እስራኤል፣ ኢትዮጵያን፣ ኬንያን፣ ደቡብ ሱዳንንና ታንዛኒያን ያቀፈ አንድ አክራሪነትን የሚዋጋ ጥምረት ልትፈጥር መሆኑ ታወቀ

ህዳር 5 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ይህን የተናገሩት የኬንያው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት ራይላ ኦዲንጋ፣ አገራቸው የአልሸባብን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር በምታደርገው እንቅስቃሴ እስራአል ድጋፍ እንድትሰጣቸው ለመጠዬቅ ወደ ቴላቪቭ ባመሩበት ወቅት ነው።

ለኬንያ ጥያቄ አዎንታዊ መልስ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ናታኒያሁ፣ አገራቸው የእስልምና አክራሪነትን ለመዋጋት ኢትዮጵያን፣ ታንዛኒያን፣ ደቡብ ሱዳንንና ኬንያን ያቀፈ ጥምረት ለመመስረት እየሰራችመ መሆኑን ይፋ እድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ናትኒያሁ የኬንያ ጠላቶች የእስረኤልም ጠላቶች ናቸው ብለው መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

አራቱ አገሮች በእስራኤል መሪነት የእስልምና አክራሪነትን የሚዋጋ ጥምረት በይፋ የሚመሰርቱ ከሆነ፣ የአካባቢውን የሙስሊም አገሮች ሊያስቆጣና ምስራቅ አፍሪካን የትርምስ ቀጠና ሊያደርገው እንደሚችል የፖለቲካ ተንታኞች ይናገራሉ።

ኬንያ ጦሩዋን ወደ ሶማሊያ በማስገባት ከአልሸባብን ሰራዊት ጋር እየተዋጋች መሆኑ ይታወቃል።