የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የመረጃ ምንጮቻችን ከተለያዩ ከተሞች የላኩልን መረጃ እንደሚያሳያው በክልሉ ውስጥ ከሚገኙ ከተሞች መካከል የደሴ፣ ኮምቦልቻ፣ ሸዋ ሮቢት፣ አጣዬ፣ ቆቦ፣ ከምሴ፣ መርሳ ሾፌሮች አድማውን አጠናክረው በመቀጠላቸው፣የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት በከፍተኛ ሁኔታ ተስተጓጉሏል። በኦሮምያ ደግሞ በነቀምቴ ተመሳሳይ አድማ በመካሄድ ላይ ነው። በወልድያ የተጀመረው አድማ ለሁለት ቀናት ከተካሄደ በሁዋላ ብዙዎች ታርጋቸው ተመልሶላቸው ስራ ጀምረዋል።የወረዳው ባለስልጣናት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
“በጸረ-ሽብርተኝነት ዘመቻው አጋራችን የሆነችውን ኢትዮጵያ ከከፋው የድርቅ አደጋ ልንታደጋት ይገባል!” ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለማቀፍ የልማት ኤጄንሲ አስተዳዳር ተናገሩ።
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኤጄንሲው ኃላፊ ጋይለ ስሚዝ ይህን ያሉት ሀሙስ እለት የኢትዮጵያን ረሀብና መሰጠት ያለበትን የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ አስመልክተው ለአሜሪካ የአደጋ ጊዜ ደራሽ ቡድን በሰጡት መግለጫ ነው። እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ በድርቅ ምክንያት የሚከሰተውን የደህንነት ስጋት ማስወገድ እንዲቻል የኦባማ አስተዳደር በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተውን የከፋ ድርቅ የሚቃኝ፣ የሚያስፈልገውን አስቸኳይ የእርዳታ መጠን የሚያሳውቅና ድጋፍ ...
Read More »በኮንሶ የወረዳ አመራሮች ታሰሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኮንሶ ህዝብ ያቀረበው የአስተዳደር ጥያቄ ለበርካቶች መታሰር ምክንያት ከሆነ በሁዋላ፣ የክልሉ ርእሰ ብሄር ቦታው ድረስ በመሄድ ህዝቡን አነጋግረው መፍትሄ እንደሚሰጡ ቃል ከገቡ በሁዋላ፣ የወረዳው አመራሮች እርስ በርስ እየተጣሉና እየተካሰሱ ሲሆን፣የታሰሩ መኖራቸውም ታውቋል።አመራሮቹ “በህዝብ የተረገመና ያልተረገመ “በሚል በሁለት ተከፍለው አንደኛው በሌላኛው ላይ ክስ ከማሰማት አልፎ፣ የህዝብ ወገን ናቸው የተባሉ አመራሮች ታስረዋል። ...
Read More »አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በምስክርነት ለማቅረብ የተደረገው ጥረት ውድቅ ተደረገ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ በአንደኛ ተከሳሽ አቶ ዘላለም ወርቃገኘሁ ላይ በቀረበው ክስ፣ ተከሳሹ ከግንቦት ሰባት ዋና ጸሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ጋር መጻጻፉን አቃቢ ህግ በክሱ ውስጥ ማስፈሩን ተከትሎ፣ ተከሳሽ አቶ አንዳርጋቸው ለምስክርነት እንዲጠሩላቸው ሲወተውቱ ቆይተዋል።ይሁን እንጅ እስር ቤቱ አቶ አንዳርጋቸውን ማቅረብ ባለመቻሉ፣ተከሳሽ ከአቶ አንዳርጋቸው ጋር በተያያዘ ...
Read More »የኦህአዴድ ካድሬዎች ለግምገማ ተጠሩ
የካቲት ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባና በዙሪያዋ የሚገኙ መላው የኦሮምያ ክልል የበላይና ከፍተኛ አመራሮች እና ካድሬዎች ከነገ ጅምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ለሚቆይ ግምገማ አዳማ በሚዘጋጀው ክልል አቀፍ የካድሬዎች ስብሰባ ላይ እንዲገኙ ታዘዋል፡፡ በየደረጃው የሚገኙ የኦህደዴ አባላት ከሰዓት ጀምሮ አዲስ አበባን ለቀው ወጥተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አብዛኛው የኦሮምያ አካባቢዎች በክልሉ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ በአጋዚ ወታደሮችና ...
Read More »በወልዲያ የተቀሰቀሰው የህዝብ ማመላለሻ አገልግሎት የስራ ማቆም አድማ ወደሌሎች ከተሞች መስፋፋቱ ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በወልዲያ ከተማ የተጀመረው የአሽከርካሪዎች የመኪና ባለቤቶች የስራ ማቆም አድማ ዛሬ ለሁለተኛ ቀን መቀጠሉ ታወቀ። ትናንት ከቀትር በኋላ የተጀመረው አድማ ዛሬ ሌሎች የሰሜን ወሎ ከተሞች መቀላቀላቸውን ያገኘነው መረጃ የመለክታል። በደሴ ዛሬ በስፋት የተጀመረ ሲሆን ኮምቦልቻ ውርጊዛ፣ ውጫሌ፣ ቆቦና አላማጣ ከተሞችም በተመሳሳይ የአሽከርካርዎች አድማ ተመቷል። በወልዲያ የመንግስት ባለስልጣናት ማስፈራሪያና ማታለያ የተንጸባረቀበት ስብሰባ ለተሽከርካሪ ባለሃብቶች አዘጋጅተው የነበረ ቢሆንም፣ ...
Read More »ከ2 ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናትና በእርግዝና ላይ የሚገኙ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸው ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ ለአስቸኳይ የምግብ እርዳታ ለተጋለጡ ሰዎች መቅረብ ያለበት ድጋፍ በወቅቱ ባለመድረሱ ምክንያት ከሁለት ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ህጻናትና በእርግዝና ላይ የሚገኙ እናቶች ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን የእርዳታ ተቋማት ገለጡ። ተረጂዎችን ለመታደግ የሚደረገው ጥረት እስከቀጣዩ ወር ድረስ አፋጣኝ ምላሽ ማግኘት ካልተጀመረም በሃገሪቱ መጠነ-ሰፊ የሆነ የሰብዓዊ ቀውስ ሊከሰት እንደሚችል ተቋማቱ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ የአለም ምግብ ፕሮግራም ተወካይ የሆኑት ጆን ...
Read More »የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ አባላት እንቅስቃሴያቸውን በጎንደር ከተማ ለህዝብ ማሳወቃቸው ተገለጸ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) ዛሬ በጎንደር ከተማ 1ሺህ በላይ ነዋሪ በታደመበት ስብሰባ፣ የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ አባላት እንቅስቃሴያቸውን ለህዝብ ማሳወቃቸው ተገለጸ። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ መንግስት እየተዋከቡ የሚገኙትና በብሄረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ድጋፍ ያጡት የወልቃይት የአማራ ማንነት አስተባባሪ ኮሚቴ አባለት በብአዴን የተከለከለ ስብሰባ ዛሬ በጎንደር ከተማ ከህዝቡ ጋር ማካሄዳቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የብአዴን ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አለምነት መኮንን ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑዌር ወጣቶች ህብረት የደቡብ ሱዳን መልዕክተኛን ሹመት ተቃወመ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የሚገኘው የኑዌር ወጣቶች ህብረት የደቡብ ሱዳን መልዕክተኛ አድርጎ የሾማቸውን አምባሳደር ተቃወመ። የሃገሪቱ መንግስትም የመልዕከተኛው ጀምስ ሞርጋንን ሹመት በአስቸኳይ እንዲሰርዝ ህብረቱ መጠየቁን ሱዳን ትሪቢዩን ጋዜጣ ሃሙስ ከአዲስ አበባ ዘግቧል። በልዩ መልዕክተኛው ላይ ተቃውሞ ያቀረበው የኑዌር ወጣቶች ህብረት አምባሳደር ጀምስ ሞርጋን የተባበሩት ኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ከተባለ አማጺ ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው የሚል ምክንያት ማቅረቡንም ጋዜጣው አስነብቧል። ...
Read More »አቶ ሌንጮ ለታ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ለኢትዮጵያ አንድነት መንገድ የጠረገ መሆኑን ገለጹ
ኢሳት (የካቲት 24 ፥ 2008) በኢትዮጵያ የኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እንቅስቃሴ የኦሮሞ አንድነት ያረጋገጠና ለእውነተኛ ኢትዮጵያ አንድነት መንገድ የጠረገ እንቅስቃሴ ነው ሲሉ አቶ ሌንጮ ለታ ገለጹ። የኦሮሞ ነጻነት ግንባት መስራችና ምክትል ዋና ጸሃፊ የነበሩትና በአሁኑ ወቅት የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ፕሬዚደንት የሆኑት አቶ ሌንጮ ለታ፣ ይህንን የተናገሩን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ነው። ለስራ ጉዳይ ከአውሮፓ ወደ ዋሽንግተን ብቅ ያሉትና ...
Read More »