(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010) የጸጥታ ሃይሎች ወገን ለይተው በድንበር ግጭት መሳተፋቸው የሀገራችንን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት አስጊ እንዳደረገው ኢሶዴፓ ገለጸ። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ብቻ ከወሰን አካባቢ ግጭቶች ርቀው በሚኖሩ አካባቢዎች የሚካሄደው ግድያና ማፈናቀል ተጠናክሮ መቀጠሉ እንዳሳሰበውም ኢሶዴፓ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። የኢትዮጵያን አንድነትና የሕዝባችንን ሰላምና ደህንነት ማረጋገጥ ከሁሉም ጉዳይ ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል በሚል ርዕስ የኢትዮጵያ ሶሻል ዲሞክራቲክ ፓርቲ መግለጫ አውጥቷል። በመግለጫውም ባለፉት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በግጨው ጉዳይ ብአዴን ውዝግብ ውስጥ ገባ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010)በግጨው ጉዳይ ብአዴን ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ተገለጸ። የአማራ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሜቴና የአማራ ክልል ካቢኔ በማያውቁት ሁኔታ ግጨውን ለትግራይ ክልል አሳልፈው መስጠታቸው በባህርዳር እየተካሄደ ባለው አጠቃላይ የድርጅት ጉባዔ ላይ ዋና አጀንዳ ሆኖ መነሳቱ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት ያለስምምነት የተበተነውን የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባን ተከትሎ የተጠራው የድርጅቱ አጠቃላይ ጉባዔ የህወሀት የበላይነትን በግንባር ቀደምትነት በማንሳት ውይይት አካሂዷል። ...
Read More »በደብረታቦር ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶች ታፍሰው መወሰዳቸው ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 15/2010)በደብረታቦር ትላንት የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ወጣቶችና የሀይማኖት አባቶች ታፍሰው መወሰዳቸው ተገለጸ። በኢየሱስ ደብር የሚተከለውን የመረጃ ቋት ማማ በመቃወም ወደቤተክርስቲያን መስቀል ይዘው በተመሙ ነዋሪዎች ላይ የመንግስት ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው በርካታ ሰዎች ቆስለዋል። ደብረታቦር ቁጥሩ የበዛ የመንግስት ሃይል የገባ ሲሆን ቤት ለቤት በመዘዋወር ወጣቶችን አፍሰው ወስደዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል በሚልም የተወሰኑ የሃይማኖት አባቶች መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። የኢየሱስ ደብር ቤተክርስቲያን አባት ...
Read More »የሕንዱ ካራቱሪ ኩባንያ የሕወሃቱ አገዛዝ ካሳ እንዲከፍለው ጠየቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 12/2010)በኢትዮጵያ ለኢንቨስትመንት በጋምቤላ ክልል የወሰደውን ሰፊ መሬት የተነጠቀው የሕንዱ ካራቱሪ ኩባንያ የሕወሃቱ አገዛዝ ካሳ እንዲከፍለው ጠየቀ። የኩባንያው ባለቤትና ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሳይ ካራቱሪ ብሉምበርግ ለተባለው የዜና ወኪል በላኩት መግለጫ ኢትዮጵያ በነበረን ቆይታ ተሰላችተናል ደክሞናልም ብለዋል። ሚስተር ካራቱሪ በኢትዮጵያ የነበራቸው የንግድ ፈቃድ መሰረዙንና ንብረታቸው ግን እንዳልተመለሰላቸው ገልጸዋል። የህንዱ ኩባንያ ካራቱሪ ለኢንቨስትመንት ወደ ኢትዮጵያ ሲመጣ 3 መቶ ሺ ሔክታር መሬት ...
Read More »በኦሮሞዎችና በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አወገዘ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 12/2010)በምስራቅ ኢትዮጵያ በኦሮሞዎችና በኢትዮጵያ ሶማሌዎች ላይ የተፈጸመውን ግድያ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ንቅናቄ አወገዘ። የችግሩ ፈጣሪና አስፈጻሚ ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በመሆኑ መፍትሄውም ስርአቱን ማስወገድ ብቻ ነው ሲል የትብብር ጥሪ አቅርቧል። የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ መድረክም ከአዲስ አበባ ድርጊቱን በማውገዝ የስርአቱ ከፋፍለህ ግዛው ውጤት ነው ሲል መግለጫ አውጥቷል። ሕወሃት መራሹ ግፈኛ ቡድን ለ26 አመታት የተካነበትን ጎረቤት ከጎረቤት፣ማህበረሰብ ከማህበረሰብ የማናከስና የማጣላት ሴራውን ...
Read More »የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ያለስምምነት ተበተነ
(ኢሳት ምንጮች–መስከረም 12/2010)የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ብአዴን/ማዕከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ ያለስምምነት መበተኑን ምንጮች ገለጹ። በስልጣን ላይ ለ2 አመታት የቆየው የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አዲስ ምርጫ ማካሄድ ይጠበቅበት ነበር::የሚባረሩ እንዳሉም ይነገራል። የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት በግጨው የስምምነት ጉዳይና በቅማንት ሕዝበ ውሳኔ ውጤት መነታረካቸውን ምንጮቻችን ገልጸዋል። የብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባ በስምምነት የተጠናቀቀ ለማስመሰል የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮንን የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ መግለጫ ሰጥተው ...
Read More »በቅርቡ በሚከበረው የእሬቻ በአል አንድም የታጠቀ ፖሊስ ወይም ወታደር እንደማይሰማራ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 14/2010)በኦሮሚያ ቢሾፍቱ ከተማ በቅርቡ በሚከበረው የእሬቻ በአል አንድም የታጠቀ ፖሊስ ወይም ወታደር እንደማይሰማራ የክልሉ መንግስት ገለጸ። የኦሮሚያ ክልላዊ አስተዳደር በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች ይሳተፉበታል በተባለው የእሬቻ በአልን ለመቆጣጠር ያልታጠቁ 3 መቶ ወጣቶች ብቻ እንደሚሰማሩ ገልጿል። ባለፈው አመት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይትና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተፈጠረ መተፋፈግ መገደላቸው ይታወሳል። ዘንድሮ ምንም አይነት ፖሊስ በአካባቢው አይደርስም መባሉ ላለፈው እልቂት ተጠያቂው ...
Read More »በመንገድ ግንባታና ስርጭት ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ሆና የተገኘችው ትግራይ ናት ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 12/2010) በኢትዮጵያ ባለፉት 10 አመታት በመንገድ ግንባታና ስርጭት ከአዲስ አበባ ቀጥሎ ግንባር ቀደም ሆና የተገኘችው ትግራይ መሆኗን የአለም ባንክ ጥናት አመለከተ። አማራ ክልል ደግሞ የመጨረሻ ሆኖ ተመዝግቧል። ለመንገድና ለልዩ ልዩ ፕሮጀክቶች በስልጣን ላይ ላለው የኢትዮጵያ መንግስት በብድርና በስጦታ ገንዘብ በማቅረብ የሚታወቀው የአለም ባንክ በኢትዮጵያ ውስጥ ባለፉት 10 አመታት የተካሄዱ የመንገድ ግንባታዎችን የገመገመበትን ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። አዲስ አበባና የኦሮሚያ ...
Read More »በሜክሲኮ ፍርስራሽ ስር የተቀበሩ ሕጻናትን ለማትረፍ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየተሯሯጡ ነው
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) በሜክሲኮ በደረሰው ርዕደ መሬት ፍርስራሽ ስር የተቀበሩ ሕጻናትን ለማትረፍ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየተሯሯጡ መሆናቸው ተነገረ። ሕጻናትና ታዳጊ ልጆች ከርእደ መሬቱ ጋር በተያያዘ ከተደረመሰው ትምህርት ቤት ሕንጻ ስር ሆነው የአድኑን ጥሪ እያሰሙ መሆናቸው ተነግሯል። በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 1 በተመዘገበው ርእደ መሬት እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የሜክሲኮው ርዕደ መሬት ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነው።በሜክሲኮ መናገሻ ከተማ የደረሰውን የመሬት ...
Read More »የኢጋድ አባል ሀገራት የደቡብ ሱዳንን ችግር ከመፍታት ይልቅ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እያስቀደሙ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪና የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት የኢጋድ አባል ሀገራት የደቡብ ሱዳንን ችግር ከመፍታት ይልቅ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እያስቀደሙ ችግር መፍጠራቸውን ገለጹ። ሬክ ማቻር በኢጋድ አባል ሀገራት ላይ ተስፋ መቁረጣቸውን ያስታወቁት ባለፈው ሀሙስ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጻፉት ደብዳቤ መሆኑን መረዳት ተችሏል። የአማጽያኑ መሪ ዶክተር ሬክ ማቻር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 14/2017 የጻፉትና በሱዳን ትሪቡን በኩል ...
Read More »