.የኢሳት አማርኛ ዜና

የአወልያ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ዛሬ ትምህርት ጀምረዋል፣ ኮሌጁ ግን አሁንም እንደተዘጋ ነው

ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአወልያ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና እና የአወልያ ኮሌጅ ተማሪዎች  ላለፉት ተከታታይ ሳምንታት ትምህርታቸውን አቋርጠው የተለያዩ ሀይማኖታዊ መብቶችን ሲጠይቁ ነበር። ተማሪዎች መንግስት አንዳንድ ጥያቄያቸውን በመመለሱ እና ቀሪዎችን ጥያቄዎቻቸውን  በመረጡዋቸው ወኪሎች አማካኝነት ለመጠየቅ በመስማማት በዛሬው እለት ትምህርት ጀምረዋል። ተማሪዎቹ ለኢሳት እንደገለጡት ምንም እንኳ አብዛኞቹ ጥያቄዎቻቸው፣ በተለይም መጅሊስ እንዲፈርስና አህባሽን ያማስፋፋት ተልእኮው እንዲቋረጥ ያቀረቡት ጥያቄ ባይመለስም ፣ አስተማሪዎቻቸው ...

Read More »

በሳኡዲ አረቢያ በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ወደ እስር ቤት ከተጋዙት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል ሦስቱ ሞቱ

ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በሳኡዲ አረቢያ-ሪያድ ውስጥ የገናን በዓል ለማክበር በተሰበሰቡበት  በፖሊስ ቁጥጥር ውለው ወደ አስፈሪ እስር ቤት ከተጋዙት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል ሦስቱ በእስር ቤት ውስጥ መሞታቸውን በስፍራው የሚገኘው የኢሳት ወኪል ዘገበ። ዘጋቢያችን እንዳረጋገጠው፤ የገናን በዓል ለማክበር በመሰብሰባቸው  ሳቢያ ለ እስር ከተዳረጉት 35 ኢትዮጵያውያን መካከል፤ ህፃናት 29ኙ   ሴቶች ናቸው። ከነዚህ ሶቶች መካከል ብዙዎቹ የሚጠቡ ህፃናት ልጆቻቸውን በቤታቸው ትተው ...

Read More »

በመጪዎቹ 100 ዓመታት ውስጥ ይፈጸማሉ ስለተባሉት ነገሮች ምን ሰምተዋል? ይላል ቢቢሲ

ጥር 7 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት  ፕርሰን እና ቱከር የተባሉ ተምባዮች  በመጪዎች መቶ አመታት ውስጥ ምን ምን አይነት ለውጦችን ትጠብቃላችሁ ብለው ላቀረቡት ጥያቄ፣ አስተያየት ሰጪዎች የሚከተሉትን ብለዋል። ውቅያኖሶች ለአሳ ምርት ብቻ ሳይሆን የአረንጓዴ ሀይል ምርትን ለመጨመር እንዲሁም እያደገ የመጣውን ህዝብ ለመመገብ ይታረሳሉ። በድምጽ ወይም በድርጊት ሳይገልጡ ሀሳብን በማወቅ ብቻ ለመግባባት የሚያስችሉ መሳሪያዎች ይፈጠራሉ። ሳይንቲስቶች ለዘላለሙ የማይሞቱ እና እጅግ ...

Read More »

በአርባምንጭ ከተማ አንድ ለጸጥታ ስጋት ነው የተባለ የ18 ዓመት ወጣት በፖሊስ ጥይት ተበሳስቶ ተገደለ

ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የአርባምንጭ ወኪል እንደገለጠው ወጣት ደግነት ጌታቸው ታህሳስ 28 ፣ 2004 ዓም ለገና በአል ዋዜማ ከጓደኞቹ ጋር ሲዝናና በነበረበት ወቅት፣ በፖሊሶች ተገድሏል። ወጣት ደግነት  ለጸጥታ አደገኛ ነው በሚል ምክንያት ክትትል ሲደረግበት እንደነበር ዘጋቢያችን ገልጧል። የወጣት ደግነት አባት የሆኑት አቶ ጌታቸው ለኢሳት እንደተናገሩት ልጃቸው የተገደለው ምንም ጥፋት ሳያጠፋ መሆኑን ገልጠው፣ ገዳይ ፖሊሶችን ለፍርድ ለማቅረብ አቅም ...

Read More »

በሺ የሚቆጠሩ የስዊድን ጋዜጠኞች፣ የሰብአዊ መብት ተሟጋቾችና ነዋሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የስዊዲን ጋዜጠኞች እና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች እንዲሁም ከዴንማርክ፣ ፊንላንድ፣ ኖርዌይ፣  ኢትዮጵያ፣ ኢራቅ እና ኢራን የመጡ በስዊድን የሚኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። ሰልፈኞቹ የስዊድን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ያለውን ግንኙነት ለህዝብ እንዲያሳውቅ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ስልጣን እንዲለቁ፣  የመለስ መንግስት ጋዜጠኞችን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈታ እንዲሁም የስዊድን መንግስት ጋዜጠኞችን በገንዘብ ለማስፈታት የሚያደርገው ...

Read More »

በመንግስትና በኦሞ ሸለቆ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መካከል ያለው ውዝግብ እንደቀጠለ ነው

ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-መንግስት በአካባቢው የሚኖሩ በርካታ ብሄረሰቦችን በማፈናቀል ፣ መሬታቸውን ለእርሻ ልማት ማዋሉ የአካባቢውን ነዋሪዎች ማስቆጣቱን ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አስታውቋል። ንቅናቄው የቦዲ ብሄረሰብ አባላት በጭነት መኪና ቀያቸውን ለቀው ከተጋዙ በኋላ በመሬታቸው ላይ ስላላቸው መብት መንግስት እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ቢጠይቁም ምላሽ አላገኙም። ታህሳስ 28፣ 2004ዓም ወ/ሮ ቢኮሉ የተባሉ ሴት ወደ ከብቶቻቸው እየተጓዙ ባለበት ወቅት በከባድ ጭነት መኪና ...

Read More »

የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት ተቃውሞ ቀረበበት

ጥር 5 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የከተማ ቦታን አስመልክቶ የወጣው አዲስ አዋጅ ፓርላማ በተባለው የኢህአዴግ አባላት ሸንጎ ከፀደቀ በሁዋላ የአዲስ አበባ ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ በአዋጁ ዙሪያ ከነዋሪው ጋር ያደረጉት ውይይት  ተቃውሞ ቀረበበት። የአቶ ኩማ አስተዳድር ቢሊዝ አዋጁ ላይ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ በተለየ መልኩ የተስተጋባው ተቃውሞ፤ የራሱ የውይይት መድረኩn መዘጋጀቱ  ፋይዳነት ጥያቄ ውስጥ ያስገባ ነው። ምክንያት፦  የሊዝ አዋጁ ለውይይት ተብሎ ...

Read More »

በአወልያ የተጀመረውን ተቃውሞ ተከትሎ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች ለተማሪዎች እንቅስቃሴ ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ

ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአርብ ወይም የጁማን ስገደት ለመስገድ በአወልያ መስጂድ የተገኙት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሙስሊሞች፣ ከተማሪዎች ጋር በመሆን የተቃውሞ መፈክሮችን አሰምተዋል። በርካታ ሙስሊሞች በአወልያ መስጂድ ተገኝተው ስግደት መስገዳቸውን፣ ከስግደቱ በሁዋላ በአንድ ተማሪ አማካኝነት የቀረበውን መፈክር አብረው መድገማቸውን ተማሪዎች ለኢሳት ገልጠዋል። ከመፈክሮቹ መካከል ምርጫ በነጻነት ይካሄድ፣ መጂሊሱ ይፍረስ፣ የሀይማኖት ነጻነት ይከበር የሚሉ ይገኝበታል። ለስግደት የሄዱት ሙስሊሞች ተማሪዎችን ሲያበረታቱ ...

Read More »

በምእራብ ጎጃም ዜን በአዴት ወረዳ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ሰዎች ታሰሩ፣ መሳሪያ የቀሙት ወጣቶችን የማደኑ ስራ ቀጥሏል

ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወረዳው ፈቃድ በህብረተሰቡ የተገነቡ ከ500 መቶ መኖሪያ ቤቶች በላይ በቅርቡ በክልሉ መንግስት ጨረቃ ቤት ተብለው ማክሰኞ እለት በግብረ ኃይል ሊያፈርሱ የተንቀሳቀሱት የወረዳው የጥቃቅን እና እንዱስትሪ ዋና ኃላፊ አቶ ይበሉ ደሴ፣ ምክትል ኃላፊው አቶ እንድሪስ ክንዴ፣ የቤቶች ቁጥጥር ኃላፊው አቶ ገበያው ደምለው እና ፖሊስ ይልማ ተፈራ በታጣቂ ኃይል ይዘውት የመጡትን መሳሪያ ተቀምተው መመታታቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ...

Read More »

በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ላይ ሊሰጥ የነበረውን የጥፋተኝነት አሊያም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን በተለዋጭ ቀጠሮ አራዘመ

ጥር 4 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአቶ መለስ መንግሥት በእነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው 24  የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ሊሰጥ የነበረውን የጥፋተኝነት አሊያም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን ለጥር 14 ቀን 2004 ዓ.ም በጊዜ ተለዋጭ ቀጠሮ አራዘመ፡፡ በዳኛ እንደሻው አዳነ፣ ሙሉጌታ ኪዳኔ ...

Read More »