ህዳር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ፦” የታሰሩት ሰዎች በሙሉ ሽብርተኛ ለመሆናቸው ከበቂ በላይ ማረጋገጫ አለን” ሲሉ ቢደመጡም ፤የ ኢትዮጵያ ህዝብ ግን የታሠሩት በሙሉ የሰላምና የነፃነት ታጋዮች እንጂ አሸባሪዎች እንዳልሆኑ በተደጋጋሚ ሲናገር መቆየቱ ይታወቃል። ከእስረኞቹ ቤተሰቦች አንዱ ለ ኢሳት በሰጡት አስተያዬት፦” የታሰሩት ወንድምና እህቶቻችን አሸባሪዎች እንዳልሆኑ ራሳቸው እነ አቶ መለስ ያውቁታል።የሚያደርጉት የትግል እንቅስቃሴ ስልጣናቸውን እንዳያሳጣቸው በማሰብ ነው ያሰሯቸው። ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ስሎቫኪያ ፦”ኢትዮጵያ ለፈጸመችው ስህተት በይፋ ይቅርታ ልትጠይቅ ይገባል” ስትል አሣሰበች
ህዳር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስሎቫኪያ በኢትዮጵያ ታስረው የነበሩትን አምባሳደሯን አስመልክቶ በኢትዮጵያ መንግስት የተሰጣት ማብራሪያ በቂ ስላልሆነ ተጨማሪ ማብራሪያ እንዲሰጣት አጥብቃ ጠይቃለች። “ ዘ ስሎቫክ ስፔክታተር” የተባለው የስሎቫኪያ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ በኢትዮጵያ ፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር ውለው ለሁለት ቀናት ከታሰሩ በኋላ የተለቀቁት በኢትዮጵያ የስሎቫኪያ አምባሳደር፣ በጉዳዩ ዙርያ ከስሎቫክ ባለሥልጣናት ጋር ለመመካከር ወደ አገራቸው ተመልሰዋል ፡፡ አምባሳደር ሚላን ዱብቼክ ከመኖሪያቸው ወጥተው የእግር ጉዞ ...
Read More »በዋካ ከተማ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ መርተዋል የተባሉት አባት ከሀላፊነት እንዲነሱ ተደረገ፣ ህዝቡ ግን ተቃውሞውን እያሰማ ነው
ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአካባቢው ያለውን ጭቆና፣ የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ መታጣት በመቃወም እራሱን በእሳት በማጋየት ተቃውሞን የገለጠው የመምህር የኔሰው ገብሬ አስደንጋጭ ዜና የህዝቡ የመነጋገሪያ አጀንዳ በሆነበት ማግስት፣ የአካባቢው የሀይማኖት ባለስልጣናት፣ “ተቃውሞውን የሚያስተባብሩት በከተማው የሚገኘው የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ካህን ናቸው” በሚል ሰበብ ፣ የቤተክርስቲያኑዋን አስተዳዳሪ የሆኑትን በኩረ ትጉሀን ይልማ መኮንንን ከሃላፊነት አንስተዋል። የእገዳውን ደብዳቤ የጻፉት የዞኑ የአገረስብከት ሀላፊ የሆኑት መምህር ...
Read More »በኢትዮጵያ የዳቦ ታሪፍ መመሪያ ወጣ
ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፉት 20 ዓመታት የግብርና ምርትን 40 በመቶ አሳድጌያለሁ የሚለው የአቶ መለስ መንግስት፤ ልክ እንደ ታክሲ ሁሉ ለዳቦም- ታሪፍ ማውጣቱን የዘገበው፤ ፍኖተ-ነፃነት ነው። የአዲስ አበባ ንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሕዳር 2 ቀን 2004 ዓመተ ምህረት ባወጣው የታሪፍ መመሪያ በከተማዋ በሚገኙ ዳቦ ቤቶች 100 ግራም ዳቦ በ1 ብር ከ20 ሳንቲም፣200 ግራም ዳቦ በ2 ብር ከ40 ሳንቲም እና፣300 ...
Read More »የየካ ክፍለ-ከተማ ነዋሪዎች ፤የኢህአዴግ ልማት ኮሚቴ የጠሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ተዘገበ
ህዳር 6 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የየካ ክፍለ-ከተማ ነዋሪዎች ፤የኢህአዴግ ልማት ኮሚቴ የጠሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸው ተዘገበ። ህዝቡ በአዲሱ የሊዝ አዋጅ እያመፀ ነው፡፡ በሺህ የሚቆጠሩ ነዋሪዎች ስብሰባውን ረግጠውና የስብሰባውን አዳራሽ ጥለው ለመውጣት የተገደዱት ፤በአዲሱ የመሬት ሊዝ አዋጅና በመሬት ይዞታ ማረጋገጫ፣ እንዲሁም በሊዝ የክፍያ ስርዓትና ባለይዞታዎች በካሬ ሜትር እንዲከፍሉ በተተመነው ገንዘብ ዙሪያ ጥያቄ አቅርበው ከመድረክ ምላሽ ስለተነፈጋቸው መሆኑ ታውቋል፡፡ ህዝቡ “ልማትን” አስመልክቶ ...
Read More »በሸዋ ሮቢት አንድ የእህል ንግድ ድርጅት ተወካይ በነጋዴውና በመንግስት መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ እራሱን ውሀ ውስጥ ወርውሮ መግደሉ ታወቀ
ህዳር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሰሜን ሸዋ ዞን በሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኙ ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ለሀላፊው ሞት ምክንያት የሆነው በመንግስትና በነጋዴዎች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ነው። መንግስት ወደ ውጭ አገር የሚልከው ማሽ እየተባለ የሚጠራው የአበባ እህል መጠን መቀነሱን ተከትሎ፣ በእህል ንግድ ድርጅት አማካኝነት ግዢ እንዲፈጸም መመሪያ ማውጣቱን የገለጡት ምንጮች፣ መመሪያውን ተንተርሶ፣ 14 የአካባቢው ነጋዴዎች 4 ሺ ኩንታል የማሽ እህል ...
Read More »የግንቦት 7 ህቡዕ አባላት ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 4 ወጣቶች ታፍነው ተወሰዱ፣ አንድ ወጣት ደግሞ የደረሰበት አልታወቀም
ህዳር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በምእራብ ጎጃም ዞን ውስጥ በሚገኝ አንድ ወረዳ ውስጥ ይኖሩ የነበሩ 4 ወጣቶች የግንቦት 7 የእቡዕ አባላት ናቸው ተብለው በመጠርጠራቸው በደህንነት ሰዎች ተወስደው መታሰራቸውን የአማራ ክልል ወኪላችን የላከው ዘገባ ያመለክታል። ለደህንነታቸው ሲባል የቤተሰቦቻቸውን እንዲሁም የወረዳውንና ቀበሌውን ዝርዝር ከመግለጥ የተቆጠበው ዘጋቢያችን፣ ወጣቶቹ የተያዙት ኖቬምበር 7፣ 2011 ወይም ጥቅምት 30፣ 2004 ሲሆን፣ ከአንደኛው ወጣት አድርሻ በስተቀር ሶስቱ ወጣቶች ...
Read More »እስራኤል፣ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ደቡብ ሱዳንንና ታንዛኒያን ያቀፈ አንድ አክራሪነትን የሚዋጋ ጥምረት ልትፈጥር መሆኑ ታወቀ
ህዳር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን የተናገሩት የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ፣ አገራቸው የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በምታደርገው እንቅስቃሴ እስራአል ድጋፍ እንድትሰጣቸው ለመጠዬቅ ወደ ቴላቪቭ ባመሩበት ወቅት ነው። ለኬንያ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ናታኒያሁ፣ አገራቸው የእስልምና አክራሪነትን ለመዋጋት ኢትዮጵያን፣ ታንዛኒያን፣ ደቡብ ሱዳንንና ኬንያን ያቀፈ ጥምረት ለመመስረት እየሰራችመ መሆኑን ይፋ እድርገዋል። ጠቅላይ ሚኒሰትር ናትኒያሁ የኬንያ ...
Read More »ፍትህና ዲሞክራሲ በሌለበት አገር አልኖርም በሚል ምክንያት አንድ መምህር ራሱን በእሳት አጋዬ
ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዋካ ከተማ ነዋሪ የሆነው መምህር የኔሰው ገብሬ የስድስት ወረዳዎች ባለስልጣናት በአንድነት ተሰባስበው በቅርቡ በዋካ የተፈጠረውን ችግር በሚወያዩበት ወቅት፣ በራሱ ላይ ቤንዚን አርከፍክፎ እየተቃጠለ ወደ ስብሰባ አዳራሹ ገብቷል። መምህሩ ራሱን እያነደደ ወደ ውስጥ ሲገባ የተመለከቱት የወረዳ ባለስልጣናት በመደናገጣቸው ከመምህሩ ለመራቅ ጥረት ያደርጉ ነበር ተብሎአል። ምሁሩ በከተማው ውስጥ ከሚታወቁት በሳል ምሁራን መካከል አንዱ ነው የሚሉት ...
Read More »መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ
ህዳር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገው ጣልቃ ገብነት በጊዜ ካልተገታ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚፈጠረው የሙስሊሞች መከፋፈልና በአገሪቱ ሰላምና መረጋጋት ላይ ለሚያመጣው መዘዝ ተጠያቂ ነው ሲሉ በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ገለጡ:: ኦክቶበር 30፣ በቶሮንቶ አካባቢ የሚኖሩ በርካታ ሙስሊሞች ያደረጉትን ስብሰባ ተከትሎ ባወጡት መግለጫ ፤ ” የኢትዮጵያ መንግስት በፌደራል ሚኒስትሩ ቢሮ አማካኝነትና ሕዝብ ባልወከላቸው ግለሰቦች በሚመራውና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጠቅላይ ...
Read More »