላይ ውርጃንና የመሳሰሉ ችግሮችን በማስከተል ላይ ይገኛል። መንግስት ቁጥሩን ወደ 70 በመቶ ለማሳደግ እየሰራሁ ነው ብሎአል። በአሁኑ ...
Read More »ኦህዴድ ከፍተኛ አመራሮችን ከስልጣን ሊያነሳ እንደሆነ ተገለጸ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ማዕከላዊ ኮሚቴ በስራ አስፈጻሚ ደረጃ አስቸኳይ ስብሰባ መቀመጡ ታወቀ። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት አቶ ሙክታር ከድር እየተገመገሙ እንደሆነና ስልጣናቸውን ሊለቁ እንደሚችሉ ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ከጨፌ ኦሮሚያ የውስጥ ምንጮች ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ኦህዴድ በመላው የኦሮሚያ አካባቢ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ እምቢተኝነት ቁልፍ አመራር እየገመገመ መሆኑ ታውቋል። የድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴና ስራ አስፈጻሚው ግምገማውን ...
Read More »በኢትዮጵያ እየደረሰ ባለው የትራፊክ አደጋ በእሺ የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈ ነው ተባለ
ኢሳት (ጥር 19 ፥ 2008) ባለፉት ሶስት ወራቶች ብቻ በደረሱ የትራፊው አደጋዎች ከ1ሺ 100 በላይ ሰዎች በተለያዩ የሃገሪቱ ክልሎች መሞታቸውን የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለጠ። ይኸው ቁጥር በአመቱ መጨረሻ 4ሺ 600 ይደርሳል ተብሎ እንደሚጠበቅና፣ በሃገሪቱ እየደረሰ ያለው የትራፊክ ጉዳት ከመቼውም ጊዜ በላይ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን ሚኒስትሩ ማስታወቁን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። ባለፉት ጥቂት አመታት ውስጥ በሃገሪቱ በአመት 2ሺ 500 ሰዎች ...
Read More »