.የኢሳት አማርኛ ዜና

በአደርቃይ የተከሰተው ግጭት መቀጠሉ ተሰማ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) በሰሜን ጎንደር ዞን አደርቃይ የተከሰተው ግጭት መቀጠሉ ተገለጸ። በማይጋባ ወንዝ አካባቢ በሚገኘው የወርቅ ማውጣት ስራ በተሰማሩ ሰዎች የተነሳው ግጭት በመከላከያ ሰራዊት የሚደገፉ የትግራይ ሚሊሺያዎች ጣልቃ መግባታቸውን ተከትሎ አድማሱን በማስፋት መቀጠሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በግጭቱ ምክንያት በአደርቃይ ዛሬማና ሌሎች አነስተኛ መንደሮች የንግድና የትራንስፖርት እንቅስቃሴ መቋረጡን ጠቅሰዋል። በሌላ በኩል በቤንሻንጉል ጉምዝ በአማራ ተወላጆች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንደቀጠለ ነው። በቀስት ...

Read More »

የረመዳን ጾም ተጀመረ

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9 /2010) 1 ሺህ 439ኛው የረመዳን ጾም ዛሬ በመላው ዓለም ተጀመረ። የኢትዮጵያ  ሙስሊሞች የረመዳንን ጾም  ሰደቃ በማብዛት፣ የታመሙትን በመጠየቅና ከተቸገረው ጎን በመሆን ሃይማኖታዊ ግዴታቸውን እንዲወጡ የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል። የጾም ወቅቱ ከሚፈቅዳቸው በጎ ምግባራት ጎን ለጎን ሙስሊሙ ማህበረሰብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እንዲወጣ  የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብይ አህመድ ደግሞ ዛሬ የጀመረውን የረመዳን ፆም በማስመልከት ለመላ የእስልምና እምነት ተከታዮች ‘የእንኳን ...

Read More »

በጥቅም የተያዙ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለአብዲ ኢሌ ሽፋን እየሰጡ ነው ተባለ

በጥቅም የተያዙ የፌደራል መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ለአብዲ ኢሌ ሽፋን እየሰጡ ነው ተባለ (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) የሶማሊ ክልል ፕሬዚዳንት አብዲ ኢሌ በክልሉ ውስጥ የሚፈጽመው የሰብአዊ መብት ጥሰት በወንጀል የሚያስጠይቀው ቢሆንም፣ በገንዘብ ጥቅም የተያዙት በርካታ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናትና የመከላከያ አዛዦች ከለላ እየሰጡት መሆኑን ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ የክልሉ ተወላጆች ይናገራሉ። ከጅግጅጋና የተለያዩ ቦታዎች የተፈናቀሉ የኦሮሞ ተወላጆችን ጉዳይ እንዲያጣሩ የተላኩ ...

Read More »

የናይጀሪያዊው ባለሀብት የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ እና ሁለት ኢትዮጵያውያን የሥራ ባልደረቦቹ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደላቸው ዋናው መስሪያ ቤት ማብራሪያ ሰጠ

የናይጀሪያዊው ባለሀብት የዳንጎቴ ሲሚንቶ የኢትዮጵያ ሥራ አስኪያጅ እና ሁለት ኢትዮጵያውያን የሥራ ባልደረቦቹ በአሰቃቂ ሁኔታ ስለመገደላቸው ዋናው መስሪያ ቤት ማብራሪያ ሰጠ (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በበኩላቸው በተፈጸመው ግድያ ሀዘናቸውን መግለጻቸው ተነግሯል። የድርጅቱ የማርኬቲንግ ምክትል ሥራ አስኪያጁን አቶ ታሪኩ አለማየሁ ለብሉምበርግ በስልክ እንደገለጹት ዲፕ ካማራ እና ሁለቱ ኢትዮጵያውያን የድርጅቱ ሠራተኞች ባልታወቁ ታጣቂዎች ተገድለዋል። ሦስቱም ...

Read More »

በጉጂ ዞን የተፈናቀሉት የጌዲዮ ተወላጆች እስካሁን እርዳታ አልደረሰላቸውም

በጉጂ ዞን የተፈናቀሉት የጌዲዮ ተወላጆች እስካሁን እርዳታ አልደረሰላቸውም (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ከ100 ሺ በላይ የሚሆኑ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ እየገቡ ቢሆንም፣ እስከዛሬ ድረስ እርዳታ አለመቅረቡን የከተማዋ ምንጮች ገልጸዋል። ተፈናቀዮች ዛሬም ድረስ ከገጠር ወደ ከተማ እየገቡ ሲሆን፣ ብዙዎቹ እርዳታ በማጣታቸው ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ልመና ተሰማርተዋል። ሁኔታው እጅግ አስከፊ ነው የሚሉት የከተማዋ ምንጮች፣ አፋጣኝ እርዳታ ...

Read More »

የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ስልጣን ለቀቁ

የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ፕረዚዳንት ፕ/ር ጨመዳ ፊኒንሳ ስልጣን ለቀቁ (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) የሃረማያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጨመዳ ፊኒንሳ የስልጣን መልቀቂያ ደብዳቤያቸው ተቀባይነት በማግኘቱ ከኃላፊነት ተስተዋል ። ፕ/ር ጨመዳ ሃላፊነታቸውን ለመልቀቅ ለምን እንደፈለጉ በግልጽ ባይታወቅም፣ ከዩኒቨርስቲው ቦርድ ሰብሳቢ ከአቶ ስለሺ ጌታሁን ጋር ባላቻው አለመግባባት ይሆናል ሲሉ ምንጮች ይገልጻሉ። ሌሎች ወገኖች ደግሞ በዩኒቨርስቲው ውስጥ በየጊዜው የሚነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ፣ የጸጥታ ...

Read More »

ትናንት ማምሻውን በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ በ06 ቀበሌ በሚገኘው ደዌ ተቅዋ መስጂድ ግጭት ተፈጥሮ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ።

ትናንት ማምሻውን በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ በ06 ቀበሌ በሚገኘው ደዌ ተቅዋ መስጂድ ግጭት ተፈጥሮ በሰውና በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ ተገለጸ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) ምንጮቻችን ከሥፍራው እንደዘገቡት በእለቱ በስፍራው ለሶላት የመጡ ሙስሊሞች ለሁለት የተከፈሉ ሲሆን፣ የዚህም ምክንያቱ አብዛኛው ሙስሊም-የመንግስት ተላላኪዎች ናቸው የሚባሉትን” ፤ እናንተ የመንግሥት እንጅ የእስልምና ተወካይ ስላልሆናችሁ መስጂዳችንን መልሳችሁ ውጡልን!!” በማለት ተቃውሞ በማሰማቱ ነው። ...

Read More »

ኢቦላ በኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱ ተነገረ

ኢቦላ በኮንጎ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱ ተነገረ (ኢሳት ዜና ግንቦት 09 ቀን 2010 ዓ/ም) በዲሞክራቲክ ኮንጎ የታየው የኢቦላ ወረርሽኝ በፍጥነት እየተስፋፋ መምጣቱን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ገልጸዋል። ሚኒስትሩ ኦሊይ ሊሉንጋ ካሌንጋ ለቢቢሲ እንደተናገሩት፣ በሽታው በገጠር ከታየ በሁዋላ፣ አንድ ሚሊዮን ሰዎች ወደሚኖሩበት ምባንዳካ ከተማ ተዛምቷል። በሽታው ወደ ዋና ከተማዋ ኪንሻ ይዛመታል የሚል ፍርሃት ማሳደሩም ተዘግቧል። እስካሁን ድረስ 42 ሰዎች መያዛቸው የተረጋጋጠ ሲሆን፣ ...

Read More »

ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ

ከ100 ሺ በላይ የሚቆጠሩ የጌዲዮ ተወላጆች ከጉጂ ዞን ተፈናቅለው ገደብ ከተማ ገቡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ከሳምንታት በፊት በጉጂ ብሄረሰብ አባላትና በጌዲዮ ብሄረሰብ አባላት መካከል ተነስቶ የነበረው ግጭት ተከትሎ ከ200 ሺ በላይ ዜጎች ተፈናቅለው የነበረ ቢሆንም፣ ግጭቱን በሽምግልና ለመፍታት በተደረገው ሙከራ ብዙዎቹ ወደ ተፈናቀሉበት ቦታ ተመልሰው ነበር። ይሁን እንጅ ግጭቱ ካለፈው እሁድ ጀምሮ እንደገና በማገርሸቱ ከ 100 ...

Read More »

የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ

የአፋር ወጣቶች የጅቡቲን መስመር ዘግተው አመሹ (ኢሳት ዜና ግንቦት 08 ቀን 2010 ዓ/ም) ወጣቶቹ እርምጃውን የወሰዱት ከህዳር 26 ጀምሮ በደህንነት አባላት ታፍኖ ከተወሰደ በሁዋላ እስከዛሬ ድረስ ያለበት ያልታወቀው የሰመራ ዩኒቨርስቲ የሰው ሃይል አስተዳደር ሃላፊ አቶ ሳሊህ ረሺድ እንዲፈታ ለመጠየቅ ነው። ወጣቶቹ በሌሊት የጅቡቲን መንገድ በመዝጋት የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስተጓጎል ያደረጉ ሲሆን፣ የክለልዩ ልዩ ሃይል ወደ ስፋረው በመጓዝ መንገዱን አስከፍቷል። ወጣቶች መንገዱን ...

Read More »