.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ መግለጫ ሕዝብን ለማታለል ያለመ ነው ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 23/2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ያወጣው መግለጫ ሕዝብን ለማታለል ያለመና ከዚህ ቀደም ካወጣቸው መግለጫዎች የተለየ አለመሆኑን አስተያየታቸውን ለኢሳት የሰጡ ምሁራንና ፖለቲከኞች ገለጹ። በኢትዮጵያ ለተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ የኢሕአዴግ አመራር ሙሉ ሃላፊነትን እወስዳለሁ ሲል በመግለጫው ማስፈሩ ከቃላት ጋጋታ ያልዘለለ ነው ሲሉም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እናም ሕዝቡ የጀመረውን ትግል አጠናክሮ በመቀጠል ለነጻነት የተጀመረውን ጉዞ ማፋጠን ያስፈልጋል ብለዋል። የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ኦፌኮ/ስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ...

Read More »

የፈረንጆቹ 2017 ሊጠናቀቅ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010) የፈረንጆቹ 2017 እሁድ ይጠናቀቃል። እንደ ሌሎቹ አመታት ሁሉ 2017 ታላላቅ ክንዋኔዎችን አስተናግዷል። አመቱ የፖለቲካ፣የኢኮኖሚ፣የሽብር፣የተፈጥሮ አደጋ፣የኒዩክለር ፍጥጫ።አሰቃቂ ጦርነቶችና ሌሎችም ክስተቶች ተከናውነውበታል። አሮጌ አመት ባለፈ ቁጥር እንዲህ አይነት ለየት ያለ አመት እስካሁን አልነበረም ማለት የተለመደ ነው። የተጠናቀቀው የፈረንጆቹ አመትም በርካታ መጥፎና ጥሩ ክንውኖችን በማስተናገዱ ለየት ያለ አመት ሆኖ አልፏል የሚሉ በርካቶች ናቸው። ከአፍሪካ ብንጀምር በዚምባቡዌ ሮበርት ሙጋቤ ከ37 አመታት ...

Read More »

የዶክተር መረራ የክስ መዝገብ ሌላ ማስረጃ ቀረበበት

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010) ብይን ይሰጥበታል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የዶክተር መረራ ጉዲና የክስ መዝገብ ሌላ የቪዲዮ፣ የድምጽና የምስል ማስረጃ በአቃቢ ሕግ እንደቀረበበት ተሰማ። ዐቃቢ ህግ ማስረጃውን ያቀረበው በዶክተር መረራ ላይ የማቀርበውን ማስረጃ ጨርሻለሁ ካለ በኋላ ነው። ዶ/ር መረራም የቀረበው ማስረጃ የመንግስት ባለስልጣናት ይቅርታ የጠየቁብት ነው ሲሉ ተከራከረዋል። ከአንድ አመት በለይ በእስር ላይ የሚገኙት ዶክተር መረራ ጉዲና ዛሬ ለውሳኔ ተቀጥረው ነበር ። ...

Read More »

ሕወሃት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ አይቀርም ተባለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010) በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በሕገ መንግስቱ መሰረት የአስቸኳይ ጊዜ ምርጫ ለማካሄድ የሚገደድበት ሁኔታ መፈጠሩ እንደማይቀር የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ተናገሩ። ዶክተር ነጋሶ እንዳሉት ኢሕአዴግ እንደ ፓርቲ የመቀጠልና ሀገር የማስተዳደር ሕልሙ በማክተም ላይ ነው። የኢትዮጵያ የቀድሞው ፕሬዝዳንት ዶክተር ነጋሶ ጊዳዳ ወቅታዊውን የሀገሪቱን የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ አስተያየታቸውን ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ገልጸዋል። እናም ዶክተር ነጋሶ እንደሚሉት ሕዝብ ላነሳቸው ጥያቄዎች ተገቢው ...

Read More »

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመረው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010) በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተጀመረው ተቃውሞ አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች መቀጠሉ ታወቀ። የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የትምህርት ማቆም አድማ ሲመቱ የአዳማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ደግሞ በግድ እንዲማሩ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል። ተቃውሞ አቅርበዋል የተባሉ 50 ተማሪዎች ተይዘው መታሰራቸውንም ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል። በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ አባያ በተባለው ካምፓስ ውስጥ የተበተነውን የተቃውሞ ወረቀት ተከትሎ የቀጠለው አድማ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። በሳምንቱ ...

Read More »

በኦሮሚያ የተለያዩ አካባቢዎች ተቃውሞ ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 20/2010) በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል አካባቢዎች ዛሬ ተቃውሞ መደረጉ ታወቀ። በምስራቅና በምዕራብ ወለጋ በበርካታ ከተሞች በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የአገዛዙ ሃይሎችና ነዋሪው መጋጨታቸውን ለማወቅ ተችሏል። በባኮና አደአ በርጋ ህዝባዊ ተቃውሞ መቀስቀሱም ተሰምቷል። በወለጋ ሻምቡ በአጋዚ ሃይል ሁለት ሰዎች ተገድለዋል። በሌላ በኩል በሀረር መስመር ጭሮ ከተማ አቅራቢያ አራት የሰላም ባስ አውቶብሶች መሰባበራቸውን ተከትሎ በአካባቢው ውጥረት መንገሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። ከሀረር አዲስ አበባ መስመር ...

Read More »

8 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) ሕጻናትን ጨምሮ 8 የደቡብ ሱዳን ስደተኞች በኢትዮጵያ መጠለያ ካምፕ ጋምቤላ ውስጥ መገደላቸው ተሰማ። ሬዲዮ ታማዙጅ የተባለ ጣቢያ ከሱዳን እንደዘገበው ሴቶችና ሕጻናትን ጨምሮ የሙርሌ ጎሳ አባላት የሆኑ ሱዳናውያን ዲማ የስደተኞች ካምፕ ውስጥ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። የካምፑ የስራ ሃላፊ አንድሪው ካካ እንዳረጋገጡትም ከትላንት በስትያ ታህሳስ 17 ለሊት ላይ በስደተኞች መጠለያ ውስጥ ተኩስ ተከፍቶ 8ቱ ሰዎች ተገድለዋል። ከስምንቱ የሙርሊ ...

Read More »

የሀውቲ አማጽያን ላይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 68 ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) በሳውዲ የሚመራው ጥምር ጦር በየመን የሀውቲ አማጽያን ላይ በፈጸመው የአየር ጥቃት ቢያንስ 68 ሰላማዊ ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ መገደላቸው ታወቀ። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጎ አድራጎት አስተባባሪ እንደሚሉት ማክሰኞ ዕለት በተከታታይ በተፈጸመው የአየር ጥቃት በአንድ የገበያ ቦታ ላይ በተፈጸመው የመጀመሪያ ጥቃት 54 ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ በሁለተኛው ጥቃት ደግሞ 14 ሰዎች መገደላቸው ታውቋል። የተባበሩት መንግስታት የበጎ አድራጎት ማስተባበሪያ ሃላፊ ...

Read More »

ቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ስራዎቹን አስመራ ላይ ማቅረብ እፈልጋለሁ አለ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) ድምጻዊ ቴድሮስ ካሳሁን በኤርትራ መዲና አስመራ የሙዚቃ ስራዎቹን ማቅረብ እንደሚፈልግ ገለጸ። ለፈረንሳዩ የዜና ወኪል ኤ ኤፍ ፒ ቃለመጠይቅ የሰጠው ቴዲ አፍሮ በአስመራ የሙዚቃ ኮንሰርት በማቅረብ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማሻሻል እንደሚፈልግ አስታውቋል። በሌላ በኩል ለመጪው የኢትዮጵያ የገና በዓል በአዲስ አበባ የሙዚቃ ዝግጅት ለማቅረብ የአገዛዙን ፈቃድ በመጠበቅ ላይ መሆኑንም ኤ ኤፍ ፒ በዘገባው አመልክቷል። አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ...

Read More »

የማላዊ ባለስልጣናት ስምምነቱን አጣጣሉ

(ኢሳት ዲሲ–ታህሳስ 19/2010) በኢትዮጵያ አየር መንገድና በማላዊ አየር መንገድ መካከል የተፈጸመው የንግድ ሽርክና እርባና የሌለውና የማይጠቅም ሲሉ የሀገሪቱ መንግስት ባለስልጣናት ስምምነቱን አጣጣሉ። የማላዊ መንግስት ባለስልጣናትና የሀገሪቱ የፓርላማ አባላት ሁለቱ አየር መንገዶች የሽርክና ስምምነት ከመረመሩ በኋላ ጉዳዩ አዋጭ እንዳልሆነ ደርሰንበታል ብለዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከማላዊ አቻው ጋር ባካሄደው የንግድ ሽርክና ስምምነት 49 በመቶ ድርሻ በመያዝ የትርፍ ተከፋይ ለመሆን ነው። የ51 በመቶ ...

Read More »