(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራው የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ በሀገሪቱ አዲስ የሽግግር መንግስት እንዲመሰረት ጥሪ አቀረበ። ፓርቲው ባካሄደው የድርጅቱ 2ኛ ጉባኤ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታን ገምግሟል። ዶክተር መረራና አቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ ሁሉም የኦፌኮ አመራሮች ከእስራት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርቧል። የኦህዴድ መሪዎች ለሕዝብ ላሳዩት ወገናዊነትም አድናቆቱን ገልጿል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ከተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከመጡ አባላቱ ጋር ያካሄደውን የድርጅቱን 2ኛ ጉባኤ በማስመልከት ባለፈው ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
መንግስት ችግሮችን በድርድርና በውይይት እንዲፈታ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) በኢትዮጵያ የተከሰቱ ችግሮችን መንግስት በድርድርና በውይይት እንዲፈታ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ጥሪ አቀረበች። አገሪቱን ከውድቀት፣ ሕዝቡንም ከሞትና ከስደት ለመታደግ መንግስት ከባድ ሞራላዊና መንግስታዊ ሃላፊነት እንዳለበትም አሳስባለች። የሃይማኖት አባቶችም አጥፊውን ወገን ያለፍርሃት እንዲገስጹም ጥሪዋን አቅርባለች። የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ እንዳሳሰባት የገለጸችው የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በ34ኛው የጳጳሳት መደበኛ ጉባኤ በጉዳዩ ላይ ከመከረች በኋላ መግለጫ ማውጣቷ ተመልክቷል። የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በብጹዕ ካርዲናል ...
Read More »በሀገሪቱ ያለው ችግር የብሔር ፖለቲካ ያመጣው መዘዝ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 16/2010) የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ያሳሰባቸው ታዋቂ ዜጎች በሀገሪቱ ያለው ችግር የብሔር ፖለቲካ ያመጣው መዘዝ መሆኑን ገለጹ። በወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ላይ አስተያየታቸውን የሰጡት ዜጎች በአሁኑ ጊዜ የሰው ሕይወትና ንብረት እየወደመ እንዲመጣ ምክንያት የሆነው ልዩነትን የሚያበረታታው ሕገመንግስት ነው ብለዋል። ከፊሎቹ ይህን ሀሳብ ቢቃወሙም ብዙዎቹ ግን የብሔር ፖለቲካው ያመጣውን መዘዝ ለማስወገድ ሕዝቡ ለአንድነቱ መቆም አለበት ብለዋል። ሕዝባዊና ሀገራዊ እርቅ እንዲደረግ ጥሪ ...
Read More »አንድ የአፍጋኒስታን ተወላጅ 19 ያህል ሰዎችን አቆሰለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) በአውስትራሊያ ሜልቦርን ከተማ አንድ የአፍጋኒስታን ተወላጅ ሆን ብሎ በመኪና ባደረሰው አደጋ 19 ያህል ሰዎች መቁሰላቸው ታወቀ። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰአት ከደጋው ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ባይኖሩም በአደጋው ከቆሰሉት ሰዎች ግን አራቱ ሕይወታቸው አስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ታውቋል። በሜልቦርን ማዕከላዊ የንግድ ክፍለ ከተማ ለገና ገበያ ወዲያ ወዲህ ሲሉ የነበሩ ሰዎችን በሚያሽከረክረው ሱዙኪ ኤስ ዩ ቪ ተሽከርካሪ የገጨው የ32 ...
Read More »የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እያስገባ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) በኢትዮጵያ ሕዝባዊ ተቃውሞ የከፋ ደረጃ ይደርሳል በሚል የሕወሃት አገዛዝ ከፍተኛ የእህል ክምችት ወደ ትግራይ እንዲገባ እያደረገ መሆኑ ተነገረ። መጪው ጊዜ ያስፈራው የህወሃት መንግስት ቀደም ሲልም ግዙፍ የእህል ጎተራ በማስገንባት እህል ሲያከማች መቆየቱ ይታወሳል። አሁን ደግሞ ተጨማሪ እህል ከአማራ አካባቢና ሌሎች የኢትዮጵያ አምራች አካባቢዎች ከአርሶ አደሩ በርካሽ ዋጋ እየገዛ ወደ ትግራይ እያጓጎዘ መሆኑ ታውቋል። የትግራይ ክልል ብዙ እህል ...
Read More »የብአዴን አመራር አባላት የአማራ ሕዝብ ሆድ ብሶታል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የአዲስ አበባ ወረዳዎች የብአዴን አመራር አባላት የአማራ ሕዝብ ሆድ ብሶታል በሕወሃት አገዛዝም ከፍተኛ በደል እየደረሰበት ነው ሲሉ አማረሩ። የብአዴን ካድሬዎች ያካሄዱት የጥልቅ ተሃድሶ የግምገማ ቃለጉባኤ ኢሳት እጅ ገብቷል። ካድሬዎቹ የሕወሃት የበላይነት ስለመኖሩም ማረጋገጫ በማቅረብ መግባባት ላይ ደርሰዋል። የአዲስ አበባ ብአዴን ካድሬዎች ባካሄዱት ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ በየወረዳዎቻቸው የሚገኙ የሕወሃት አመራሮች ቁልፍ ቦታዎችን እንደተቆጣጠሩ ይፋ አድርገዋል። የሕወሃት የበላይነት በየተቋማቱ ...
Read More »የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ አወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ከሳምንት በፊት የጀመረው ስብሰባ አለመጠናቀቁን በማስመልከት ግንባሩ መግለጫ አወጣ። በአባል ድርጅቶች ውስጥ አለመተማመንና መጠራጠር እንደነበርም መግለጫው ዘርዝሯል። አዘቅት ውስጥም ገብተናል ሲልም ያክላል። በአጠቃላይ ጉዳይ የተጀመረውና የቀድሞ አመራሮችን ያሳተፈው ግምገማ አሁንም መቀጠሉን በፓርቲና በመንግስት መገናኛ ብዙሃን የተለቀቀው የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ መግለጫ ያስረዳል። “እስካሁን በተደረገው ጥልቅ ግምገማ ከስኬት ጎዳና እያራቁን የሚገኙት የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ...
Read More »የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ሁኔታ አሳስቦኛል አለ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 12/2010) የአውሮፓ ህብረት የኢትዮጵያ ሁኔታ ስጋት ውስጥ እንደከተተው አስታወቀ። ትላንት በህብረቱ ቃል አቀባይ የተላለፈው መልዕክት ላይ እንደተገለጸው የአውሮፓ ሀገራት ህብረት በኢትዮጵያ ያለው ብሄርን መሰረት ያደረገው አለመረጋጋት አሳሳቢ ሆኖበታል። በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎችና በዩኒቨርስቲዎች የሚታየው የሰላም መደፍረስ ስጋት ውስጥ እንደከተተው ህብረቱ ትላንት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። በተለይም በሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች መሀል የተፈጠረው ግጭት የማያባራ ሆኖ መቀጠል በከፍተኛ ሁኔታ አሳስቦኛል ብሏል የአውሮፓ ...
Read More »በኦሮሚያ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ታሕሳስ 12/2010) በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ ከተሞች ተቃውሞ ሲደረግ መዋሉ ታወቀ። በሀረርጌ የአጋዚ ወታደሮች መገደላቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በመቱ ለአራተኛ ቀን ተቃውሞው የቀጠለ ሲሆን በጂማና በቄሌም ወለጋም ተመሳሳይ የተቃውሞ ትዕይንት መደረጉን ለማወቅ ተችሏል። በወለጋ በአንዳንድ ቦታዎች ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላትና ደጋፊዎች የትምህርት አገልግሎትን ጨምሮ ብድርና እርዳታ እንደተከለከሉ ተገልጿል። ህዝባዊ ተቃውሞና ግድያ ተለይቶት በማያውቀው ሀረርጌ ዛሬም ጠንከር ያለ ...
Read More »የኦሕዴድና ብአዴን የፓርላማ አባላት ስብሰባ አንሳተፍም አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 11/2010) በኢትዮጵያ ፓርላማ የኦሕዴድና ብአዴን አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በምክር ቤት ተገኝተው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ካልሰጧቸው በመደበኛ ስብሰባዎች አንሳተፍም አሉ። የኦሕዴድና የብአዴን የሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ሀገሪቱን ስጋት ላይ በጣላት ብሄር ተኮር ግጭትና የፖለቲካ ቀውስ ላይ አቶ ሃይለማርያም ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ አቅርበዋል። አባላቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በተወከሉባቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ውይይት ካካሄዱ በኋላ ነው። በኢትዮጵያ ያለው ...
Read More »