.የኢሳት አማርኛ ዜና

አርበኞች ግንቦት ሰባትና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010) አርበኞች ግንቦት ሰባትና የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይል ንቅናቄ በአማራ ክልል ወጣቶችን በማደራጀትና በማሰልጠን በከፍተኛ ሁኔታ በመንቀሳቀስ ላይ መሆናቸውን አንድ የኮማንድ ፖስት ሰነድ አመለከተ። ለኢሳት የደረሰውና በጎንደር የኮማንድ ፖስት የተዘጋጀው ሰነድ ላይ አርበኞች ግንቦት ሰባትና አዴሀን ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማፍረስ እየተረባረቡ መሆናቸው ተገልጿል። በጎንደር ከተማ በስድስቱ ክፍለከተሞችና በጎንደር ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀው የኮማንድ ፖስቱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መድረክ ላይ የቀረበው ሰነድ ...

Read More »

በሞያሌ ከተማ ስለተገደሉት ዜጎች የሚያጣራው ቡድን የማጣራት ተልዕኮውን እንዲያቋርጥ ታዘዘ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 21/2010)በመከላከያ ሰራዊት አባላት በሞያሌ ከተማ ስለተገደሉት ዜጎች እንዲያጣራ የተሰየመውና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም የሚከታተለው መርማሪ ቡድን የማጣራት ተልዕኮውን እንዲያቋርጥ ታዘዘ። በኢትዮጵያ ፓርላማ የተቋቋመው የስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መርማሪ ቡድን ከመጋቢት 16 እስከ መጋቢት 24 ድረስ ወደ ሞያሌ ተጉዞ ምርመራ የማካሄድ እቅድ ነበረው። ዋዜማ የቡድኑን አባል ጠቅሶ እንደዘገበው መርማሪ ቦርድ “ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ” ነው በሚል ተልዕኳቸውን አቋርጠው እንዲመለሱ ተደርጓል። አስራሁለት ...

Read More »

የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ተጠራ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) እነእስክንድር ነጋ እንዲፈቱ ግፊት ለማድረግ የታሰበ የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ለነገ ተጠራ። በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኙ አክቲቪስቶች ያዘጋጁት የማህበራዊ ሚዲያ ዘመቻ ባለፈው ዕሁድ የታሰሩት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ መሪዎችን በተመለከተ ትኩረት እንዲያገኙና በአገዛዙ ላይ ጫና በመፍጠር እንዲፈቱ ለማድረግ እንደሆነ ተገልጿል። ኮከብ የሌለበትን ሰንደቅ ዓላማ ይዛችኋል በሚል በፖሊስ የታሰሩት እነእስክንድር ነጋ ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ጋር በተያያዘ በኮማንድ ፖስቱ የሚፈለጉ እንደሆነም መረጃዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ ፓርላማ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ሊሰይም ነው

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት20 /2010)የኢትዮጵያ ፓርላማ በመጭው ሰኞ በሚያካሂደው ስብሰባ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሰይም ታወቀ። በዚሁም መሰረት ኢህአዴግ የድርጅቱ ሊቀመንበር አድርጎ የሰየማቸው ዶክተር አብይ አሕመድ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ይሾማሉ። የዶክተር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነት የፓርላማ ሹመት በመጭው ቅዳሜ ይካሄዳል ተብሎ የሕወሃት ንብረት በሆነው ፋና ሚዲያ ከተገለጸ በኋላ እንደገና ለሰኞ መቀየሩ ተገልጿል። ፓርላማው በመጭው ሰኞ በሚያካሂደው ስብሰባ ተሰናባቹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ስልጣናቸውን ...

Read More »

የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በድጋሚ የማሸነፍ እድላቸውን አረጋገጡ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 29/2010) የግብጹ ፕሬዝደንት አብዱል ፈታህ አል ሲሲ በሃገሪቱ የተካሄደውን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በድጋሚ የማሸነፍ እድላቸውን ማረጋገጣቸው ታወቀ። ጠንካራ የሚባሉት ተቃዋሚዎች እራሳቸውን ከምርጫ ማግለላቸውን ተከትሎም በተቃዋሚዎች ዘንድ  መራጮች ድምጽ እንዳይሰጡ ጥሪ መደረጉን ቢቢሲ በዘገባው ላይ አስፍሯል። ለ 3 ቀናት በተካሄደው በዚህ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ተመዝግበው ድምጽ ያልሰጡ መራጮች ከ 500 – 28 ፖውንድ ቅጣት ይጠብቃቸዋል ተብሏል። የሀገሪቱ ህግ ለምርጫ የደረሰ ማንኛውንም ...

Read More »

ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) ዲያቆን ዳንኤል ክብረት፣አቶ አብዱ አሊ ሂጅራን ጨምሮ ታዋቂ ኢትዮጵያውያን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን አማካሪ ቦርድ አባል ሆነው ተሾሙ። ግለሰቦቹ የተመረጡበት መንገድ አነጋጋሪ ሆኗል። ለአዲስ አበባና ለኦሮሚያ የተዘጋጀው የተቀናጀ ማስተር ፕላን በሕዝባዊ እምቢተኝነት የተሰረዘ መሆኑ የሚታወቅ ነው። ይህንንም ተከትሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ከፍተኛ እልህ የተጋቡና ጥቅማችን ሊቀርብን ይችላል ያሉት የሕወሃት ነባር ባለስልጣናት የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በተናጠል እንዲታወጅ ...

Read More »

ዶክተር አብይ ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ ቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 20/2010) “ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን ውሰድ ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ከጎንህ ነው” የቀድሞው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለስልጣን የነበሩት ሚስተር ኽርማን ኮኽን  ዶክተር  አብይ ደፋር የለውጥ ርምጃዎችን እንዲወስዱ ጥሪ አቀረቡ። ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንደሆነም አረጋግጠዋል። የአፍሪካ ሕብረት የወቅቱ ሊቀመንበር እና የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜም በአፍሪካ ሕብረት  እና በአፍሪካ መሪዎች ስም የደስታ መግለጫ አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያም በአፍሪካ  አህጉር ታሪካዊ እና ...

Read More »

የዶ/ር አብይ የኢህአዴግ ሊ/መንበር ሆኖ በመመረጡ ደስታቸውን የገለጹ የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደበደቡ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የኦህዴዱ ሊ/መንበር ዶ/ር አብይ አህመድ የኢህአዴግ ሊቀመንበር ሆነው መመረጣቸው ይፋ እንደሆነ ደስታቸውን በመግለጽ ላይ የነበሩ የጅማ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣ በአጋዚ ወታደሮች ከፉኛ መደብደባቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ትናንት ፣ ረቡዕ፣ በኢንጂነሪንግ ትምህርት ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች፣በድስታ ሲጨፍሩ ኮማንድ ፖስት ሳታስፈቅዱ ለምን ጨፈራችሁ በሚል ...

Read More »

በጎንደር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው

በጎንደር የባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ እንዳያደርጉ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው (ኢሳት ዜና ማጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) አሽከርካሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ ትናንት ጠዋት የወታደራዊ እዙ አመራሮች ናቸው የተባሉና የከተማው ጸጥታ ሃላፊ ዘለቀ የሚባል ሰው በሲኒማ አዳራሽ በጠሩት ስብሰባ የባጃጅ አሽከርካሪዎች አድማ እንዳያደርጉ አስጠንቅቀዋቸዋል። አሽከርካሪዎች የዋጋ ተመን ቅናሽ እንዲያደርጉ፣ አርማ የሌለበትን ሰንደቅ አላማ እንዳያደርጉ፣ የኢትዮጵያ ካርታ፣ ኢትዮጵያ አገሬ የሚል ጽሁፍ እንዲያነሱ፣ የነጋስታቱን ፎቶ እንዲያወርዱ ካላወረዱ ...

Read More »

የአፋርና የኦሮሞህ ህዝብ ለማጋጨት የተደረገውን ሙከራ ኦነግና አነግፓ አወገዙ

የአፋርና የኦሮሞህ ህዝብ ለማጋጨት የተደረገውን ሙከራ ኦነግና አነግፓ አወገዙ (ኢሳት ዜና ማጋቢት 20 ቀን 2010 ዓ/ም) የኣፋር ነጻነት ግንባር ፓርቲና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ባወጡት መግለጫ፣ የኢሕኣዴግ ሃይሎች እራሳቸውን በመደበቅ በምስራቅና ሰሜን- ምስራቅ የኦሮሚያና የኣፋር ክልል ኣዋሳኝ ድንበር ላይ በሰላማዊ መንገድ ኑሮኣቸውን ሲመሩ በነበሩ ሲቪሎች ላይ ጥቃት ሊያደርሱ መሞከራቸውን ጠቅሰዋል። ድርጊቱ የወያኔ/ኢሕኣዴግ ስርዓት በመላው ሃገሪቷ ብሄሮችና ብሄረሰቦችን ለማናቆር ሲፈጽመው የነበረው ድራማ ...

Read More »