(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ከከፍተኛ ማንገራገር በኋላ ስልጣናቸውን ለቀቁ። በምትካቸውም ሲሪል ራምፖሳ የደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት በመሆን ተመርጠዋል። በሌላም በኩል ታዋቂው የዚምባቡዌ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪና የቀድሞው ፓርቲ መሪና የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ሞርጋን ቻንግራይ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል። የሙስና ወንጀሎችን ጨምሮ የተለያዩ ክሶች የቀረቡባቸው የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ ፓርቲያቸው የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ በሳምንቱ መጀመሪያ ስልጣናቸውን እንዲለቁ የሰጣቸውን ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የትግራይን መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ
የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት የትግራይን መንግስት ይቅርታ እንዲጠይቅ የቀረበው ጥያቄ ውድቅ ሆነ (ኢሳት ዜና የካቲት 8 ቀን 2010ዓ/ም) በሰሞኑ ብአዴን እያደረገ ባለው ዝግ ስብሰባ ላይ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት በሰራቸው ዜናዎችና ፕሮግራሞች የተከፉትን የህውሃት አመራሮች ለማስደሰት በማሰብ ፣ አቶ አለምነው መኮንን “ጋዜጠኞች ጥፋተኞች እንደሆኑ በማመን የትግራይን መንግስት ይቅርታ መጠየቅ አለብን” በማለት የእርሱን ደጋፊዎች በመያዝ ለሶስት ቀናት ሲከራከር ቢቆይም፣ በአቶ ገዱ ...
Read More »አቶ መላኩ ገላው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) የክራርና የዋሽንት ሊቅ በሚል የሚታወቁትና የያሬድ ሙዚቃ ትምህርት ቤት መምህር የነበሩት አቶ መላኩ ገላው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ። በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ሕይወታቸው ያለፈው የአቶ መላኩ ገላው አስከሬን ዛሬ ወደ ትውልድ ሀገራቸው ኢትዮጵያ ተልኳል። ከአባታቸው ከአቶ ገላው ወልደተክሌና ከእናታቸው እማሆይ ትኩነሽ ተሰማ መጋቢት 12/1931 የተወለዱት አቶ መላኩ ገላው ከ1956 ጀምሮ በኢትዮጵያ የባህላዊ መሳሪያዎች በተለይም በክራርና ዋሽንት ተጫዋችነት ሲያገለግሉ ...
Read More »የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ በጭቅጭቅና በንትርክ እየተካሄደ ነው
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ከ3 በተከፈለ ቡድን በጭቅጭቅና በንትርክ እየተካሄደ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ስብሰባው በዘለፋና በስድብ ታጅቦ በወልቃይት ኮሚቴ አባላት አያያዝ፥ በመከላከያና ደህንነት ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በሕወሃት የበላይነት ጉዳይ ላይ ክርክር ተደርጎ አሁን ባለው ሁኔታ ወደ ግለ ሂስ ተገብቷል። በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው የሚመራው ቡድን ችግራችን ውጫዊና በክልላችን የሚደረግ ጣልቃገብነት ነው እያለ ነው። በእነ አቶ አለምነው የሚመራው ...
Read More »የአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሀውልት ፈረሰ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) በአጋሮ ከተማ መሀል አደባባይ የቆመው የአቶ መለስ ዜናዊ መታሰቢያ ሀውልት ፈረሰ። የከተማዋ ቄሮ በወሰደው ርምጃ ሀውልቱ ከቆመበት እንዲወገድ መደረጉ ታውቋል። በተለያዩ የኦሮሚያ ክልል ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞው ቀጥሏል። በአርሲ ኢተያ በሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል የሃይማኖት ግጭት ለመቀስቀስ ሙከራ እየተደረገ ነው። በጅማ አመጽ የተቀላቀለበት ተቃውሞ በመካሄድ ላይ ነው። በሸዋ ሮቢት የአጋዚ ወታደሮች ግድያ መፈጸማቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መሃል አጋሮ ከተማ ...
Read More »የስራ ማቆም አድማው ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተቀየረ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ የስራ ማቆም አድማው ወደ አደባባይ ተቃውሞ ተቀየረ። የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ጥቃት ደርሶባቸዋል። የግብር መሰብሰቢያ መስሪያ ቤት ህንጻ በእሳት ተቃጥሎ፣ ሰነዶች መውደማቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ቢያንስ የአንድ ሰው ህይወት መጥፋቱ እየተነገረ ነው። ከጦላይ የጦር ማሰልጠኛ ካምፕ የመከላከያ ሰራዊት ወልቂጤ መግባቱንም ለማወቅ ተችሏል። በከተማዋ ህዝባዊ አመጹ ተጠናክሮ መቀጠሉን ዘግይተው የሚወጡ መረጃዎችም አመልክተዋል። የተጠራቀመ ብሶት አደባባይ ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም የስልጣን መልቀቂያ አቀረቡ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 8/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ የስልጣን መልቀቂያ ማቅረባቸውን ገለጹ። አቶ ሃይለማርያም በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ቀርበው ስልጣን ለመልቀቅ የወሰኑት ለሃገር መረጋጋትና ለሰላማዊ የስልጣን ሽግግር መሆኑን ገልጸዋል። ጥያቄያቸው አባልና ሊቀመንበር በሆኑበት ድርጅት በደኢህዴንና በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ተቀባይነት አግኝቷልም ብለዋል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ መልቀቂያ ተግባራዊ የሚሆነው ግን በኢሕአዴግ ምክር ቤትና በፓርላማው ሲጸድቅ ይሆናል። ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ በመግለጫቸው እንዳሉት ኢትዮጵያ በአስከፊ ሁኔታ ...
Read More »ጃኮብ ዙማ ስልጣን አለቅም አሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝዳንት ጃኮብ ዙማ የፈጸምኩት ምንም ጥፋት ስለሌለ ከስልጣን የምወርድበት ምክንያት የለም ሲሉ ለፓርቲያቸውም ምላሽ መስጠታቸው ታወቀ። የደቡብ አፍሪካው ገዢ ፓርቲ የአፍሪካ ብሔራዊ ኮንግረስ ጃኮብ ዙማ በሙስናና በልዩ ልዩ ተደራራቢ የወንጀል ክሶች ተጠያቂ በመሆናቸው ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው እንዲለቁ ግፊት ሲያደርግ ቆይቷል። ነገር ግን ፕሬዝዳንቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ ስልጣን እንደማይለቁ አረጋግጠዋል። ፓርቲያቸው እያቀረበላቸው ያለው ጥያቄም ቢሆን ትክክል ያለሆነና ...
Read More »ቶኒ ብሌር በዱከም ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት ተሰረዘ
(ኢሳት ዲሲ–ጥር 7/2010) የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌር በዱከም ሊያደርጉት የነበረው ጉብኝት መሰረዙ ታወቀ። ለቶኒ ብሌር ጉብኝት መሰረዝ ምክንያቱ በኦሮሚያ ክልል የተነሳው ህዝባዊ እምቢተኝነት መሆኑ ታውቋል። ህዝባዊ እምቢተኝነቱና የስራ ማቆም አድማው ለሶስተኛ ቀን ተጠናክሮ ቀጥሏል። በኦሮሚያ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ወደ ተለያዩ አካባቢዎችም መዛመቱ ታውቋል። ይህንን ተከትሎም የቀድሞ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስቴር ቶኒ ብሌር በዱከም የነበራቸው ጉብኝት ተሰርዟል። ቶኒ ቢሊየር ወደ ዱከም ...
Read More »የተጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ለ3ኛ ቀን ቀጠለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 7/2010) በኦሮሚያ ክልል የተጀመረው አድማና የተቃውሞ ሰልፍ ለ3ኛ ቀን መቀጠሉ ታውቋል። በወሊሶ፣ ነቀምት፣ አዳማ፣ አወዳይ፣ አዲስ አበባ ዙሪያና ሌሎች በርካታ አከባቢዎች በሶስተኛው ቀን ተቃውሞ ተሳታፊ ሆነዋል። በወሊሶ ዛሬ በተካሄደው ትዕይንተ ህዝብ በስልጣን ላይ ያለው የትግራይ ነጻ አውጪ ግንባር ሕወሃት መንግስት ላይ ተቃውሞ ተሰምቷል። ዛሬም በወሊሶ ሱቆችና መደብሮች እንደተዘጉ ነው። በነቀምት ወለጋ በሶስተኛ ቀን የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሕዝቡ አደባባይ በመውጣት ...
Read More »