.የኢሳት አማርኛ ዜና

በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተባብር ልዩ ቢሮ በዋሽንግተን ዲሲ ሊቋቋም ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 5/2011) አዲስ አበባ ውስጥ በኢንቨስትመንት ለመሰማራት የሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያንን የሚያስተባብር ልዩ ቢሮ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚቋቋም የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ  ገለጹ። ኢንጅነር ታከለ ኡማ በዋሽንግተን ዲሲ ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በኢትዮጵያ ኢምባሲ ተገኝተው ባሰተላለፉት መልዕክት ሁሉም ባለው እዉቀት እና ልምዱን በማስተባበር አዲስ አበባን እንዲለውጥ ጥሪ አቅርበዋል። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሰደር ፍጹም አረጋ ...

Read More »

በቴፒ ውጥረት መንገሱ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 6/2011)በቴፒ የአንድ የሐረማያ ዩንቨርሲቲ ተማሪ በጸጥታ ሐይሎች በመገደሉ ውጥረት መንገሱ ተነገረ። ልጃቸውን  ለመዳር የተዘጋጀው የሟች ቤተሰብ ደስታ ወደ  ሀዘን ተቀይሯል ። በከተማው ሌሎች  ሁለት  ወጣቶች  በጥይት  ተመተው  በቴፒ ሆስፒታል  በመታከም ላይ ይገኛሉ ። ውጥረቱን ተከትሎ  በርካታ የንግድ ተቋማት ተዘግተዋል፣ የትራንስፖርትም አገልግሎት  ተቋርጧል። በቴፒና አካባቢዋ በመከላከያ የሚመራ የኮማንድ ፖስት ቢታወጅም አሁንም ሰላምን ማስጠበቅ እንዳልተቻለ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በቴፒና አካባቢው ...

Read More »

አቶ በረከት ስምዖን የአማራ ክልል ህግ የማስከበር አቅም አጥቷል አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 5/2011)አቶ በረከት ስምዖን የአማራ ክልል ህግ የማስከበር አቅም አጥቷል ሲሉ ተናገሩ። ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመብኝ ነው ሲሉ በችሎት ተቃውሞ አሰሙ። በዛቻና ማስፈራራት ምክንያት ጠበቃ የሚቆምልን አላገኘንም በማለት መናገራቸውም ታውቋል። ሌላኛው ተከሳሽ አቶ ታደሰ ካሳ የፈጸምኩት ወንጀል የለም በማለት የእምነት ክህደት ቃል መስጠታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።  

Read More »

በየመን ከሶስት ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች ከእስር እንዲለቀቁ አይ ኦ ኤም ጠየቀ

 (ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 2/2011)በየመን በአስከፊ ሁኔታ በማጎሪያ እስር ቤቶች የሚገኙ ከሶስት ሺህ በላይ የውጭ ዜጎች እንዲለቀቁ ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም ጠየቀ። አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ የገለጸው ድርጅቱ ኢሰብዓዊ በሆኑ የከፋ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙትን እስረኞች ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከተለያዩ የየመን አካባቢዎች የተያዙ እንደሆኑ አስታውቋል። ከ2 ሺህ 500 ስደተኞች በአብዛኛው ኢትዮጵያውያን የሆኑ ስደተኞች በስታዲየም ውስጥ በስቃይ ላይ መሆናቸውንም መረጃዎች ያመለክታሉ። ተላላፊ ...

Read More »

አቶ በረከት ስምዖን የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 2/2011)አቶ በረከት ስምዖን ጥፋተኛ አይደለሁም ሲሉ የእምነት ክህደት ቃላቸውን ሰጡ። አብረዋቸው የተከሰሱት አቶ ታደሰ ካሳ ፍቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ተሰምቷል። የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት እንደዘገበው ሁለቱ የቀድሞ የብአዴንና የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች  ክሳቸው እንዲቋረጥ  ያቀረቡት መቃወሚያ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል። ተከሳሾቹ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክሱን ማየት ስልጣን የለውም በሚል መከራከራቸውና ጥያቄያቸውም በተመሳሳይ ተቀባይነት ሳይገኝ መቅረቱ ተገልጿል። ሁለቱ የቀድሞ ...

Read More »

አዴሃን የአማራ ክልል መንግስት ቃሉን አልጠበቀም በሚል የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 2/2011) የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ አዴሃን የአማራ ክልል መንግስት ቃሉን አልጠበቀም በሚል በዛሬው ዕለት የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ። ከስምንት ወራት በፊት ከኤርትራ ትጥቁን በመፍታት ወደሃገር ቤት የገባው አዴሃን ከክልሉ ገዢ ፓርቲ አዴፓ ጋር ከደረሳቸው ባለ 41ነጥብ ስምምነቶች አንዳቸውም ተግባራዊ አልተደረጉም ሲል አስታውቋል። የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ተስፋሁን አለምነህ ለኢሳት እንደገለጹት የአዴሃን አባላት በከፋ ችግር እየተሰቃዩ ናቸው። በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ከምርጫ ...

Read More »

ኢዜማ የፓርቲውን መሪዎች በመምረጥ ጉባዔውን አጠናቀቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 2/2011) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ የፓርቲውን መሪዎች በመምረጥ የመስራች ጉባዔውን አጠናቀቀ። የሰባት ፓርቲዎች ውህድ በመሆን የተመሰረተው ኢዜማ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋን የፓርቲው መሪ፣ አቶ አንዱዓለም አራጌን በምክትልነት መርጧል። አቶ የሺዋስ አሰፋን የፓርቲው ሊቀመንበር፣ ዶክተር ከበደ ጫኔን ደግሞ በምክትል ሊቀመንበርነት መምረጡ ታውቋል። ከ300 በላይ ወረዳዎች ተወካዮቻቸውን በመላክ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት ጉባዔውን ያካሄደው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ ዜግነት ...

Read More »

አዲሱ ፓርቲ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ በሚል ስያሜውን አጸደቀ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 1/2011) የሰባት የፖለቲካ ሃይሎች ውህደት የሆነው አዲሱ ፓርቲ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ በሚል ስያሜውን አጸደቀ። መስራች ጉባዔውን ዛሬ በአዲስ አበባ የጀመረው አዲሱ ፓርቲ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከ300 በላይ ወረዳዎች በተወከሉ የመስራች ጉባዔ አባላት መተዳደሪያ ደንብ፣ አወቃቀር እና አርማ ላይ ውሳኔ በመስጠት እየተካሄደ መሆኑን የመስራች ጉባዔው አስተባባሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በድምጽ የሚሳተፉ 1200 የጉባዔ አባላት የአዲሱ ፓርቲ አመራሮችን ይመርጣሉ ተብሎ ...

Read More »

የአፋር ሶስት ቀበሌዎች ይመለሱ ሲል ያሳለፈው ውሳኔ አግባብነት እንደሌለው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 1/2011) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት የአፋር ሶስት ቀበሌዎች ይመለሱ ሲል ያሳለፈው ውሳኔ አግባብነት የሌለው ነው ሲል የአፋር ህዝብ ፓርቲ አስታወቀ። የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ኮንቴ ሙሳ ከኢሳት ጋር በነበራቸው ቆይታ እንዳሉት ከሆነ ከሶማሌ ክልል ተወስደዋል የተባሉት ቀበሌዎች ድንበር ላይ ያሉ ሳይሆኑ 300 ኪሎ ሜትር ወደ አፋር ክልል የገቡ ናቸው። ይህ ባለበት ሁኔታ አይነቱን ጥያቄ ማንሳት አግባብነት የሌለውና የህዝብን መብት ...

Read More »

በኢትዮጵያ ግጭቶችን በመቀስቀስና ዜጎችን በማፈናቀል 1ሺህ 300 የሚሆኑ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 1/2011) የኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችን በመቀስቀስና ዜጎችን በማፈናቀል ከተጠረጠሩ 2500 ሰዎች 1ሺህ 300 የሚሆኑት በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ክፍል ሃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ለኢሳት እንደገለጹት ከእነዚህ በቁጥጥር ስር ከዋሉት ግለሶቦች የክልል አመራሮች ይገኙበታል። መንግስት በርካታ ግጭቶችን ከመከሰታቸው አስቀድሞ ማምከን መቻሉን የገለጹት አቶ ንጉሱ ቢከሰቱ ኖሮ ለአያሌ ዜጎች ሞት መንስዔ ይሆኑ ነበር ብለዋል። ግጭቶችን ...

Read More »