የጋምቤላ ክልል በፊዴራል መንግስት ስር ወደቀ

በጋምቤላ ሙሉ በሙሉ በፌዴራል መንግስት ቁጥጥር ስር ወደቀች። ከአርብ ጥር 20 2008 ጀምሮ ፕሬዚደንቱን ጨምሮ የክልሉ ባለስልጣናት ከስራ ውጭ መሆናቸውን የተረጋገጠ ሲሆን፣ የክልሉንም ጸጥታ የፌዴራል መንግስት ተረክቧል።

በአካባቢው የተቀሰቀሰውን የጎሳ ግጭት ተከትሎ በክልሉ ውጥረት የጨመረ ሲሆን የጋምቤላ ወህኒ ቤት ዛሬ መሰበሩ ታውቋል። በርካታ ሰዎች በዛሬው የወህኒ ቤት ጥቃት መገደላቸው ተገልጿል።

የፌዴራል መንግስት የክልል ባለስልጣናትን ከስራ ውጭ ያደረገው የጸጥታን መቆጣጠር አልቻላችሁም በሚል ምክንያት ቢሆንም በክልል ውስጥ የእርስ በዕርስ ግጭት እንዲከሰት በገዢው ስርዓት በኩል ሚናው ከፍተኛ እንደሆነ መረጃዎች ያሳያሉ።

በጋምቤላ በቀጠለው ግጭት የሟቾች ቁጥር እየጨመረ ሲሆን፣ በአካባቢው መጠለያ የተሰጣቸው የደቡብ ሱዳን መንግስት ተቃዋሚዎች ተሳታፊ መሆናቸው ተሰምቷል።