ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሕዝባዊ እንቢተኝነቱን ተከትሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙት የአርሶ አደሮችን መሬት ነጠቃ ከተቋረጠ ወዲህ ገዥው ሕወሃት/ኢህአዴግ ፊቱን ወደ ዋና ከተማዋ መልሷል የሚሉት ነዋሪዎች፤ በልማት ስም ነባር ይዞታያላቸውን የከተማ ነዋሪዎች መሬት መንጠቅ ተጧጡፎ መቀጠሉን ይገልጻሉ። ነዋሪዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ካለፍላጎታቸው ከይዞታቸው እንዲነሱ የተደረጉት ነዋሪዎች መኖሪያውን ከመልቀቃቸው አስቀድሞ በመስተዳድሩ ቃል የተገቡላቸው በሙሉ ተፈጻሚ አይሆኑም። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በጥምረት መስራት አትራፊ እንዳልሆነ አንድ የማላዊ የፓርላማአባል ገለጹ::
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማላዊ ኮንግረስ ፓርቲና የአገሪቱ ፓርላማ አባል የሆኑት ወ/ሮ ጁሊያን ሉንዛጊ ዛሬ ለአገራቸው ፓርላማ እንዳሳወቁት የማላዊ አየር መንገድ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በጥምረት መስራቱ አትራፊአያደርገውም ብለዋል። ጁሊያን ሉንዛጊ አያይዘውም የአገራቸው የትራንስፖርት ሚኒስቴር መስሪያ ቤት-አየር መንገዱ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመሥራቱ እንዴት ትርፋማ ሊሆን እንደሚችል ሪፖርትእንዲያቀርብ ጠይቀዋል። የፓርላማ አባሏ “ትርፋማ ካልሆንን ለምን አብረን ...
Read More »በዶክተር ቴዎድሮስ አድኃኖም ላይ የሚደረገው ተቃውሞ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ አሚን ጁዲ ጥሪ አቀረቡ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የፖለቲካ ጉዳይ ሀላፊ አክቲቪስት አሚን ጁዲ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከኅብር ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የአፍሪካ ህብረት ዶክተር ቴዎድሮስን ደገፈው፤ አልደገፈው ኢትዮጵያውያን ተቃውሟቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል። ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በዓለም ጤና ድርጅት ስም ስልጣን እንዲይዝ የሚፈልጉት፤ ከጀርባ እሱን ተጠቅመው በአፍሪካ ደሃ ሕዝብ ላይ የፈለጉትን ...
Read More »አቡነ ዘካርያስ የተጭበረበሩትን 1 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር ራሳቸው ከፈሉ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቀደም ሲል የምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት አስተዳደር የነበሩትና አሁን የኒውዮርክና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት አቡነ ዘካርያስ፣ በሐሰተኛ ሰነድ ተጭበርብረው ሕንፃበመግዛታቸው የከሰረውን ገንዘብ ከምዕመናን በማሰባሰብ ራሳቸው ፈጸሙ፡፡ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የሆኑት አቡነ ዘካርያስ ቀደም ሲል ያስተዳድሩት በነበረ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ደቀ መዛሙርት ማሠልጠኛና ለአብነት ትምህርት ቤቶች ድጋፍ ...
Read More »ሟቹ የኢትዮጵያ ቡና እግር ኳስ ቡድን አስጨፋሪ ከጨጓራ ህመም ውጪ ምንም ዐይነት ህመም እንደሌለበት ወላጅ አባቱ ገለጹ።
ግንቦት ፪ ( ሁለት ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የዘነበ አባት አቶ በላይ በተለይ ለኢሳት እንደገለጹት ልጃቸው ከጨጓራ ህመም ውጪ የልብ ድካምም ሆነ ድንገት ለህልፈት የሚዳርግ በሽታ እንዳልነበረበት ጠቅሰው፤ እስካሁን ድረስ ምን ሆኖ እንደሞተ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ በሀዘን ስሜት ተውጠው ተናግረዋል። ቡና ከሃዋሳ ከነማ ጋር ላለው ግጥሚያ ከአንድ ወር ከአስራ አምስት ቀን በፊት ወደ ሃዋሳ ሲያመራ አብሮ እንደተጓዘ ...
Read More »አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠውን የገንዘብ ድጋፍ አቋረጠች
ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) አሜሪካ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የምትሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ለሙስና የተጋለጠ ነው በማለት ድጋፏን አቋረጠች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴት ለኬንያ መንግስት ባሳወቀው በዚሁ ውሳኔ 12 ሚሊዮን ዶላር አካባቢ ድጋፍ እንዲቋረጥ መደረጉን እንደገለጸ ዴይሊ ኔሽን ጋዜጣ ማክሰኞ ዘግቧል። በኬንያ የአሜሪካ አምባሳደር ሮበርት ጎዴክ በሃገሪቱ ሙስናና ተጠያቂነት አሳሳቢ እየሆነ በመምጣቱ ለኬንያ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቀጥታ የሚሰጠው የገንዘብ ድጋፍ ...
Read More »በህገወጥ መንገድ ወደ ሞዛምቢክ የገቡ ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) የሞዛምቢክ የኢሚግሬሽን ባለስልጣናት ወደ ሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል የተባሉ 24 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ መደረጉን ማክሰኞ አስታወቁ። ለቀናት ያህል በሃገሪቱ ፖሊስ በቁጥጥር ስር የነበሩት ኢትዮጵያውያን ከአዲስ አበባ ሲነሱ የተሳሳተ ቪዛን ይዘው እንደተጓዙ የሞዛምቢክ የጸጥታ ሃላፊዎችን ዋቢ በማድረግ ዴይሊ ኔሽን የተሰኘ ጋዜጣ ዘግቧል። ባለፈው ወር በተመሳሳይ መልኩ ወደ ሃገሪቱ ገብተዋል የተባሉ 13 ኢትዮጵያውያን ወደ ሃገራቸው እንዲመለሱ ...
Read More »ኢትዮጵያ ያልተመጣጠነ የዜጎች ገቢን በማስመዝገብ በአለም በዝቅተኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) ከ90 ሚሊዮን ህዝብ በላይ ያላት ኢትዮጵያ በአለም ካሉ ሃገራት መካከል ያልተመጣጠነ የዜጎች ገቢን በማስመዝገብ በዝቅተኛ ደረጃ ላይ መፈረጇ ተገለጸ። ሃገሪቱ ባለፉት 10 አመታት የባለ ሁለት አህዝ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን አስመዝግባለች ቢባልም፣ ኢትዮጵያ አሁንም ድረስ በድህነት ውስጥ ከሚገኙ ሃገራት ተርታ አንዷ መሆኗን ወርልድ ኢኮኖሚስ ጋዜጣ የተለያዩ መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ማክሰኞ ዘግቧል። በአሁኑ ወቅትም የኢትዮጵያን አማካኝ የነፍስ ወከፍ ...
Read More »ከህወሃት መሪዎች ጋር በሽርክና የሚሰሩ የሌላ አካባቢ ተወላጅ ጥቂት ባለሃብቶች ከፍተኛ ብድር እየወሰዱ መሆናቸው ተገለጸ
ኢሳት (ግንቦት 1 ፥ 2009) ለኤፈርትና ለትግራይ ተወላጆች ከሃገሪቱ ባንኮች ከፍተኛ ሃብት በብድር መውጣቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት፣ ከህወሃት መሪዎች ጋር በሽርክና የሚሰሩ የሌላ አካባቢ ተወላጅ ጥቂት ባለሃብቶች በተመሳሳይ ከፍተኛ ብድር እየወሰዱ መሆናቸውን ምንጮች ገለጹ። በሌላ በኩል በንግዱ አለም በራሳቸው ጥረት ውጤታማ የሆኑት ሲገፉ መቆየታቸውና አሁንም በመገፋት ላይ መሆናቸውንም ኢሳት ያጠናከረው ማስረጃ ያስረዳል። በተለይ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ከፍተኛ ብድር በመውሰድ ዕዳቸው ...
Read More »በርካታ የኦሮሚያ ስፍራዎች ወደ ሶማሌ ክልል መጠቃለላቸውን የሶማሌ ክልል ፕሬዚዳንት በግልጽ ተናገሩ።
ግንቦት ፩ ( አንድ ) ቀን ፪፲፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በጭናክሰንና በባቢሌ ከፍተኛ ውጥረትና ተቃውሞ የተቀሰቀሰ ሲሆን የኦሮሚያ ክልል ፖሊሶች ትጥቅ እንዲፈቱ ተደርጓል። በኦሮሚያና በሶማሊያ ድንበር አካባቢዎች ይፈጠሩ የውነበሩ ግጭቶች እልባት እንዳገኙ በቅርቡ በመንግስት መገናኛ ብዙሀን በተደጋጋሚ ቢገለጽም ሁኔታው ወደ አደገኛ መንገድ እያመራ እንደሆነ የባቢሌና የጭናክሰን ነዋሪዎች በተለይ ለኢሳት ገልጸዋል። የሶማሌው ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አብዲ መሀመድ እሁድ ዕለት በመከላከያ ...
Read More »