(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት በገዛ ፈቃዳቸው ለመልቀቅ ያመለከቱት አቶ አባዱላ ገመዳ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ስብሰባ ላይ ቅሬታቸውን ማቅረባቸው ተሰማ። አቶ አባዱላ በእኔም ሆነ በድርጅቴ ኦሕዴድ ላይ የተፈጠረው ችግር በኢሕአዴግም ሆነ በመንግስት መዋቅሮች ውስጥ የሕወሃት የበላይነት በመኖሩ ነው ብለው እቅጩን ተናግረዋል። በስብሰባው መጀመሪያ ላይ ቅሬታቸውን በይፋ ያቀረቡት አቶ አባዱላ ገመዳ ከተወሰኑ የኦሕዴድ አባላት ድጋፍ ቢያገኙም የተወሰኑት ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በመከላከያ ሰራዊት 7 ሰላማዊ ሰዎች ተገደሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በኦሮሚያ ክልል ከያቤሎ እስከ ሞያሌ መስመር በመከላከያ ሰራዊት 7 ሰላማዊ ሰዎች መገደላቸው ተገለጸ። በአከባቢው ባሉ ወረዳዎች ግጭት ተፈጥሯል። መንገዶች መዘጋታቸው ታውቋል። በመቱ፣ በነቀምት፣ በደምቢዶሎ፣ በዋደራ፣ በሻኪሶና በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ዛሬ ተቃውሞች ተካሂደዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግጭት ተለይቶት የማያውቀው የሞያሌ መስመር በየዕለቱ ሰዎች መገደላቸው እየተለመደ መቷል። በተለይም የመከላከያ ሰራዊትና የአጋዚ ጦር በህዝቡ ላይ በሚወስዱት ርምጃ የሚገደሉ ሰዎች ...
Read More »በሚሊሺያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻ ተጀመረ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 10/2010) በአማራ ክልል በጎጃምና ጎንደር መስመር ዋና ዋና መንገዶች ላይ በሚሊሺያ ሰራዊትና በፌደራል ፖሊስ ጥብቅ ፍተሻና ጥበቃ መጀመሩ ተገለጸ። የህዝብ ንቅናቄ በተፈጠሩባቸው ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት በብዛት መግባቱ ተገልጿል። በዩኒቨርስቲዎች አሁንም ትምህርት አልተጀመረም። በአፋር፣ ጋምቤላና አሶሳ ዩኒቨርስቲዎች ለተማሪዎች የንብረት ማውጫ ፍቃድ መከልከሉም ታውቋል። በአማራ ክልል በተለያዩ ቦታዎች ውጥረት መንገሱን የሚያሳዩ መረጃዎች ለኢሳት ደርሰውታል። በጎጃምና በጎንደር መስመሮች ከፍተኛ ፍተሻና ጥበቃ ...
Read More »ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገለት
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የጎንደሩ ፋሲል ከነማ እግር ኳስ ክለብ በኦሮሚያ የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል ተደረገለት። የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች የፋሲል ከነማን ተጫዋቾች “ፋሲል ኬኛ” በማለት በሞተረኛ ፖሊሶች አጅበው ፍቅራቸውን በመለገስ እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል። የአዳማ ከነማ ህዝብ ለፋሲል ከነማ ያደረገው አቀባበል በኦሮሚያና አማራ ሕዝብ መካከል ያለው ትስስር ጠንካራ መሆኑን አመላክቷል። የሕወሃትን አገዛዝ በመቃወም በአንድ ወቅት የጎንደርና የባህርዳር ህዝብ የኦሮሞ ደም ...
Read More »ሲሪል ራምፖሳ አሸነፉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ/ኤ ኤን ሲ/ ፓርቲን የመሪነት ቦታ ምክትል ፕሬዝዳንቱ ሲሪል ራምፖሳ አሸነፉ። የመሪነቱን ቦታ ማን ይወስዳል የሚለውን ውጤት ለማወቅ ደቡብ አፍሪካውያን በጉጉት በመጠባበቅ ላይ ነበሩ። አዲሱ ተመራጭ ሲሪል ራምፖሳ በስልጣን ላይ ያሉትን የሀገሪቱን ፕሬዝዳንትና የፓርቲውን መሪ ጃኮብ ዙማን ይተካሉ። የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ የኤ ኤን ሲ ፓርቲ መሪን ለመምረጥ በተካሄደው ምርጫ በምክትል ፕሬዝዳንቱ ሲሪል ራምፖሳና በቀድሞው የአፍሪካ ...
Read More »የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መኖሪያ ቤቶች ተሸጡ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሊቀመንበር የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መኖሪያ ቤቶች በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተሽጠው ለመንግስት ገቢ መሆናቸውን የፌደራል ጠቅላይ አቃቢ ህግ አስታወቀ። በእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ መዝገብ ሕገ መንግስታዊ ስርአቱን በሃይል ለመናድ ሞክራችኋል በሚል በተመሰረተባቸው ክስ የሞት ፍርድ የተወሰነባቸው ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋና አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ንብረታቸውም እንዲወረስ በፍርድ ቤት ተወስኗል። ጠቅላይ አቃቢ ህግ አደረኩት ...
Read More »በኢትዮጵያ ያለው ቀውስና ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) በኢትዮጵያ ያለው ቀውስና ግጭት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኢሕአዴግ ባለስልጣን መግለጻቸው ተነገረ። በጨለንቆ በቅርቡ የተፈጸመውን ጅምላ ግድያ ለማውገዝ በአምቦ ከተማ በተካሄደ ተቃውሞ በመከላከያ ሰራዊትና በኦሮሚያ ፖሊስ መካከል በተደረገው የተኩስ ልውውጥ የሞቱና የቆሰሉ እንደነበሩም ለማወቅ ተችሏል። እዚህ ደረጃ የደረሰው የሀገሪቱ ቀውስና ግጭት አሳሳቢ እየሆነ የመጣውም በኢትዮጵያ ያለውን የጸጥታ ችግር ለመፍታት ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤቱ ...
Read More »በኦሮሚያ ለተቀሰቀሰው ተቃውሞ የክልሉ መንግስትና የክልሉ የጸጥታ ሃይል ተጠያቂዎች ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) በኦሮሚያ ክልል በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የክልሉ መንግስትና የክልሉ የጸጥታ ሃይል ሰልፈኞቹን አትንኳቸው በማለት የያዙት አቋም ለሰው ሕይወት ማለፍና ለንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል ሲል የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ለተቃውሞ አደባባይ የወጡት ሰልፈኞች በንብረት ላይ ካደረሱት ጉዳት በተጨማሪ በጸጥታ ሃይሎች ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን እንዲሁም የወረዳና የቀበሌ አመራሮችን በማውረድ አዳዲስ ሽስከ መሾም መድረሳቸውንም ይፋ አድርገዋል። በፌደራል ፖሊስ በተዘጋጀውና ለአመራሩ በቀረበው በባለ ...
Read More »የተጀመሩት ተቃውሞዎች እንደቀጠሉ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) በድሬዳዋ ዩንቨርስቲ ተቃውሞ ተቀሰቀሰ። ዛሬ በዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የአጋዚ ሰራዊት ወደ ግቢው በመግባት ድብደባ የፈጸመ ሲሆን በርካታ ተማሪዎች ተጎድተው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል። በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ዛሬ ተቃውሞ መደረጉ ታወቀ። በአማራ ክልል ትምህርት በተቋረጠባቸው ዩኒቨርስቲዎች ትምህርት አልተጀመረም። በደብረማርቆስ ፣ደብረታቦር ፣ባህርዳርና ወልድያ ዩኒቨርስቲዎች አብዛኛው ተማሪ ወደየቤተሰቡ መሄዱ ታውቋል። በሌላ በኩል ካለፈው ሳምንት ጀምሮ የተባባሰውን የኦሮሚያ ክልል ...
Read More »የተገደሉት የሶማሌ ክልል ተወላጆች በኦሮሚያ ፖሊስ ስር ተጠልለው የነበሩ ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 9/2010) በምዕራብ ሀረርጌ በድሮሎቢ ወረዳ በጋድሌ ቀበሌ የተገደሉት እስከ አንድ መቶ የሚደርሱ የሶማሌ ክልል ተወላጆች በኦሮሚያ ፖሊስ ስር ተጠልለው የነበሩ መሆናቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። አቶ ሃይለማርያም በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ድንገት በሰጡት መግለጫ እንዳሉት በኦሮሚያና ሶማሌ ክልልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች ግጭቱ አገርሽቶ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሞትና የአካል ጉዳት ደርሷል። መከላከያና የጸጥታ ሃይሎች ወደ አካባቢው የገቡት ግን ተልዕኮ ተሰጥቷቸው ...
Read More »