.የኢሳት አማርኛ ዜና

የብረታ ብረትና ኢንጂነሪን ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከ3 ቢሊዮን ብር በላይ ኮንትራት ተረከበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) የመንግስት የልማት ፕሮጄክቶችን ያለ ግልጽ ጨረታ በመረከብ ላይ የሚገኘው የብረታ ብረትትና ኢንጂነሪን  ኮርፖሬሽን ለአዲስ አበባ ከተማ አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከሶስት ቢሊዮን ብር በላይ ኮንትራት ተረከበ። የህወሃት ጄኔራሎች የሚመሩት ኮርፖሬሽኑ 750 አውቶቡሶችን ለማቅረብ ከከተማው አስተዳደር ጋር የኮንትራት ስምምነት መድረሱን ከሃገር ቤት የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአዲስ አበባ መንገዶችና ትራንስፖርት ቢሮ በቀጣዩ ሳምንት ከኮርፖሬሽኑ ጋር የ3.5 ቢሊዮን ብር ስምምነት ...

Read More »

በሶማሌ ክልል የተከሰተውን ኮሌራ በቁጥር ስር ለማዋል የውጭ ሃገራት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቀረበ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) በኢትዮጵያ የሶማሌ ክልል ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነውን የኮሌራ በሽታ ስርጭት (ወረርሽኝ) በቁጥር ስር ለማዋል የውጭ ሃገራት ድጋፍ እንደሚያስፈልግ የፈረንሳዩ አለም አቀፍ ድንበር የለሽ የሃኪሞች ግብረ ሰናይ ድርጅት ጥሪውን አቀረበ። በክልሉ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት በመደገፍ ላይ መሆኑን የገለጸው ድርጅቱ፣ ከ16 ሺ በላይ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን ይፋ አድርጓል። የፌዴራልና የክልሉ ባለስልጣት በበሽታው ስርጭት ሳቢያ በሰዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለግል ባለሃብቶች የሚሰጠውን የኢንቨስትመንት ብድር አቋረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣውን አዲስ መመሪያ ተከትሎ ንግድ ባንክ ለረጅም አመታት ለግል ባለሃብቶች ሲሰጥ የቆየውን ብድር ከሚያዚያ 2 ፥ 2009 አም ጀምሮ ማቋረጡን ካፒታል የተሰኘው ጋዜጣ ዘግቧል። ብሄራዊ ባንክ ከንግድ ባንክ ብድር እንዳያገኙ የተደረጉ ባለሃብቶች ጥያቄያቸውን ለኢትዮጵያ ልማት ባንክ በማቅረብ እንዲያስተናግዱ ትዕዛዝ መስጠቱ ታውቋል። በዚሁ የብሄራዊ ባንክ አዲስ መመሪያ መሰረት የብድር ጥያቄን አቅርበው ውሳኔን በመጠባበቅ ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የአለማችን የፕሬስ ነጻነት ጀግና በሚል ተመረጠ

ኢሳት (ሚያዚያ 17 ፥ 2009) መቀመጫውን በኦስትሪያ ቬይና ያደረገው አለም አቀፍ የፕሬስ ኢንስቲትዩት ከአለም አቀፉ የሚዲያ ድጋፍ (IMS) ጋር በጋራ እስክንድር ነጋ የአለማችን የ2017 የፕሬስ ነጻነት ጀግና በሚል ሰይመውታል። አለም አቀፉ የፕሬስ ኢንስቲትዩት ማክሰኞ ኤፕሬል 25, 2017 ከአውስሪያ መዲና ቬይና ባወጣው መግለጫ፣ ሃሳብን ለመግለፅ ነጻነት ወደር የሌለው ፅናትን ለሚያሳዩ የአለማችን ጋዜጠኞች የሚሰጠው ይኸው ሽልማት ለ2017 እስክንድር ነጋ መመረጡን አስታውቋል። ላለፉት ...

Read More »

አሜሪካ አልሸባብ ላይ ልታካሄድ ባቀደቸው አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ዙሪያ ላይ ለመምከር የመከላከያ ሚኒስትሯ ወደጅቡቲ ላከች

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ጂም ማቲስ ሃገራቸው በሶማሊያ ታጣቂ ሃይል አልሸባብ ላይ ልታካሄድ ባቀደቸው አዲስ ወታደራዊ ጥቃት ዙሪያ ላይ ለመምከር ትላንት ዕሁድ በጅቡቲ ጉብኝት አደረጉ። የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር በአል-ሸባብ ታጣቂ ሃይል ላይ አዲስ ወታደራዊ ዘመቻ እንዲያካሄድ በሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ልዩ ትዕዛዝ ከተሰጠው በኋላ የመከላከያ ሚኒስትሩ በጅቡቲ ጉብኝት ሲያደርጉ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑ ታውቋል። የመከላከያ ሚኒስትሩ ማቲስ ...

Read More »

የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነ-ስርዓት በኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተገለጸ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) ታዋቂው ጸሃፊ፣ የህግ ባለሙያና የቀድሞ የፓርላማ አባል የአቶ አሰፋ ጫቦ የቀብር ስነስርዓት በትውልድ ሃገራቸው ኢትዮጵያ እንደሚፈጸም ተገለጸ። አስከሬኑን ወደ ኢትዮጵያ ለመሸኘትም እንቅስቃሴ ተጀምሯል። እሁድ ሚያዚያ 15 ፥ 2009 በዬስ አሜሪካ ቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ ህይወታቸው ያለፈው አቶ አሰፋ ጫቦ፣ ከ73 አመታት በፊት በደቡብ ኢትዮጵያ በጋሞጎፋ ጨንቻ ከተማ መወለዳቸውን የህይወት ታሪካቸው ያስረዳል። የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ...

Read More »

የድርቅ አደጋ በመባባሱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ተረጂዎች ለምግብ ድጋፍ ተጋለጡ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) በኢትዮጵያ ተከስቶ ያለው የድርቅ አደጋ መባባስን ተከትሎ በኦሮሚያና የደቡብ ክልሎች ከአንድ ሚሊዮን በላይ ተጨማሪ ተረጂዎች ለምግብ ድጋፍ ተጋለጡ። የመንግስት ባለስልጣናት የተረጂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን በቅርቡ ይፋ ቢያደርጉም ቁጥሩን ግን ለህዝብ ከማሳወቅ ተቆጥበው ይገኛሉ። ይሁንና በዚሁ የድርቅ አደጋ ዙሪያ አዲስ ሪፖርትን ያወጣው የተባበሩት መንግስታት የህጻናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች መጣል የነበረበት የበልግ ዝናብ በወቅቱ ...

Read More »

ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸውን ክስ በመቃወም ለፍርድ ቤት መቃወሚያ አቀረቡ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተላልፈዋል ተብለው የታሰሩትና ህገ-መንስታዊውን ስርዓት በሃይል ለመናድ በሚል በእስር የሚገኙት ዶ/ር መረራ ጉዲና የቀረበባቸውን ክስ በመቃወም ሰኞ ለፍርድ ቤት መቃወሚያን አቀረቡ። ዶ/ር መረራ ጉዲና በከሳሽ አቃቤ ህግ የተመሰረተባቸውን ክስ ለመቃወም ባለ 11 ገፅ የክስ መቃወሚያን ያቀረቡ ሲሆን፣ ቤልጂየም ለህዝባዊ ስራ በሄድኩበት ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ ዋጁን ተላልፏል ተብሎ የቀረበውን ክስ ተዋውመዋል። ከሳሽ አቃቤ ...

Read More »

በህወሃት ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል በሽምግልና ለመፍታት ጥረት ተጀመረ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) ውስጥ የተፈጠረውን ክፍፍል በሽምግልና ለመፍታት የሃገር ሽማግሌዎች እንቅስቃሴ ጀመሩ። በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅና በአትሌት ሃይሌ ገ/ስላሴ የተጀመረው ይህ ጥረት የአርበኞች ማህበር ሊቀመንበር/ ልጅ ዳንዔል ጆቴንም እንዳካተተ መረዳት ተችሏል። በህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አመራር ውስት ረጅም ጊዜያት የዘለቀና ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ገያድ እየወጣ የሚመጣውን ልዩነት ለመሰምገል ከራሱ ከህወሃት የተውጣቱ ገለልተኛ ቡድኖች ...

Read More »

በቻግኒ ከተማ የባጃጅ ታክሲ አሽከርካሪዎች ስራ የማቆም አድማ አደረጉ

ኢሳት (ሚያዚያ 16 ፥ 2009) በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የባጃጅ ታክሲ አሽከርካሪዎች ዛሬ የስራ ማቆም አድማ ጀመሩ። ከትራንስፖርት ታሪፍ ጋር በተያያዘ አሸከርካሪዎቹ በመቱት አድማ፣ የቻግኒ ትራንስፖርት አገልግሎት መቋረጡን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። የባጃጅ አሽከርካሪዎች የዋጋ ታሪፍ እንዲቀንስ በመንግስት የተወሰደውን ዕርምጃ ተከትሎ ነው የስራ ማቆም አድማውን የመቱት። ከ190 በላይ የባጃጅ አሽከርካሪዎች በተሳተፉበት በዚሁ ድርጊት፣ የቻግኒ ከተማ የታክሲ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ እንዲቋረጥ ...

Read More »