የወጣቶችን ፈንድ በአስቸኳይ ለማከፋፈል እንቅስቃሴ ተጀመረ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)በአገሪቱ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ ለወጣቶች የስራ እድል በመፍጠር ተቃውሞውን ሊቀንስ ይችላል በሚል የተመደበው የወጣቶች የስራ ማስያዣ በጀት በአፋጣኝ ጥቅም ላይ እንዲውል ትዕዛዝ በመተላለፉ ሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደሮችና ክልሎች ወከባ ውስጥ መውደቃቸው ታውቋል። ገንዘቡ ከተመደ በሁዋላ የባለስልጣናት ቤተሰቦችን ኪስ ከማደለብ ውጭ የፈየደው ነገር እንዳልነበር የሚገልጹት ምንጮች፣ በአዲስ አበባ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
የሞዛንቢክ ፖሊስ ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታወቀ
የሞዛንቢክ ፖሊስ ሕገወጥ ናቸው ያላቸውን 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን አስታወቀ (ኢሳት ዜና የካቲት 22 ቀን 2010 ዓ/ም)ከሞዛንቢክ ዋና ከተማ ማፑቶ በ80 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ከሚገኘው ማኒካ አውራጃ አቆራርጠው በሕገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊገቡ የሞከሩ 23 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአገሪቱ ፖሊስ ገልጿል። የስደተኞች ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጆርጌ ማቻቫ ”ኢትዮጵያዊያኑን ስደተኞች በተኙበት ይዘናቸዋል። በአሁኑ ወቅትም በቫንዱዚ ፖሊስ ...
Read More »የጎንደር አካባቢ ህዝብ ደስታውን ሲገልጽ ዋለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ትላንት የአርበኛ ጎቤ መልኬን አንደኛ ሙት ዓመት መታሰቢያና የወልቃይት የአማራ ማንነት ኮሚቴ አባላትን ከእስር መለቀቅ ምክንያት በማድረግ በቆላማው የጎንደር አካባቢ ህዝቡ ደስታውን ሲገልጽ መዋሉ ታወቀ። በተኮስ እሩምታና በመኪናጥሩምባ የታጀበው የደስታ መግለጫ ትዕይንት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የጣሰ የህዝብ እርምጃ እንደሆነ ም ታውቋል። አርበኛ ጎቤ መልኬ ከጎንደሩ ህዝባዊ እምቢተኝነት በኋላ ስማቸው ጎልቶ የወጣ ይሁን እንጂ በፊትም በልጅ አዋቂው ዘንድ ...
Read More »በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ (ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) አሁን ከገጠመን አደገኛ አዙሪት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ሀገሩን የሚወድ ዜጋ ሁሉ በአንድነት መታገል አለበት ሲል በስደት የሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስተያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪ አቀረበ። የአስቸኳይ ግዜ አዋጁ እንዲነሳ እና የሽግግር መንግስት እንዲመሰረትም ጥሪ አቅርቧል። በስደት የሚገኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ብሄራዊ መረጋጋትና የሰላም ጥሪ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ በማለት ባወጣው ...
Read More »ጃሬድ ኩሽነር የደህንነት ምርመራን ለማልፍ አለመቻላቸው ተነገረ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) የአሜሪካው ፕሬዝዳንት የቅርብ አማካሪና የልጃቸው ባለቤት ጃሬድ ኩሽነር በኋይት ሃውስ ከፍተኛ ሰነዶችን ለማየት የሚያስችለውን የደህንነት ምርመራን ለማልፍ አለመቻላቸው ተነገረ። ፕሬዝደንት ትራምፕ ከተመረጡ ግዜ አንስቶ ከፍተኛ አማካሪያቸው አድርገው የሾሟቸው ጃሬድ ኩሽነር በጊዜያዊ የደህንነት ፈቃድ አማካሪ ሆነው ቆይተዋል። እንደ ሲ ኤን ኤን ዘገባ ከሆነ ኩሽነር ከዚህ በኋላ በቋሚነት ከፍተኛ ሰነዶችን ለማየት የሚያስችላቸው ፈቃድ ከአሜሪካ የደህንነት መስሪያ ቤት ማግኘት አይችሉም። ...
Read More »በጋምቤላ የባጃጅ አገልግሎት ተቋረጠ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ጋምቤላ ከተማ የባጃጅ ታክሲ አገልግሎት መቋረጡ ተገለጸ። ከፍተኛ ግብር ተጭኖብናል ያሉት የታክሲ አሽከርካሪዎቹ ከዛሬ ጀምሮ ስራ ማቆማቸውን ነው ሪፖርተር ጋዜጣ የዘገበው። እነዚህ ለጋምቤላ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡት ባጃጆች ዛሬ ረቡዕ ከጠዋት ጀምሮ አገልግሎት ማቆማቸው የተገለጸ ሲሆን በዚህም የተነሳ ነዋሪዎች ትራንስፖርት መቸገራቸው ታውቋል። የታክሲ አገልግሎት የሚሰጡት የባጃጅ ሾፌሮቹ የተጣለብን ግብር ከአቅማችን በላይ በመሆኑ መክፈል አንችልም ማለታቸው ተጠቅሷል። በጉዳዩ ...
Read More »ሁሉም የኢህአዴግ ምክርቤት አባላት ለግንባሩ ሊቀመንበርነት መወዳደር ይችላሉ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21/2010) ሁሉም የኢህአዴግ ምክርቤት አባላት ለግንባሩ ሊቀመንበርነት መወዳደር እንደሚችሉ አቶ በረከት ስምኦን ገለፁ ሰሞኑን በማህበራዊ ድረ ገፅ የተለቀቀው ፅሁፍ ” የእኔ አይደለም” ሲሉም አስተባብለዋል። ህውሓት/ ኢህአዴግ አጣብቂኝ ውስጥ በገባ ቁጥር ወደ ሚዲያ በመምጣት መግለጫ በመስጠት ይታወቃሉ አቶ በረከት ስምኦን። የብአዴን ነባር አባልና በተለያዩ የድርጅት እና የመንግስት ስልጣናት ላይ በመመደብ ህውሓትን በታማኝነት ያገለገሉ ናቸው። በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ በውሸትና የተሳሳተ ...
Read More »በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ ተጠናክሮ ቀጥሏል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 21 2010) የአስቸኳይ ገዜ አዋጁን እንዲያጸድቁ በፓርላማ አባላት ላይ የሚደረገው ማስፈራሪያ ተጠናክሮ መቀጠሉ ታውቀ። ከኦህዴድ አባላት በተጨማሪ በብአዴን እና ደኢህዴን አባላት ላይ ጭምር በተጠናከረው በዚሁ የማስፈራራት ርምጃ በዋናነት የሚሳተፉት ከመከላከያ ሚኒስቴር የተላኩ ጄኔራሎች እና የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውን ለኢሳት የደረሰው መራጃ ያመለክታል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ደኢህዴን በአቶ ሃይለማርያም ምትክ ሊቀመንበር የመረጠውና በኋላም የቀየረው በሕወሃት መሪዎች ትዕዛዝ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ...
Read More »ህወሃት የዶ/ር አብይ አህመድን መመረጥ አጥብቆ እየተቃወመ ነው
ህወሃት የዶ/ር አብይ አህመድን መመረጥ አጥብቆ እየተቃወመ ነው (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝን ለመተካት ኦህዴድ በእጩነት ለማቅረብ ያዘጋጃቸው ዶ/ር አብይ እንዳይመረጡ፣ ህወሃት ጠንካራ ቅስቀሳ በማድረግ ላይ ነው። የደረሱን ተጨባጭ መረጃዎች እንደሚያመለክቲት፣ህወሃቶች ዶ/ር አብይን “ትግሬን ይጠላል” የሚል ቅስቀሳ ከፍተውባቸዋል። የኦሮምያ ክልል መሪ አቶ ለማ መገርሳ ከኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ላይ ዶ/ር አብይ የድርጅቱ ...
Read More »በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ
በደሴ የመጓጓዣ ዋጋ ተመን በእጥፍ ጭማሪ እንደተደረገበት ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና የካቲት 21 ቀን 2010 ዓ/ም) በደሴ ከተማና በዙሪያዋ በሚገኙ የታክሲና የአውቶቡስ መጓጓዣ ላይ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል።መረጃዎች እንዳሳዩት፣ በተለይ በከተማዋ የታክሲ ዋጋ ላይ ሃምሳ በመቶ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል። ‘’በዓለም ላይ የነዳጅ ዋጋ እየቀነሰ ባለበትና ምንም ዓይነት የዋጋ ጭማሪ ሳይኖር ለምን የዋጋ ጭማሪው ማድረግ አስፈለገ?’’ ሲሉ ነዋሪዎቹ ቢጠይቁም፣ ምላሽ የሚሰጣቸው አካል ...
Read More »