ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ “ የኢትዮጵያ ህዝብ ማንኛዉንም መስዋዕትነት ይከፍላል፡ በአንድ ቃል ‘ ግድቡ ይሰራ!’ እንደሚሉ ምንም ጥርጥር የለኝም” በማለት የተናገሩ ቢሆንም ፣ ዜጎች በአብዛኛዉ በግንባታዉ ስራ ደስተኛ እንዳልሆኑ ክርስቲያን ሳይንስ ሞኒተርስ ዘገበ። አገሪቱ በራሷ ተግባራዊ አደርገዋለሁ ብላ የተያያዘችዉና ያደረባት ጉጉት ከሚገባዉ በላይ መጠኑን ያለፈ መሆኑ እና ፕሮጀክቱ ለህዝብ በተገለፀ ከአንድ ወር በሚያንስ ጊዜ ዉስጥ ...
Read More ».የኢሳት አማርኛ ዜና
ኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዊያን በደረሰባቸዉ የዘር መድልዎ ያነሱት ተቃዉሞ እንደሚጣራ ፖሊስ አረጋገጠ
ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእየሩሳሌም ኪሪያት ማላኪ በተባለዉ አካባቢ ነዋሪዎች ቤታቸዉን ለኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዊያን ላለማከራየትና ላለመሸጥ በፊርማ ያደረጉት ስምምነት ያስቆጣቸዉ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላቀረቡት አቤቱታና ተቃዉሞ የተሰጣቸዉ መልስ ሌላ ቁጣን አስከትሏል። የቤተ እስራኤላዉያኑን አቤቱታ ለመስማት የተገኙት የእስራኤል የስደተኛ ጉዳዮች ሚኒስትር ወ/ሮ ሶፋ ላንድቨር “ ከኢትዮጵያ የመጡት ፈላሻዎች የእስራኤል መንግሰት ላደረገላቸዉ ዉለታ ምስጋና ሊያቀርቡ ይገባል” በማለት የሰጡት ምላሽ “በዘር ላይ ...
Read More »በም/ጎጃም በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ አንድ ባለስልጣን ሲገደል ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ አንድ ባለስልጣን ከፉኛ ቆስለዋል
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል በምእራብ ጎጃም ዞን በይልማና ዴንሳ ወረዳ በአዴት ከተማ በተነሳ የህዝብ ተቃውሞ አንድ ባለስልጣን ሲገደል ሌሎች ሁለት ፖሊሶች እና ሌላ አንድ ባለስልጣን ከፉኛ ቆስለዋል። ማምሻውን በደረሰን ዜና ደግሞ በጽኑ ከቆሰሉት መካከል አንደኛው ህይወቱ አልፎአል። በትናንትናው እለት የወረዳው ባለስልጣናት የጨረቃ ቤቶችን ለማፍረስ በተንቀሳቀሱበት ጊዜ፣ ህዝቡ ቤታችንን አታፈርሱም በማለት ከባለስልጣኖች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብቶ ነበር። ...
Read More »የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች የሚያደርጉትን አድማ እንደቀጠሉ ነው
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት የተጀመረው የተማሪዎች ተቃውሞ እየከረረ በመሄዱ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በተማሪዎች ላይ ስለሚወስዱት እርምጃ ግራ ተጋብተዋል ይላል የደረሰን መረጃ። ተማሪዎቹ ላለፉት ሁለት ቀናት ምግብ እንዳላገኙ፣ ግቢያቸውን ለመልቀቅም ፈቃደኞች እንደልሆኑ፣ የፌደራል ፖሊስ አባላትም አካባቢውን ከቦ መቀመጡን ለማወቅ ተችሎአል። የአወልያ ኮሌጅ እና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዛሬው እለት ለተለያዩ የእስልምና ተከታዮች የስልክ ጥሪ በማድረግ ለዝሁር ጸሎት እንዲቀላቀሏቸው ...
Read More »አገር የመጠበቅ ግዳጅ ተጥሎበታል የተባለው መከላከያ ሚኒስቴር፤ በሆቴል ግንባታና ንግድ ውስጥ መሰማራቱ ተዘገበ
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እንደ ፎርቹን ዘገባ፤መከላከያ ሚኒስቴር በትግራይ-መቀሌ ውስጥ በ165 ሚሊዮን ብር ወጪ ለከፍተኛ የጦር መኮንኖች መዝናኛ የሚሆን ባለ ሦስት ኮከብ ልዩ ሆቴል ለማስገንባት እንቅስቃሴ የጀመረ ሲሆን፤ ሆቴሉን በበላይነት ከመቆጣጠር ባሻገር የንግድ ስራውን የሚያካሂደውም ራሱ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ነው። በኢትዮጵያ የመከላከያ ታሪክ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር ፤ ንግድ ለማካሄድ ሆቴል ሲያስገነባ ፤ይህ የመጀመሪያው ነው። በመከላከያ ሚኒስቴር አማካይነት መቀሌ ...
Read More »ሁለት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተገደሉ
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሰሞኑን ለቀምት ከተማ በሚገኘው የወለጋ ዩኒቨርስቲ ግጭት መፈጠሩን ተከትሎ ሲራጂ እና ከማል የተባሉ ሁለት የሕግ ተማሪዎች ሞቱ። ተማሪዎቹ የተገደሉት በፖሊስ በተተኮሰ ጥይት ይሁን ወይም በሌላ ምክንያት እስካሁን የተረጋገጠ ነገር ባይኖርም፤ ውስጥ አዋቂዎች ፦”ተማሪዎቹ የሞቱት በምግብ መመረዝ ነው”ማለታቸውን ፍኖተ -ነፃነት ዘግቧል። የሟቾቹ ተማሪዎቹ የቀብር ሥነ ሥርዓት ከትናንት በስቲያ ተፈጽሟል። ስለጉዳዬ የ ዩኒቨርሲቲውን ሀላፊዎች ለማነጋገር የተደረገው ...
Read More »የኑሮ ውድነቱ ፤ ለእግር ኳስ ውድድር መቋረጥ ምክንያት ሆነ
ጥር 3 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በቅዱስ ጊዮርጊስና በ አየር ሀይል ክለቦች መካከል ከትላንት በስቲያ በደብረዘይት ከተማ ሊከናወን የነበረው የእግር ኳስ ውድድር ፤ከኑሮ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ተመልካቹ ማሰማት በጀመረው ተቃውሞ መባባስ ምክንያት ተቋረጠ። ውድድሩ ከመጀመሩ በፊት በስቴዲዮሙ የተገኘው ተመልካች የወቅቱን የኑሮ ውድነትና በገዥው ፓርቲ እየተፈጸመ ያለውን የአፈና ድርጊት በዜማና በግጥም መቃወም መጀመሩን የዘገበው ፍኖተ-ነፃነት፤ በዚህ መልክ የተጀመረው የተመልካች ተቃውሞ ውድድሩም ...
Read More »በእኛ መታሰር በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰት ዓለም ለማወቅ ችሎአል ሲሉ የስዊድን ጋዜጠኞች መናገራቸው ተሰማ
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በእኛ መታሰር ዓለም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የፕሬስ ነጻነት አፈና ለማወቅ ችሎአል ሲሉ በእስር ላይ የሚገኙት የስዊድን ጋዜጠኞች መናገራቸው ተሰማ ሲኤን ኤን የማርቲን ሺቢየ እናት የሆኑትን ካሪን ሽብየን አነጋግሮ እንደዘገበው ማርቲን ሽብየና ጆን ፔርሰን የአለም ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የፕሬስ አፈና ለመረዳት በመቻሉ፣ ተልኮአቸው መና እንዳልቀረ ይረዳሉ። “ጋዜጠኞቹ ንጹሀን ...
Read More »ከ200 ሺ ብር በላይ ከባንክ የሚወጣ ወይም የሚገባ ገንዘብን አስመልክቶ የተደነገገው አዲስ አዋጅ ተቃውሞና ትችት እየቀረበበት ነው
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት ፤ ከጥር 1 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ከ200 ሺ ብር ወይም ከ10 ሺ የአሜሪካን ዶላር በላይ ከባንክ የሚወጣ ወይም የሚገባ ገንዘብን አስመልክቶ ብሔራዊ ባንክ-ለፀረ-ሽብር ግብረ-ሀይል ሪፖርት ማድረግ እንዳለበት የደነገገው አዲስ አዋጅ ተቃውሞና ትችት እየቀረበበት ነው። ስማቸውን መጥቀስ ያልፈለጉ አንድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ባለሙያ በመጥቀስ ሰንደቅ እንደዘገበው፤ መመሪያው ሥራ ላይ የዋለው ኅብተሰቡን ስለ ...
Read More »አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ
ጥር 2 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግስት “ፓርላማ” ብሎ በሚጠራው የገዥው ፓርቲ አባላት ስብስብ ውስጥ ብቸኛ የተቃዋሚ ፓርቲ ተመራጭ የሆኑት አቶ ግርማ ሠይፉ፦ “ ባለፈው እሁድ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እሥረኛ ለመጠየቅ ሄጄ በፖሊስ እንዳልገባ ተከልክያለሁ” ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ። በጉዲፈቻ ወደ አሜሪካ የሚወሰዱ ልጆችን የጤና ሁኔታ ለመከታተል የሚያስችል መመሪያ ለህፃናት ሀኪሞች ተዘጋጀ፡ በጉዲፈቻ የሚወሰዱ አዳዲስ ህፃናትን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ ...
Read More »