የእስራኤል የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው ኢትዮጵያ ውስጥ ተወልዶ በ14 አመት እድሜው እኤእ በ1972 ወደ እስራኤል የተጓዘው ራቻሚም ኢላዛር በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር ሆኖ ተሹሟል። ራቻሚም ቴላቪቭ ዩኒቨርስቲ ገብቶ በዲግሪ የተመረቀ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ሲሆን፣ ላለፉት 30 አመታትም በጋዜጠኝነት ማገልገሉ ታውቋል።
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
በአዲስ አበባ ከፍተኛ የውሀ እጥረት ተከሰተ
ዘገቢያችን እንደገለጠው በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፈው አንድ ሳምንት ጀምሮ ውሀ የሚባል ነገር የለም። በገርጂ፣ አቃቂ ፣ አዲሱ ገበያ፣ መገናኛና በሌሎችም አካባቢዎች ነዋሪዎች ለመጠጥ የሚሆን ውሀ አጥተው ተቸግረዋል። የአዲስ አበባ መስተዳዳር የውሀ ባለስልጣናት ችግሮች መከሰታቸውን አምነው፣ ችግሮቹ የተፈጠሩት አንዳንድ የማስተላለፊያ መስመሮች በመበላሸታቸውና ክረምቱ ማለቁን ተከትሎ የውሀ እጥረት በማጋጠሙ ነው። እንደ ባለስልጣኖቹ ገለጣ ችግሮቹ በአብዛኛው በሚቀጥሉት 2 ወራት ውስጥ ይፈታሉ። 25 ...
Read More »የህወሐት ነባር አመራሮች በሰበብ አስባባቡ ስራ እየለቀቁ አንዳንዶችም በቅጣት በማይመጥናቸው ቦታ እየተመደቡ መሆኑ ታወቀ
ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የኢፈርት ዋና ስራ አስኪያጅ የነበሩት አቶ አባዲ ዘሙ ከሀላፊነታቸው ተነስተው በኢትዮጵያ የሱዳን አምባሳደር ሆነው ተሹመዋል። በሌላ በኩል ደግሞ በሱዳን የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት አቶ ሐይሌ ኪሮስ ገሰሰ የስራ ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ሀላፊነታቸውን እንዲለቁ ተደርገዋል። አቶ ሀይለ ኪሮስ ገሰሰ ከቻይና አምባሳደርነት ሲነሱ የቀድሞውን የዶ/ር ተቀዳ አለሙን የምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትርነት ቦታ እይዛለሁ ብለው ገምተው የነበረ ቢሆንም፣ ቦታው ለአቶ ብርሀነ ...
Read More »በአውሮፓ የሚኖሩ ሙስሊሞች መንግስት አህባሽ የተባለውን የእስልምና አስተምህሮ ለማስፋፋት እቅድ ዘርግቶ መንቀሳቀሱን አወገዙ
ኢሳት ዜና:-1 ሺ 4 መቶ 33ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል በብራሰልስ፣ ቤልጂም በተከበረበት ወቅት የሉቅማን ኢትዮጵያዊያን ቤልጄማውያን ሙስሊሞች ማህበር ሊቀመንበር የሆኑት አብዩ ያሲን መንግስት በፖሊሲ ደረጃ ቀርጾ አህባሽ የተባለውን የእስልምና አስተምህሮ ለማስፋፋት እየሰራ መሆኑን የጽሁፍና የንግግር ማስረጃዎችን በማቅረብ ለተሳታፊው አስረድተዋል። ከዚህ ቀደም በአለማያ ከተሰጠው ስልጠና በተጨማሪ በአሁኑ ጊዜ መንግስት በሰንዳፋ ወታደራዊ ማሰልጠኛ ውስጥ 200 የሚሆኑ የአህባሽ አሰልጣኞችን እያሰለጠ መሆኑን ...
Read More »አርቲስትና የመብት ተሟጋች ደበበ እሸቱ አርብ እለት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ብቻውን በዝግ ችሎት ቀረበ
ዳኛ ታሪኳ ተበጀ በሚያስችሉት አንደኛ ወንጀል ዝግ ችሎት ላይ ማንኛውም የተከሳሽ ቤተሰብ፣ ጋዜጠኛ፣ የመብት ተሟጋችና ታዛቢዎች እንዲገቡ አልተፈቀደም፡፡ ከተከሳሾቹ ቀደም ብለው ፍርድ ቤቱን የከበቡት ፌዴራል ፖሊሶች በችሎቱ አቅራቢያ ማንኛውም ሰው እንዳይጠጋ የከለከሉ ሲሆን ሦስት ጋዜጠኛች ብቻ የፖሊሶችን ከለላ በትግል አልፈው የፍርድ ቤቱ መዝገብ አመላላሽ ጋር በመድረስ “እኛ ጋዜጠኞች ነን ፖሊሶች ከልክለውን ነው፣ እባክሽን ዳኟዋ ጋር ሂጂና እንድንገባ እንድትፈቅድልን ጠይቂልን” በማለት መታወቂያቸውን ያሳይዋት ሲሆን ፣ ...
Read More »የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚቴ ለሱዳን የተሰጠው ሰፊ መሬት ለወደፊቱ የግጭት መንስኤ ሊሆን እንደሚችል አስጠነቀቀ
ኢሳት ዜና:-ኮሚቴው ኖቬምበር 3፣ 2011 ለሱዳኑ ፕሬዚዳንት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው፣ የመለስ መንግስት ከኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን ከራሱ የፓርላማ አባላትም ሳይቀር በመደበቅ ለሱዳን የሰጠው ሰፊ የኢትዮጵያ መሬት ህጋዊ ተቀባይነት የለውም። የድንበር ኮሚቴው የመለስ መንግስት የኢትዮጵያ ህዝብ ከመሬቱ አልተፈናቀለም እያለ ቢናገርም፣ ሚስጢራዊ ሰነዶችን በማውጣት ታወቀው ዊኪሊኪስ የመለስ መንግስት ሰፊ የሆነ ለም መሬት ለሱዳን መስጠቱን ከበቂ በላይ ማረጋገጡን ጠቅሶአል። የሱዳኑ መሪ የአፍሪካ ህብረት ...
Read More »በደቡብ ክልል በዳውሮ ዞን በዋካ ከተማ የተነሳውን ግጭት ተከትሎ የታሰሩት 20 የሚጠጉ የአገር ሽማግሌዎች መፈታታቸው ታወቀ
ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት ከወረዳና ከሌሎች ማህበራዊ ጥያቄዎች ጋር በተያያዘ በከተማው የተነሳው ግጭት ያሳሰበው የፌደራሉ መንግስት፣ የታሰሩት የአገር ሽማግሌዎች ተለቀው ችግራቸው እንዲታይላቸው የሚል ትእዛዝ ማስተላለፉ ታውቋል። በዚህም መሰረት የአገር ሽማግሌዎቹ አርብ ማምሻውን መለቀቃቸው ታውቋል። ይሁን እንጅ ስርአቱን ሲያወግዙ የነበሩ ወጣቶች ግን በብዛት እየታሰሩ መሆናቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የአካባቢው ህዝብ ባስነሳው ተቃውሞ ትምህርት ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት መስጪያ ተቋማት ተዘግተው እንደነበር መዘገባችን ይታወሳል። ...
Read More »የኦሮሞ ተዋጊዎችን ፍለጋ ድንበር ያቋረጠው የኢትዮጵያ ሰራዊት ሶማሊያን ለቆ ወጣ
የኦሮሞ ተዋጊዎችን በማሳደድ ቄዳር እና ማራ-ዲሌ ወደ ተባሉ የሶማሊያ አካባቢዎች ድንበር አቋርጦ የገባዉ ቁጥሩ እጅግ የበዛ የኢትዮጵያ ጦር ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን፤ ኦል አፍሪካን የዜና አገልግሎት ዘግቧል። ሰራዊቱ በአካባቢዉ የሚያደርገዉን አሰሳ አጠናቆ ከአንድ ቀን በሁዋላ ሶማሊያን ለቆ መዉጣቱን የገለፁት፤ የአካባቢዉ የአይን ምስክሮች እንደሆኑ የዜና አግልግሎቱ ገልጿል። የማእከላዊ ሶማሊያ ከተሞችን ይዞ የሚገኘዉ የኢትዮጵያ ሰራዊት የሶማሊያን ድንበር አቋርጦ የገባዉ፤ ለዘብተኛ የሆነዉ የአህሉ ሱና ...
Read More »በከፍተኛ ድጎማ ከውጪ የተገዛ ስንዴ ለህዝቡ መከፋፈል መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ
ኢሳት ዜና:- አቶ መለስ ዜናዊ ባለፉት 20 አመታት የእርሻ ምርት በ40 በመቶ ማደጉን በገለፁበት ማግስት በከፍተኛ ድጎማ ከውጪ የተገዛ ስንዴ ለህዝቡ መከፋፈል መጀመሩን የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘገቡ። በስንዴ እጥረት ምክንያት፡በርካታ ዳቦ ቤቶች ሥራቸውን ባቆሙበት ባሁኑ ጊዜ መንግስት ለአንድ ኩንታል እስከ ሁለት መቶ ብር ድጎማ በማድረግ ከውጪ የገዛው ስንዴ በዐዲስ አበባ በሁሉም ወረዳዎች እየተከፋፈለ ነው። ስንዴው እታደለ ያለውበ ሸማቾች ማህበር አማካይነት ...
Read More »ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ በእስር ላይ የሚገኙት የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ኢትዮጵያውያን በአምነስቲ ኢንተርናሽናል አማካኝነት ደብዳቤ እንዲጽፉ ጠየቁ
ኢሳት ዜና:- የቀድሞው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ወ/ት ብርቱካን በአምነስቲ ድረ ገጽ ላይ ባሰፈሩት ጽሁፍ “በፌስቡክና በቲዊተር ዘመን ደብዳቤ መጻፍ አያስፈልግም የሚሉ ሰዎች የእኔን የእስር ዘመን እንዲያስታውሱ እመክራቸዋለሁ” ብለዋል። “እኔ ነጻ እሆናለሁ የሚል ተስፋ አልነበረኝም። እኔ ምንም ወንጀል ሳልፈጽም ሀሳቤን በነጻነት በመግለጼ ብቻ ነበር የታሰርኩት ። የኢትዮጵያ መንግስት ተቀናቃኞችን ለእስር በመዳረግ ተቃውሞን ለማፈን የሚችል ይመስለዋል” ያሉት ወ/ት ብርቱካን አምነስቲ ኢንተርናሽናል በ2009 ...
Read More »