.የኢሳት አማርኛ ዜና

የሕወሃት አገዛዝ የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እርዳታ ጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010) በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ ለእለት የአስቸኳይ የምግብ እርዳታ የ1 ነጥብ 6 ቢሊየን ዶላር እርዳታ መጠየቁ ተነገረ። እርዳታው የተጠየቀው 8 ሚሊየን ለሚጠጉ የድርቅ ተጎጂዎች ድጋፍ መሆኑን የተባበሩት መንግስታት አስታውቋል። በግጭትና በድርቅ ከተጎዱ ኢትዮጵያውያን መካከል 2 ነጥብ 4 ሚሊየን የሚሆኑት አርብቶ አደሮች ናቸው ተብሏል። በኢትዮጵያ ባለፉት 3 አመታት ከተፈጠረው ፖለቲካዊ ቀውስ ባሻገር በድርቅ ሳቢያ የተጠቁት 8 ሚሊየን ያህል ናቸው። ፖለቲካዊ ...

Read More »

ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት ተከሰተ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)በኢትዮጵያ በውጭ ምንዛሪ እጥረት ሳቢያ ከፍተኛ የመድሃኒት እጥረት በመከሰቱ ሕሙማን ሕይወታቸው በአስጊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ። አቅራቢዎችም ሆነ የጤና ተቋማት በመድሃኒት እጥረት ምክንያት አገልግሎት ለመስጠት መቸገራቸውን አስታውቀዋል። በተለይም የስኳርና የልብ ሕሙማን ሕይወታቸው አደገኛ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝም ተገልጿል። በኢትዮጵያ ከ330 በላይ መድሃኒት አስመጪዎች ቢገኙም በውጭ ምንዛሪ መታጣት ምክንያት ስራቸውን በአግባቡ እየሰሩ አይደሉም። በዚሁም ሳቢያ የመንግስትም ሆነ የግል መድሃኒት ቤቶች ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋረጠ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13/2010)በኦሮሚያ ክልል የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጡን የክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘገበ። የኢንተርኔት አገልግሎት መቋረጥ በዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም በራሱ በኦሮሚያ ክልል መገናኛ ብዙሃን ላይ ተጽእኖ ማድረጉም ተመልክቷል። ኢንተርኔት ፍለጋ ከአዳማ አዲስ አበባ የሚመላለሱ ግለሰቦችም ቅሬታቸውን ገልጸዋል። የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተከትሎ ከፍተኛ የሰራዊት ሃይል የተሰማራበት የኦሮሚያ ክልል ከሌሎች ክልሎች በተለየ የኢንተርኔት አገልግሎት የተቋረጠበት ምክንያት አልታወቀም። የኦሮሚያ ክልል ቴሌቪዥን ጣቢያ ኦ ቢ ኤን እንደዘገበውም ...

Read More »

የአስቸኳይ ግዜ አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከፓርላማ እንዲባረሩ ተጠየቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 13 /2010) የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴን ስብሰባ ተከትሎ ማክሰኞ በተጀመረው  የኢሕአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የአስቸኳይ ግዜ  አዋጁን የተቃወሙ የኦህዴድ ተመራጮች ከአባልነት እንዲሁም ከፓርላማ እንዲባረሩ ህወሓት ጠየቀ። በስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው ከተወሰነው ውጭ  የቀረበው ይህ አጀንዳ ተቃውሞ ገጥሞታል። የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ አመራር አባላት በተጨማሪም በአቶ ለማ መገርሳ እና በዶ/ር አብይ አህመድ ላይ የተለያዩ ክሶች ማቅረባቸውም ተሰምቷል። እነርሱም ጠንካራ ምላሽ ...

Read More »

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው።

በሶማሌ ክልል ከሚገኙ 16 የጉምሩክ ጣቢያዎች 38 ሃላፊዎች ስራ እንዲያቆሙ ታዘዙ 34 ቱ የትግራይ ብሄር ተወላጅና የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው ናቸው። (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮች እንደገለጹት እነዚህ የኮሎኔልነት ማዕረግ ያላቸው አዛዦች ከመከላከያ በጡረታ ከተገለሉ በሁዋላ ያለ ትምህርት ደረጃቸው በትዕዛዝ ብቻ በመላ አገሪቱ ባሉ የጉሙሩክ መስሪያ ቤቶች ተቀጥረው ላለፉት 8 ዓመታት ከፍተኛ የሆነ ገንዘብ ሲመዘብሩ ቆይተዋል። ዛሬ የትምህርት ...

Read More »

በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ

በሰሜን ወሎ ሮቢት ከተማ ላይ አንድ አውቶቡስ በድንጋይ ተመታ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት እንደገለጹት ዛሬ ጠዋት ከአዲስ አበባ የተነሳ ስካይ ባስ በሚል የሚጠራ የመንገደኞች ማመላለሻ አውቶቢስ ሮቢት ከተማ ላይ በድንጋይ ተመትቶ የሚከናው መስታውት መሰባባሩን ገልጸዋል። ወጣቶቹ ያደረሱትን ጥቃት ተከትሎ በተሳፋሪዎች ላይ ጉዳት ይድረስ አይድረስ የታወቀ ነገር የለም። ጥቃቱ እንደተሰነዘረ ከቆቦ የተነሱ ወታደሮች ወዲያውኑ አካባቢውን ...

Read More »

ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ

ወጣት አወቀ አባተ ለቀናት በገመድ ተንጠልጥሎ ሲገረፍ መቆየቱን ተናገረ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የመኢአድ የአዲስ አበባ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ የነበረው ወጣት አወቀ አባተ፣ በጎንደር ሲካሄድ የነበረውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ትመራለህ ተብሎ በ2008 ዓም ከተያዘ በሁዋላ፣ ያልሰጠውን ቃል እንደሰጠ ተደርጎ እንዲፈርም ለማስገደድ ለ4 ቀናት ያክል እጆቹና እግሮቹ ታስረው ሲደበደብ መቆየቱን ተናግሯል። በድብደባው ብዛት በጥፍሮቹ ደም ይፈሰው እንደነበር ...

Read More »

ተመድ 10 ሺ ለሚሆኑ ከሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ

ተመድ 10 ሺ ለሚሆኑ ከሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) ራሱን ኮማንድ ፖስት በሚል የሚጠራው ወታደራዊ እዝ በበኩሉ ተፈናቃዮች እየተመለሱ ነው ብሎአል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽነር ከኬንያ ባወጣው መረጃ ከኢትዮጵያዋ የሞያሌ ከተማ ለተፈናቀሉ 10 ሺ ለሚሆኑ ዜጎች ዛሬ የቤትና የምግብ ማብሰያ እቃዎችን ሲያድል መዋሉን ገልጿል። ወታደራዊ እዙ ባወጣው መግለጫ ደግሞ ...

Read More »

የኢህአዴግ ካድሬዎች ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየለመኑ ቢሆንም ወጣቶቹ ግን “ መሸንገያ ነው” በማለት አልተቀበሉትም

የኢህአዴግ ካድሬዎች ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየለመኑ ቢሆንም ወጣቶቹ ግን “ መሸንገያ ነው” በማለት አልተቀበሉትም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በአገሪቱ የሚካሄደውን ህዝባዊ የለውጥ እንቅስቃሴ ተከትሎ የወጣቱን ቁጣ ያበርዳል በሚል ወጣቶች ብድር እንዲወስዱ እየተጠየቁ ነው። ከአዲስ አበባ ውጭ በሚገኙ ከተሞች፣ የኢህአዴግ ካድሬዎች ቤት ለቤት እየሄዱ ወጣቶችን ብድር ውሰዱ እያሉ በመለመን ላይ ናቸው። ወጣቶች እንደሚሉት ባልተዘጋጁበትና በገንዘቡ ምን እንደሚሰሩ በውል ...

Read More »

ካለ ምንም ፍርድ አንድ ዓመት ከአንድ ወር በእስራት የቆዩት አቶ ብስራት አቢ አሁንም አልተፈቱም

ካለ ምንም ፍርድ አንድ ዓመት ከአንድ ወር በእስራት የቆዩት አቶ ብስራት አቢ አሁንም አልተፈቱም (ኢሳት ዜና ማጋቢት 12 ቀን 2010 ዓ/ም) በሰማያዊ ፓርቲ የማእከላዊ ኮሚቴ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ የሆኑት አቶ ብስራት አቢ ከአዲስ አበባ ለሥራ ጉዳይ ወደ ደሴ ከተማ በሄዱበት ታፍነው ከተወሰዱ አንድ ዓመት ከአንድ ወር ሞልቷቸዋል። እስካሁንም ምንም ዓይነት የፍርድ ብያኔ አላገኙም። አቶ ብስራት ታፍነው ከተወሰዱ ከሁለት ወራት በኋላ ...

Read More »