(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 24/2009)በኢትዮጵያ በህዝብ ተቃውሞ ተቋርጧል ተብሎ የነበረው የአህያ እርድና የስጋ ሽያጭ እንደገና መቀጠሉ ታወቀ። በደብረዘይት ከተማ ተገንብቶ የአህያ እርድ ሲያካሂድ የነበረው ቄራ በህዝብ ቅሬታ ስራውን አቁሟል ከተባለ በኋላ ሰሞኑን 250 ሺ ኪሎግራም ስጋ ወደ ቬትናም ለመጀመሪያ ጊዜ ልኳል። የቻይና እንደሆነ የሚታወቀው ሻን ዶንግ ዶንግ የተባለው ኩባንያ በቀን 2 መቶ አህዮችን በማረድ ስጋቸውን ወደውጭ ለመላክ መቋቋሙ ይታወቃል። በ80 ሚሊየን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጠቅላይ አቃቢ ህጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ በጸረ ህዝቦች ግፊት ሚኒስትሮችን እንከስም አሉ
(ኢሳት ዜና–ሐምሌ 24/2009)በሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ፓርላማ በዚህ ሳምንት አስቸኳይ ስብሰባ መጥራቱ ተነገረ ። ፓርላማው የሚሰበሰበው በቅርቡ የሚጠናቀቀውን የአሰቸኳይ አዋጅ የተመለከተ ይሁን በሙሰና የተጠረጠረ ከፍትኛ ባለስልጣን ለማይዝ ገና የታወቀ ነገር የለም። በሙስና የተከሰሱ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን መንግስት ቢያሳውቅም ከፍተኛ ባለስልጣን ከሚላቸው እስካሁን የታሰረ አለመኖሩ ይታወቃል። ጠቅላይ አቃቢ ህጉ አቶ ጌታቸው አምባዬ በጸረ ህዝቦች ግፊት ሚኒስትሮችን አናስርም ሲሉ መግለጫ ...
Read More »አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው አቶ ተስፋዬ ሳህሉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።
(ኢሳት ዜና –ሐምሌ 24/2009)አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው አቶ ተስፋዬ ሳህሉ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በሳምንታዊው የሕጻናት ፕሮግራም ላይ ከ40 አመታት በላይ በማዝናናትና በማስተማር ታላቅ አስተዋጽኦ ያደረጉት አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው አባባ ተስፋዬ ሕይወታቸው ያለፈው እሁድ ሐምሌ 23/2009 መሆኑም ታውቋል። ሰኔ 20 ቀን 1916 በቀድሞው ባሌ ክፍለ ሀገር ኮዳ በተባለ ቦታ የተወለዱትና በ94 አመታቸው ይህችን አለም የተሰናበቱት አንጋፋው የኪነጥበብ ሰው አቶ ...
Read More »በአምቦ ዳግም የህዝብ አመጽ ተቀሰቀሰ
በአምቦ ዳግም የህዝብ አመጽ ተቀሰቀሰ (ኢሳት ዜና–ሐምሌ 21/2009) በአምቦ ዳግም የህዝብ አመጽ ተቀስቅሷል።የመንግስት ተሽከርካሪዎች ላይ ጥቃት ተሰንዝሯል።ሰላም ባስ በተሰኘው የህወሃት ንብረት ላይም ህዝብ እርምጃ መውሰዱ ታውቋል። በደደርና በአለም ገና በግብር ጭማሪው ምክንያት ነጋዴዎች አድማ መምታታቸው ተገልጿል።በአማራ ክልል በሞጣ አድማው ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።በደቡብ ኢትዮጵያ የቦንጋ ነጋዴዎች መማረራቸውን ገልጸዋል።ከ1 ሺ በላይ ነጋዴዎች ፍቃዳቸውን መመለሳቸውን ...
Read More »በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት መካከል የአቶ አባይ ጸሃዬ ባለቤት አንዷ ናቸው ተባለ
በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት መካከል የአቶ አባይ ጸሃዬ ባለቤት አንዷ ናቸው ተባለ (ኢሳት ዜና –ሐምሌ 21/2009) በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ከታሰሩት መካከል የአቶ አባይ ጸሃዬ ባለቤት እንደሚገኙበት ታወቀ። ሌሎች አራት ሰዎችም ከሙስና ወንጀል ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር ውለዋል። የደህንነት ምንጮች እንደገለጹት የአቶ አባይ ጸሃዬ ባለቤት ወይዘሮ ሳሌም ከበደ በቁጥጥር ስር የዋሉት ለልጃቸው መልስ በዝግጅት ላይ እንዳሉ ነበር። አቶ አባይ ጸሃዬ በኢትዮጵያ ...
Read More »የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ለቀቁ
የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ስልጣናቸውን ለቀቁ (ኢሳት ዜና–ሐምሌ 20/2009)የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከሀላፊነታቸው ካገዳቸው በኋላ ስልጣናቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ። ፍርድ ቤቱ የናዋዝ ሸሪፍን ስልጣን ያገደው ከሙስና ጋር በተያያዘ የቤተሰባቸውን ሀብት ካጣራ በኋላ ነው። የፓናማ ሰነድ በመባል የሚታወቀውና የሙስና ወንጀሎችን ያጋለጠው የምርመራ ዘገባ የፓኪስታኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ናዋዝ ሸሪፍ ልጆች ከሀገር ውጭ ኩባንያ እንዳላቸው አጋልጦ ነበር። ይህን ሰነድ ...
Read More »በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረት ተባባሰ
በኢትዮጵያ የነዳጅ እጥረት ተባባሰ (ኢሳት ዜና –ሐምሌ 21/2009) በኢትዮጵያ የተከሰተው የነዳጅ እጥረት የኑሮ ውድነቱን እያባባሰው መሆኑ ተገለጸ። በመላ ሀገሪቱ በተለይም በዋና ዋና ከተሞች የተከሰተው የነዳጅ እጥረት የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን በመገደቡ የምግብ እህሎች፣ሸቀጣ ሸቀጦችና ሌሎች ምርቶች አቅርቦት ቀንሷል። የዋጋ መናር መከሰቱንም የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። በአዲስ አበባ፣ባህርዳር፣ ደሴ ፣ደብረታቦር፣ደብረብርሃንና ደብረማርቆስ ተዟዙረው የገበያ ቦታዎችንና የነዳጅ ማደያዎችን የተመለከቱት ምንጮቻችን በማደያ ቦታዎች የሚታዩት መጨናነቆችና ረጃጅም ሰልፎች፣ታክሲዎችና ...
Read More »የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር የአብርሃ ደስታ የክስ መዝገብ ተዘጋ
የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር የአብርሃ ደስታ የክስ መዝገብ ተዘጋ (ኢሳት ዜና –ሐምሌ 21/2009)የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ 8 ጊዜ በፖሊስ ተገደው ችሎት ሊቀርቡ ባለመቻላቸው ፍርድ ቤቱ መዝገቡን መዝጋቱን ገልጸ። አቃቢ ህግም ሆነ ፖሊስ በውሳኔው በመስማማት ዝምታን መርጠዋል የአረና ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አብርሃ ደስታ በተደጋጋሚ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ጥሪ ቢቀርብላቸውም እሳቸው ግን መምጣት አልቻሉም። ስለዚህም ፍርድ ቤቱ መዝገባቸውን መዝጋቱን አስታውቋል። ...
Read More »ገዢው ፓርቲ በነጋዴዎች እየቀረበ ያለውን ጥያቄ ወደ ጎን በማለት “የበቀል እርምጃ” እየወሰደ ነው ሲሉ ነጋዴዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፉት 2 ሳምንታት ሲካሄድ የቆየውን የነጋዴዎች አድማ ተከትሎ፣ ገዢው ፓርቲ “ችግሩን በውይይት እፈታለሁ” በማለት በየስብሰባዎች ቃል እየገባ ነጋዴዎች ድርጅቶቻቸውን እንዲከፍቱ ለማግባባት ሲሞክር ከቆየ በሁዋላ ወደ በቀል እርምጃ መግባቱን ነጋዴዎች ይገልጻሉ። የሞጣ ከተማ ባለስልጣናት ሰሞኑን በተከታታይ ባደረጉት ስብሰባዎች ለነጋዴዎች ጥያቄ አጥጋቢ መልስ እንደሚሰጡ ሲገልጹ ቢቆዩም፣ ዛሬ ለነጋዴዎች ያላቸውን ንቀትና ...
Read More »ደም አፋሳሽ ሆኖ የቀጠለውን የጉጂ ዞን ግጭት የአካባቢው ባለስልጣናት እንዳስነሱት ነዋሪዎች ተናገሩ
ሐምሌ ፳፩ ( ሃያ አንድ ) ቀን ፳፻፱ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው ግጭት በርካታ ሰዎች መገደላቸውንና እስከ 1 ሺ የሚጠጉ ቤቶች መቃጠላቸውን የሚገልጹት የአካባቢው ነዋሪዎች ግጭቱን የጉጂ ዞን ባለስልጣናት እንዳስነሱት ይገልጻሉ። ኢሳት በተከታታይ ያቀረባቸው ዜናዎች የአንድን ወገን መረጃ ብቻ ማእከል ያደረገ ነው በማለት ቅሬታቸውንም አቅርበዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት ግጭቱ የጉጂ ዞን ባለስልጣናት በደቡብ ክልል ...
Read More »