(ኢሳት ዜና–መስከረም 9/2010)በአዲስ አበባ የመብራትና የውሃ ችግር መባባሱ ተገለጸ። በአብዛኛው የከተማዋ አካባቢዎች ውሃ ከጠፋ ቀናት መቆጠራቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። ከፍተኛ የሆነ የመብራት መቆራረጥ መኖሩ ደግሞ ነዋሪዎቹን ለከፋ ችግር መዳረጉን ለማወቅ ተችሏል። ከእነዚህ በተጨማሪ የነዳጅና የስኳር እጥረትም በከተማዋ በመከሰቱ ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን ነዋሪዎች በምሬት እየተናገሩ ነው። በሌላ በኩል መንግስት ወደ ውጭ ስኳር በመላክ የውጭ ምንዛሪ ለማግኘት እየሰራ መሆኑን ከገለጸ ከቀናት በኋላ 7ሚሊዮን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በኢትዮጵያ በየቦታው እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችና የተከተለው ቀውስ ምክንያቱ ሕወሃት በመሆኑ ሊወገድ ይገባል ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 9/2010) በኢትዮጵያ በየቦታው እየተከሰቱ ያሉ ችግሮችና የተከተለው ቀውስ ምክንያቱ ሕወሃት በመሆኑ ይህን ቡድን ከማስወገድ ውጭ መፍትሄ እንደማይኖር አርበኞች ግንቦት 7 አስታወቀ። የሕወሃት የስልጣን ዘመን እያበቃ ባለበት በአሁኑ ወቅት በኦህዴድና ብአዴን ውስጥ ያሉ እውነታውን የተገነዘቡ ወገኖች በመጨረሻው ሰአት ራሳቸውን ከተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ ስራ እንዲሰሩም አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አቅርቧል። የወቅቱን የኢትዮጵያ ሁኔታ በማስመልከት አርበኞች ግንቦት 7 በሳምንቱ መጨረሻ ባወጣው ...
Read More »በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ካልሰፋ ሀገሪቱ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ ትችላለች ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 9/2010) በኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳሩ ካልሰፋ ሀገሪቱ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ ልትገባ እንደምትችል የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነር አስጠነቀቁ። ኮሚሽነሩ ዛይድ ራድ አልሁሴን በዋሽንግተን ዲሲ ከሰብአዊ መብት ማህበረሰብ አባላትና ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ውይይት እንደገለጹት ኢትዮጵያውያን መብታቸው ካልተከበረና የፖለቲካ ምህዳሩ ካልሰፋ በሀገሪቱ የከፋ ቀውስ ሊከሰት ይችላል። የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩ ዛይድ ራድ አልሁሴን በኢትዮጵያ ባለፈው አመት የተቀሰቀሰውን ሕዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ ...
Read More »በመጪው የእሬቻ በአል ያለፈው አመት ግድያና እልቂት እንዳይደገም ሂዩማን ራይትስዎች አሳሰበ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 9/2010) በመጪው የእሬቻ በአል ያለፈው አመት ግድያና እልቂት እንዳይደገም የኢትዮጵያው አገዛዝ ታጣቂዎች ከሀይል ርምጃ እንዲቆጠቡ ሂውማን ራይትስ ዎች አሳሰበ። የኦሮሞ የእሬቻ በአል ላይ ባለፈው አመት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ በመግባት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይትና ይህንን ተከትሎም በደረሰው መተፋፈግ መገደላቸውን አለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋም አስታውሷል። በዘንድሮው በአልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በሚገኙበት በዚህ በአል ተመሳሳይ ድርጊት እንዳይፈጸም ...
Read More »ቢቢሲ በኢትዮጵያ በ3 ቋንቋዎች አገልግሎት መስጠት ጀመረ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010)የብሪታኒያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን/ቢቢሲ/የሚዲያ አፈና ባለባቸው ሀገራት በጀመረው የማስፋፊያ ፕሮግራም መሰረት በኢትዮጵያ በ3 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የኢትዮጵያና የኤርትራ አድማጮችን ኢላማ ያደረገው የቢቢሲ ፕሮግራም አገልግሎት በኢንተርኔትና በፌስቡክ ይፋ ተደርጓል። በቀጣይም የሬዲዮ ስርጭት እንደሚጀምር ተገልጿል። በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው እና በተለያዩ የአለም ቋንቋዎች የሚደመጠው ቢቢሲ ለኢትዮጵያና ለኤርትራ አድማጮች በ3 ቋንቋዎች ማለትም በአማርኛ፣ በኦሮምኛና በትግርኛ ...
Read More »የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚመለከተውን ረቂቅ የአሜሪካ ምክር ቤት እንዲያጸድቀው ተጠየቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሜሪካ ምክር ቤት አባላት ያረቀቁትንና የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታ የሚመለከተውን ረቂቅ የአሜሪካ ምክር ቤት እንዲያጸድቀው ጠየቁ። አሜሪካ በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን እልቂት በገንዘብ መደገፍዋን እንድታቆም ባካሄዱት ሰላማዊ ሰልፍ ጠይቀዋል። ዛሬ ወደ አሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በመጓዝ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ኢትዮጵያውያን ሰልፈኞች በኢሬቻ አመታዊ በአል ላይ ያለቁ ኢትዮጵያውያንን ለማሰብ፣እንዲሁም የሰሞኑን ዕልቂት በማውገዝ ድምጻቸውን አሰምተዋል። ...
Read More »ቴዲ አፍሮ የኢሳት የ2009 የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል ተመረጠ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) ዝነኛው የሙዚቃ ሰው ቴዲ አፍሮ በከፍተኛ ድምጽ የኢሳት የ2009 የአመቱ ምርጥ ሰው በሚል ተመረጠ። በኢሳት የ2010 የአዲስ አመት ፕሮግራም ላይ በተካሄደው ስነስርአት የኢሳት የሙሉጌታ ሉሌ መታሰቢያ የአመቱ ምርጥ ሰው ሽልማት ለድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ በኪነጥበብ ባለሙያዎች አማካኝነት ተበርክቷል። በኢሳት የ2010 አዲስ አመትን አስመልክቶ በተካሄደው ፕሮግራም ላይ እንደተገለጸው ከነሀሴ 8 እስከ ጳጉሜ 4/2009 በኢሳት የስልክ ...
Read More »በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቀሉ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) በኦሮሚያና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ግጭት እስካሁን ከ50 ሺ በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተገለጸ። በሁለቱም ክልሎች አካባቢዎች በነበረው ግጭት የሞቱት ሰዎች ልክ በውል ባይታወቅም በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እንደሞቱ ግን ግምቶች አሉ። እየተባባሰ በሄደው ግጭት ሳቢያ ሲወዛገቡ የነበሩት የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶች በፌደራል ጉዳዮች ሚኒስቴር አማካኝነት የጋራ መግለጫ እንዲሰጡ ተደርገዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ሁለቱ ፕሪዝዳንቶች መግለጫ ከሰጡ በኋላ ውጊያ ...
Read More »ያለህዝብ ፍቃድ በፖለቲካ ውሳኔ በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ተጠየቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 8/2010) ያለህዝብ ፍቃድ በፖለቲካ ውሳኔ በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ህዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ተጠየቀ። ትላንት በ8 ቀበሌዎች በተካሄደው ሕዝበ ውሳኔ 7ቱ ቀበሌዎች በነባሩ የሰሜን ጎንደር አስተዳደር ስር መቆየትን መምረጣቸው ተገልጿል። ይህን ተከትሎም ቀደም ሲል በህወሃት መንግስት በተከለሉት 42 ቀበሌዎች ላይ ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ በመጠየቅ ላይ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ምርጫ ቦርድ የትላንቱን ህዝበ ውሳኔ ውጤት በፌደሬሽን ምክርቤት በኩል እንደሚገለጽ አስታውቋል። ...
Read More »የኬንያ ፍርድ ቤት 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ሲል ውሳኔ አሳለፈ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010) የኬንያ ፍርድ ቤት ወደ ሀገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብተዋል ያላቸው 40 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይመለሱ ሲል ውሳኔ አሳለፈ። ፍርድ ቤቱ ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው ከመመለሳቸው በፊትም የአንድ ወር እስራትና እያንዳንዳቸው 20 ሺ ሽልንግ እንዲቀጡም ወስኗል። አብዛኞቹ እድሜያቸው በ20ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሆነ የተገለጸው ኢትዮጵያውያን ወደ ኬንያ በህገወጥ መንገድ የገቡት ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሸጋገር ነው በሚል ፍርድ ቤቱ ያቀረበባቸውን ክስ አምነዋል። ...
Read More »