በባሌ ጎባ አንጻራዊ መረጋጋት ቢታይም አሁንም ስጋቶች እንዳሉ ነዋሪዎች ገለጹ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ባለፈው ቅዳሜ ደም አፋሳሽ የነበረው ግጭት የመከላከያ ሰራዊት አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ አንጻራዊ መረጋጋት ታይቶበታል። ባለፈው ረቡዕ የዞኑ ባለስልጣናት የባሌ ገበሬዎች አመጽ መሪ የነበሩትን የሃጂ አደም ሳዶን ሃውልት ለማቆም በሚል ህዝቡን አወያይተው የነበረ ሲሆን፣ በእለቱ አብዛኛው ተሰብሳቢ ሃውልቱ ቢቆም ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መምህራን ጋር ባደረጉት ዉይይት ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባረው የነበሩ መምህራን ወደሥራቸው መመለስ እንደሚችሉ አስታወቁ (ኢሳት ዜና ሃምሌ 16 ቀን 2010 ዓ/ም )በጠቅላይ ሚኒስቴር የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከመላው ኢትዮጵያ ከሃምሳ ዩኒቨርሲቲዎች ከተወጣጡ 3 ሽህ 175 የዩኒቨርሲቲ መምህራን ጋር በአገሪቱ የከፍተኛ የትምህርት ጥራት፣ አገራዊ አንድነት፣ አገሪቱ ስላለችበት ወቅታዊ ሁኔታ፣ ስለ ብልሹ አሰራር እና ...
Read More »አቶ ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆኑ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) በቅርቡ በጡረታ የተሰናበቱት አቶ ግርማ ብሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ተሾሙ። የቀድሞው የብሔራዊ ባንክ ገዢ አቶ ተክለወልድ አጥናፉም የቦርድ አባል ሆነው መሰየማቸው ተመልክቷል። የብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ኢዮብ ተካልኝ፣ የብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዢው አቶ በቃሉ ዘለቀም የብሔራዊ ባንኩ የቦርድ አባላት ሆነው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ መሾማቸውን የዘገበው አዲስ ፎርቹን ነው። የብሔራዊ ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር ...
Read More »በአማራ ክልል በአሁኑ ወቅት በስውር ችግር የመፍጠር አቅም ያለው አካል የለም
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) በአማራ ክልል በአሁኑ ወቅት ሌላ ሃይል ጣልቃ ገብቶ በሃይል ወይንም በስውር ችግር የመፍጠር አቅም እንደሌለው ርዕሰ መስተዳድሩ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ገለጹ። ርዕሰ መስተዳድሩ ሁሉም አቅም በራሳችን እጅ ስላለ የሕግ የበላይነትን የማስከበር ስራው በኛ ብቻ ይወሰናል ሲሉ ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በነበሩ ሁኔታዎች የሰብአዊ መብት ጥሰቶችና ሌሎች ችግሮች ከክልሉ መንግስት ቁጥጥር ውጭ ነበሩ ብለዋል። በአማራ ክልል ችግሮች ቢፈጠሩ እንኳን ...
Read More »በሳውላ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው
በሳውላ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፍ ሲያስተባብሩ የነበሩ ሰዎች ጥቃት እየደረሰባቸው ነው ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በጎፋ ሳውላ የተካሄደውን የድጋፍ ሰልፍ ተከትሎ ፣ ሰልፉን አስተባብራችሁዋል የተባሉ ሰዎች እየተደበደቡ ታስረዋል። በሰልፉ ዋዜማ እለት አንድ እናት እስከ ልጃቸው የተደበደቡ ሲሆን፣ ከሰልፉ በሁዋላ ደግሞ በርካታ ወጣቶች በባለስልጣናት ድብደባ ደርሶባቸዋል። የአካባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት 5 ሰዎች ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ቤተሰብ እንዳይጠይቁዋቸው ...
Read More »በሃረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት በተገኘው አጽም የተጠረጠሩ የፖሊስ አዛዦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ ተላለፈ
በሃረሪ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት በተገኘው አጽም የተጠረጠሩ የፖሊስ አዛዦች በቁጥጥር ስር እንዲውሉ ውሳኔ ተላለፈ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ግምጃ ቤት የተገኙትን አጽሞች ተከትሎ ዛሬ አርብ ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓም የክልሉ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አበበ መብራቱ ፣ ም/ል ፕሬዚዳንት ጋቢሳ ተስፋዬ፣ ሃብሊ ሊቀመንበር አቶ ኦርዲን በድሪ፣ በኦህዴድ የሃረሪ ...
Read More »በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ
በርካታ የጌዲዮ ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከስራቸው ተባረሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) በቅርቡ በጉጅና ጌዲዮ ማህበሰረቦች መካከል የነበረውን ግጭት ተከትሎ በተለያዩ ያሃላፊነት ደረጃ ላይ የነበሩ የጌዲዮ ማህበረሰብ የመንግስት ሰራተኞች በጉጂ ዞን ከሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተባረዋል። ነዋሪዎች እንደሚሉት በሰዎች እና በንብረት ላይ ከደረሰው ጉዳት በተጨማሪ፣ የብሄረሰቡ ተወላጆች ከስራ መባረራቸው ተቀባይነት የለውም። ከተባረሩት መካከል ከ 30 በላይ ...
Read More »በሽንሌ ዞን በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ
በሽንሌ ዞን በህዝቡ ላይ የሚደርሰው ጥቃት መጨመሩን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ ( ኢሳት ዜና ሃምሌ 13 ቀን 2010 ዓ/ም ) ላለፉት 5 ወራት በሺንሌ ዞን የተጀመረው ተቃውሞ እየቀጠለ ባለበት ሰዓት ፣ የአብዲ ኢሌ አስተዳደር የሚወስደውም እርምጃ በተመሳሳይ መልኩ እየጨመረ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሻለቃ አሊ ሳምሪ ሰገድ እንደተናገሩት ከ3 ቀናት በፊት አዲጋላ ላኢ አንዲት ሴት መገደሏንና ሌላ ሴት ደግሞ መቁሰሏን ተናግረዋል። ...
Read More »የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም ያግዛል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በአሜሪካ ከኢትዮጵያውያን ጋር የሚያካሂዱት ውይይት ጥላቻና መከፋፈልን በማስወገድ ለአንድ ሃገር በጋራ ለመቆም እንደሚያግዝ የጉብኝቱ የአቀባበል ኮሜቴ ገለጸ። በዋሽንግተን ዲሲ የአቀባበል ኮሜቴ ሰብሳቢዎች በአሜሪካ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሰጡት መግለጫ ላይ ይሄ ለውጥ ከመምጣቱ በፊት የችግሩ ሰለባ የሆኑ ግለሰቦች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ፊት ለፊት ለመወያየት እድሉ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ሐምሌ 28/2010 በዋሽንግተን ኮንቬንሽን ...
Read More »የምህረት አዋጁ ጸደቀ
(ኢሳት ዲሲ–ሐምሌ 13/2010)የምህረት አዋጁ ጸደቀ። የምህረት አዋጁ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱና የሚፈለጉ እንዲሁም የተፈረደባቸውን ሰዎች ጭምር ነጻ የሚያደርግ መሆኑም ታውቋል። ፓርላማው በአስቸኳይ ስብሰባው ያጸደቀው የምህረት አዋጁ ከግንቦት 30/2010 በፊት በወንጀል የሚፈለጉና የተፈረደባቸው እንዲሁም የተከሰሱ ሰዎችን ሙሉ በሙሉ ከወንጀል ተጠያቂነት ነጻ የሚያደርግ መሆኑንም መረዳት ተችሏል። የምህረት አዋጁ የኮበለሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላትንም ነጻ የሚያደርግ ይሆናል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በአንድ ድምጸ ተአቅቦ ...
Read More »