.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአቶ አግባው ሰጠኝ ህይወት አደጋ ላይ መውደቁ ተሰማ

(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 10/2009)የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የሰሜን ጎንደር አስተባባሪ አቶ አግባው ሰጠኝ ህይወቱ አደጋ ላይ መውደቁን አስታወቀ። ጎንደር ኮሽ ባለ ቁጥር ስቃይና ሰቆቃ ይፈጸምብኛል በሚል ለፍርድ ቤት የገለጸው አቶ አግባው ሰጠኝ፡ በህይወት ስለመቆየቴም ዋስትና የለኝም በማለት መናገሩ ተሰምቷል። ማረሚያ ቤቱ ፡አቶ አግባው እስረኞችን በማሳመጽና መሳሪያ ከጠባቂዎች ለመንጠቅ በመሞከር ከፍተኛ ችግር እየፈጠረ ነው በማለት ምላሽ ሰጥቷል። የመብት ተቆርቋሪ ኢትዮጵያውያን በአቶ አግባው ...

Read More »

በሶስት ሳምንት ብቻ 17 ኢትዮጵያውያን በመብረቅ ተመተው ሕይወታቸው አለፈ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 10/2009)በሶስት ሳምንት ብቻ 17 ኢትዮጵያውያን በመብረቅ ተመተው ሕይወታቸው አለፈ። በርካታ እንስሳትም በአደጋው አልቀዋል። ጉዳት የደረሰባቸው ግለሰቦች ደግሞ በህክምና ላይ ይገኛሉ። የቻይናው ዜና አገልግሎት ዥንዋ እንደዘገበው የመብረቅ አደጋው የተከሰተው በኢትዮጵያ አፋር ክልል ነው። የአፋር ክልላዊ መንግስት የፖሊስ ሃላፊ አሊ ቡቶ እንደተናገሩት ከክረምቱ ጋር ተያይዞ በተከሰተው መብረቅ ባለፈው እሁድ ብቻ አራት ሰዎች ሲሞቱ፣በአጠቃላይ በሶስት ሳምንት ውስጥ በመብርቅ የሞቱት ሰዎች ቁጥርም ...

Read More »

የአምባሳደሮች ወደሀገር የመመለስ ጉዳይ አነጋጋሪ ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 10/2009) የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በቅርቡ በዲፕሎማቶቹ ላይ በጀመረው ብወዛ ከእነ አምባሳደር ግርማ ብሩ በተጨማሪ በካናዳ፣ሲውዲን፣ሱዳን፣ደቡብአፍሪካ፣ኳታር፣ዩናይትድ አረብ ኢምሬትና ሩዋንዳ የሚገኙ አምባሳደሮችን በማንሳት በአዳዲስ ተሿሚዎች መተካቱን አስታወቀ። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ ይፋ ባደረገው መረጃ በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ግርማ ብሩ በብአዴኑ ካሳ ተክለብርሃን መተካታቸውን ያረጋገጠ ሲሆን፣ በቻይና ቤጂንግ የሚገኙት አቶ ስዩም መስፍንም በሌላው የሕወሃት አባል በአምባሳደር ብርሃነ ገብረክርስቶስ መተካታቸውን አስታውቋል። አምባሳደር ...

Read More »

የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ በጋዜጠኝነቱ የታሰረ የለም አሉ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 10/2009) የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ቴድሮስ አድሃኖም በኢትዮጵያ በጋዜጠኝነቱ የታሰረ የለም አሉ በቅርቡ የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ሆነው የተሾሙት ቴድሮስ አድሃኖም ኢትዮጵያ ውስጥ በጋዜጠኝነቱ ወይም ሀሳቡን በነጻነት በመግለጹ የታሰረ ጋዜጠኛ የለም ሲሉ ከፎረን አፌርስ መጽሔት ጋር ባደረጉት ምልልስ ተናግረዋል። የማህበረሰብን ጤና የተመለከቱ መረጃዎችን ለሕዝብ ለማዳረስ መገናኛ ብዙሃን ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወቱ ቀደም ብሎ መናገራቸውን ተከትሎ እርሳቸው አባል ...

Read More »

በባህርዳር የሰማዕታት ቀንን አክብራችኋል በሚል የታሰሩ ታዋቂ ነጋዴዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት እየቀረቡ ነው

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 9/2009) በባህር ዳር ከተማ ነሃሴ አንድ ቀን የዋለውን የሰማዕታት ቀን አክብራችኋል በሚል በእስር ላይ ይገኙ የነበሩ ታዋቂ ነጋዴዎች እና የከተማዋ ነዋሪዎች ፍርድ ቤት እየቀረቡ ናቸው፡፡ በከተማዋ በሚገኙ የተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች የሚገኙት ነጋዴዎች በባህር ዳር ከተማ ፍርድ ቤቶች ቀርበው የጊዜ ቀጠሮ ቀርቦባቸዋል ፡፡ ክሱ የቀረበላቸው አንዲት ሴት ዳኛ የንግድ መደብርን መዝጋት መብት ነው በማለታቸው በችሎቱ የተገኙት ፖሊሶች ወንጀሉን ከአድማ ...

Read More »

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት ሊዘጋ ነው ተባለ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 9/2009) አንጋፋውና ነባሩ ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በኤሌክትሪክ ሃይል እጦት ሊዘጋ መሆኑን የፋብሪካው ስራ አስኪያጅ ገለጹ። ዋና ስራ አስኪያጁ ኢንጂነር አካሉ ገብረህይወት እንደገለጹት ፋብሪካው ካለው አቅም ከግማሽ በታች እያመረተ ነው። የሀገሪቱን የሲሚንቶ አቅርቦት የተቆጣጠረው ሞሶቦ ሲሚንቶ ከአቅሙ በላይ እያመረተ ሙገር ሲሚንቶ ሊዘጋ መቃረቡ ሆን ተብሎ የተደረገ ሊሆን እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ። የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ቀደም ባሉ አመታት የሀገሪቱን የሲሚንቶ ፍላጎት ...

Read More »

ባለስልጣናት ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ መጣሉ ተሰማ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 9/2009)የቀድሞው የሕወሃት ከፍተኛ ባለስልጣናትን ጨምሮ በስልጣንና በጡረታ ላይ በሚገኙ የተወሰኑ ባለስልጣናት ላይ ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ መጣሉን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ከባለስልጣናቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖችም ሊወጡ ሲሉ ከቦሌ አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተይዘው መመለሳቸውንም ምንጮቹ አመልክተዋል። የእስር እርምጃውን እየወሰደ ያለው ቡድን የፍርድ ቤት ትእዛዝ በማውጣት የጣለው ግልጽ አገዳና በመምሪያ የተላለፈ ማስጠንቀቂያ ባይኖርም ከሐገር ለመውጣት የተከለከሉ መኖራቸውን ግን የኢሳት ምንጮች ...

Read More »

አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ ፈቀደ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 9/2009) አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም የ4 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር ብድር ለኢትዮጵያ መፍቀዱን አስታወቀ። ይህም የሀገሪቱን ብድር ከ30 ቢሊየን ዶላር በላይ እንዳደረሰው ተመልክቷል። በዜሮ ወለድ ለድሃ ሀገራት የሚሰጠው ይህ ብድር በቀጣዩ የፈረንጆቹ አመት እንደሚለቀቅም ተመልክቷል። የሕወሃት ኢህአዴግ መንግስት በአንድ አመት በብድር የሚያገኘው ገንዘብ የደርግ መንግስት በ17 አመት ከተበደረው ብልጫ እንዳለው መረጃዎች አመልክተዋል። በአለም ባንክ ስር ያለው አለም አቀፉ ...

Read More »

የአርብቶ አደሮች ከብቶች በከፍተኛ ደረጃ እያለቁ መሆናቸውን ፋኦ አስታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 9/2009) በኢትዮጵያ በደቡብና በደቡብ ምስራቅ ከተከሰተው ድርቅ ጋር በተያያዘ የአርብቶ አደሮች ከብቶች በከፍተኛ ደረጃ እያለቁ መሆናቸውን የአለም የምግብ ድርጅት ፋኦ አስታወቀ። እስካሁን ብቻ 2 ሚሊየን ከብቶች ሞተዋል። ከብቶቹ በከፍተኛ መጠን እያለቁ የሚገኙት በግጦሽ ሳርና በውሃ እጦት መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። በኢትዮጵያ ከድርቅ ጋር በተያያዘ የተረጂዎች ቁጥር እያሻቀበ መምጣቱ ከምግብ እጥረት ጋር በተገናኘ ሰዎችም ሕይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ...

Read More »

በባህር ዳር ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ በመንግስት ዘጋቢ ፊልም በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ታወቀ

(ኢሳት ዜና–ነሐሴ 8/2009) ቅዳሜ ምሽት በባህር ዳር ከደረሰው የቦምብ ጥቃት ጋር በተያያዘ በመንግስት በኩል ዘጋቢ ፊልም በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ታወቀ። ቦምቡን ያፈነዱትና በቁጥጥር ስር የሚገኙት ተጠርጣሪዎች ከደቡብ ጎንደር ዕብናት የመጡ ናቸው የሚል መልዕክት የሚያስተላልፈው ዘጋቢ ፊልም ቀረጻው እየተካሄደ ሲሆን በቅርቡ እንደሚለቀቅ የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የግብር ጭማሪውን በመቃወም በምስራቅ ጎጃም በተለያዩ ከተሞች የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ መቀጠሉ ታውቋል። በባህርዳር ከ100 በላይ ...

Read More »