ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወልድያ ትናንት የእለት ገቢን ምክንያት አድርጎ የተጣለውን ግብር ለመቃወም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ በወልድያ የስብሰባ አዳራሽ የተገኘ ሲሆን፣ በስብሰባው ላይም ተቃውሞውን በከፍተኛ ስሜት አቅርቧል። ወኪላችን እንደገለጸው ህዝቡ ስብሰባ እንዳለ በማወቁ በብዛት የወጣ ሲሆን፣ አዳራሽ በመሙላቱ ስብሰባውን በውጭ ሆኖ እስከ መከታተል ደርሷል። ህዝቡ “ እኛን ገድላችሁ፣ ማንን ልትገዙ ነው? ዜጎችን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ በሰብዓዊ መብት ማስከበር ላይ የተሰማሩ ድርጅቶች 95 ከመቶ በላይ የሚሆኑት መዘጋታቸውን ጥናቶች አመለከቱ
ሐምሌ ፫ ( ሦስት ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአገር አቀፍ ደረጃ የሰብዓዊ መብት እና የዴሞክርሲ ግንባታ ላይ ለመስራት ፍቃድ ተሰጥቷቸው ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ ከመቶ በላይ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ውስጥ በአሁኑ ወቅት አምስቱ ብቻ ስራቸውን እየሰሩ መሆኑን ቪዥን ኢትዮጵያ ለዲሞክራሲ ጉባኤ ባዘጋጀው መድረክ ላይ ጥናቶች አመለከቱ። ድርጅቶቹ እስከ ምርጫ 1997 ዓ.ም መባቻ ድረስ ስራቸውን በአግባቡ ያከናወኑ እንደነበርም ጥናቱ አመላክቷል። ...
Read More »የኢትዮጵያ ፓርላማ ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ በጀት አጸደቀ
(ኢሳት ዜና – ሰኔ 30 2009) የኢትዮጵያ ፓርላማ 1/3ኛ የበጀት ጉድልት ያልበትን ከ320 ቢሊዮን ብር በላይ አመታዊ በጀት አጸ። የ100 ቢሊዮን ብር የበጀት ጉድለት ያለበት የመንግስት አመታዊ በጀት ከብድር እና እርዳታ ይሸፈናል ጠብሎ እንደሚጠበቅ ተገልጿል ። ዋናው ገቢ ግን ከግብር እና ከሃገር ውስጥ የሚሰበሰብ ነው ተብሏል። ይህ በጀት ካለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር በ 17 በመቶ ብልጫ ያለው ቢሆንም የበጀት ጉድለቱ ...
Read More »በአፍሪካ ቀንድ የተከሰተውን የዝናብ እጥረት ተከትሎ አስቸኳይ እርዳታ በሚቀጥለው አመትም ያስፈሊጋል ተባለ
(ኢሳት ዜና – ሰኔ 30 2009) ደቡብ ምስራቅ ኢትዮጵያና ሶማሊያን ጨምሮ በአፍሪካ ቀንድ የሚያስፈልገው አስቸኳይ የምግብ ዋስትና እርዳታ ለቀጣዩም የ2018 አመት ካልቀረበ ከፍተኛ አደጋና ችግር ሊያስከትል እንደሚችል አንድ አለም አቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ ። የረሃብ አደጋን ቀድሞ በማስጠንቀቅ የሚታወቀውና ፊውስኔት የተባለው አለም አቀፍ ተቋም እንዳስጠነቀቀው የዘንድሮው አመት የዝናብ መጠን አጥጋቢ ባለመሆኑ አስቸኳይ የምግብ እርዳታው ለአፍሪካ ቀንድ ሃገራት በሚቀጥለው አመትም ካልቀረበ አደጋው ...
Read More »በደቡብ ጎንደር የተጀመረው ትጥቅ የማስፈታት ዘመቻ ከሸፈ
(ኢሳት ዜና – ሰኔ 30 2009) በደቡብ ጎንደር እብናት ወረዳ የህውሃት አጋዚ ጦር የገበሬውን ትጥቅ ለማስፈታት ያደረገው ሙከራ መክሸፉ ተነገረ ። በሰሜን ጎንደር የተጀመረው ገበሬውን ትጥቅ የመፍታት ዘመቻ ወደ ደቡብ ጎንደር ተሻግሯል ።የኢሳት መንጮች እንደገለጹት በደቡብ ጎንደር እብናት ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች ትጥቅ ለማስፈታት የአጋዚ ጦር በከፈተው ተኩስ 3 ሰዎች ቆስለዋል ። በእብናት ወረዳ ሰፍሮ የነበረው የህውሃት አጋዚ ጦር በሚንጦች ፣ ...
Read More »ኢህአዴግ የኦሮሞን ህዝብ ያስደስታል ብሎ ያወጣው ህግ ያልተጠበቀ ውጤት በማሳየቱ ህዝቡን በግድ የድጋፍ ሰልፍ ሊያስወጣ ነው
ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የግንባሩ የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የኦሮሞ ህዝብ በአዲስ አበባ ላይ ያለውን ልዩ ጥቅም የሚያስከበር አዋጅ መደንገጉ ለድርጅቱ ከፍተኛ ህዝባዊ ድጋፍ ያስገኝለታል በሚል በኢህአዴግ የፖሊሲ፣ ጥናትና ምርምር ተቋም የቀረበው ምክር እንዳልሰራ በመታመኑ ፣ ሰነዱ በኦሮምያ ክልል በየደረጃው ባሉ አካላት ውይይት ተካሂዶበት፣ የድጋፍ ሰልፍ እንዲደረግለት ልዩ ትዕዛዝ ተላልፏል። በአቶ በረከትና አባይ ጸሃዬ ...
Read More »ዶ/ር መረራ ጉዲና ያቀረቡት መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ
ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው ፖለቲከኛ የኦሮሞ ፌደራሊስት ሊ/መንበር ዶ/ር መረራ ጉዲና የተከሰሱበት ክስ ከአርበኞች ግንቦት 7፣ ከፕ/ሮ ብርሃኑ፣ ከአቶ ጃዋር፣ ከኢሳትና ከኦኤም ኤን ተነጥሎ እንዲታይላቸው ያቀረቡት መቃወሚያ ፍርድ ቤቱ ዛሬ አርብ በዋለው ችሎት ውድቅ አድርጎታል። ፍርድ ቤቱ ምስክሮች የሚቀርቡት በሁሉም ተከሳሾች ላይ በመሆኑ ፣ ክሱ ተነጣጥሎ መቅረብ የለበትም፣ ምስክሮች መጉላላት አይገባቸውም በሚል ...
Read More »የተንዳሆ ስኳር ፕሮጀክት የቤት ግንባታ ተቋራጮች ገንዘባችንን ተቀማን ይላሉ
ሰኔ ፴ ( ሠላሳ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የተንዳሆ ቤቶች ልማት ግንባታ ምዕራፍ ሁለት ታሳተፊ ስራ ተቋራጮች ሰኔ 12 ቀን 2009 ዓም ለተወካዮች ምክር ቤት፣ ለጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ለስኳር ኮርፖሬሽን ቦርድ ሰብሳቢ ለአቶ አህመድ አብተው በጻፉት ደብዳቤ ከ200 በላይ የስራ ተቋራጮች ለግንባታ ያወጡት ገንዘብ እንዲመለስላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጀምሮ ላሉ ባለስልጣናት ደብዳቤዎችን ቢጽፉም መልስ ሊያገኙ አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል። “254 ስራ ...
Read More »የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ/ የኦህዴድን የግዛት ማስፋፋት ጥያቄን እንደሚያወግዝ አስታወቀ
ኢሳት ዜና ሰኔ 29 2009 የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት / ኦህዴድ / ከጋምቤላ ክልል ጋር በተያያዘ እያካሄደ ያለውን ማስፋፋት ጥያቄ እንደሚያወግዝ የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግምባር / ጋህዴአግ / ባወጣው መግለጫ አስታወቀ ። በአሁኑ ጊዜ የኦሮሞም ሆነ የጋምቤላ ህዝብ አንገብጋቢ ጥያቄ የግዛት መስፋፋት አለመሆኑን ጋህዴአግ ገልጿል ። የጋምቤላ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ አርነት ግንባር /ጋህዴአግ/ በመግለጫው እንዳለው ህውሃት መራሹ ገዢ ግምባር ...
Read More »ዩኤንድፒ የአፍሪካ ዳይሬክተር አቶ ተናኘወርቅ ጌቱ የጓደግኛቸውን ልጅ ካለውድድር ቀጠሩ
ኢሳት ዜና – ሰኔ 29, 2009 የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የጠቅላይ ሚንስትሩ ሃይለማሪያም ደሳለኝ አማካሪ አምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ሴት ልጅ በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ( ዩኤንድፒ ) በአባቷ እገዛ ያለውድድር እንድትቀጠር መደረጉን አንድ አለም አቀፍ የፕሬስ ተቋም አጋለጠ ። ኢንተር ሲቲ ፕሬስ የተሰኘውና በተባበሩት መንግስታት ጉዳዮች ላይ አተኩሮ የሚሰራው የሚድያ ተቋም እንዳለው የአምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ ...
Read More »