.የኢሳት አማርኛ ዜና

የኢትዮጵያ ህዝብና ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች ጎን በመቆም ቃል-ኪዳናቸውን እንዲያድሱ የኢት ዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ማህበር ጥሪ አቀረበ

ጥር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደት የሚገኘው ኢነጋማ፦”በጠመንጃ አስገዳጅነት የእውነት እጆች ቢታሰሩም፤ ታሪክና ህዝብ ግን ይፈርዳል” በሚል ርዕስ ባወጣው መግለጫ ፤በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ የሆነ አስተሳሰብ እንዲነግስ፤ በተለይ የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞች ታላቁን ሚና መጫዎታቸውን እንዲሁም፤ ሃሳብን በነጻነት መግለጽ ፤ተፈጥሯዊና  በኢትዮጵያዊያን የትግል ውጤት የተገኘ እንጂ፤ የኢህአዴግ ችሮታና ስጦታ እንዳልሆነ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ማሰማታቸውን አስታውሷል  አልፎ ተርፎም  ስልጣን ከጠመንጃ ውስጥ በሚወጣ ...

Read More »

ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለአንዲት ኢትዮጵያ ለመታገል የወሰነው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የግንቦት 7 ንቅናቄ በሚኒሶታ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ያደርጋሉ

  ጥር 18 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከኢትዮጵያውያን ጋር በጋራ ለ አንዲት ኢትዮጵያ ለመታገል የወሰነው የ ኦሮሞ ነፃነት ግንባርና የግንቦት 7 ለፍትህ፣ለነፃነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ በመጪው ፌብሩዋሪ ወር በሚኒሶታ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርጉ ዘ-ሀበሻ ዘገበ። በኦነግ የሰሜን አሜሪካ አስተባባሪና የህግ አማካሪ የሆኑትን ዶክተር ነሩ ደደፎን በመጥቀስ ዘ-ሀበሻ እንደዘ ገበው  በመቺው ወር አጋማሽ በሁለቱ ድርጅቶች መካከል የሚካሄደው ታላቅ ስብሰባ ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ያካተተ ...

Read More »

የፌዴራል ዐቃቤ- ህግ በእነ አንዱአለም አራጌና እስክንድር ነጋ ላይ ብይን ሰጠ

ጥር 16ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በህጋዊ ፓርቲ ጥላ ስር ተከልለው የመንግሥት ባለስልጣናትን ለመግደል፣ መሠረተ ልማቶችን ለማውደም እና ከአሸባሪ ቡድኖች ጋር አንድ ላይ በማበር ሕገመንግሥቱንና ሕገመንግሥታዊውን መንግስት ለመገልበጥ በሀገር ውስጥና በውጭ አገራት አሲረው ተንቀሳቅሰዋል ሲል የከሰሳቸው 24 የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት ትናንት የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል:: ዘጋቢያችን እንደገለጠው ...

Read More »

በርካታ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጄኔራል ከማል ገልቹ የሚመራው ኦነግ የወሰደውን እርምጃ እንደደገፉት ዘጋቢያችን ገለጠ

ጥር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባው ወኪላችን እንደገለጠው፣ በርካታ የኦሮሞ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በጄነራል ከማል የሚመራው ኦነግ፣ የመገንጠል አጀንዳን ሰርዞ ኢትዮጵያን አሁን ካለችበት አሳዛኝ ሁኔታ አላቆ፣ አገሪቱዋን ለመምራት የወሰደውን እርምጃ አድንቀዋል። ለደህንነቱ ሲባል ስሙን መግለጽ ያልፈለገ አንድ የኦነግ ደጋፊ እንደገለጠው ፤ አለም ወደ አንድ እየተቀራረበች በመጣችበት ጊዜ እና በአሁኑ አለም ህልውናን ጠብቆ ለመኖር አንድነት ከመቼውም ጊዜ በላይ ...

Read More »

በአፋር ክልል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኡመድ አፋሶ አሊ፤ ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው በዋስ መፈታታቸው ተዘገበ

ጥር 16 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአፋር ክልል የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ  ዋና ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ኡመድ አፋሶ አሊ፤ ከሚኖሩበት አዋሽ ፈንታሌ ወረዳ- አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተማ ወደሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ ተወስደው  በ5 ሺህ ብር ዋስ መፈታታቸውን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ።   ከድርጅቱ ጽ/ቤት የደረሰውን መረጃ በመጥቀስ ጋዜጣው እንደዘገበው አቶ ኡመድ ከመኖሪያ ቤታቸው ወደፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱት ባለፈው ቅዳሜ ነው።  አቶ ኡመድ፦“ ለምንድነው ያሰራችሁኝ?” በማለት ...

Read More »

በደሴ የሚኖሩ ከ7 ሺ በላይ ሙስሊሞች የአህበሻን አስተምህሮ፣ የመንግስትን ጣልቃ ገብነትና መጅሊሱን ተቃወሙ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በከተማዋ የሚኖሩ ሙስሊሞች በዋናው መስጊድ ግቢ በመገኘት መንግስት በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም፣ መጅሊሱ ወይም የእስልምና ጉባኤው ሙስሊሙን የማይወክል በመሆኑ እንዲፈርስ እንዲሁም የአህባሽ አስተምህሮ እንዲቋረጥ ጠይቀዋል። የመንግስት ባላስልጣናት ሙስሊሞቹ ተወካዮቻቸውን መርጠው እንዲነጋገሩ ባሳሰቡት መሰረት 50 ተወካዮች ከሰአት በሁዋላ የዜን የጸጥታ ሀላፊ፣ የዞን አስተዳዳሪ፣ የደሴ ከተማ እና ሌሎችም 9 ባለስልጣኖች ባሉበት ውይይት ተካሂዷል። የዞኑ ...

Read More »

አልሸባብ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የሶማሊያ ታጣቂ ሀይል የሆነው አልሸባብ እንደገለጠው ጥቃቱን የፈጸመው በለደወይን እየተባለች በምትጠራ የሶማሊያ ግዛት ነው። የኢትዮጵያ ጦር ባለፈው ወር ከተማዋን ከአልሸባብ በመንጠቅ የተቆጣጠራት ሲሆን፣ ለአፍሪካ ህብረት ሰራዊት ለማስረከብ በዝግጅት ላይ ነበር። ታጣቂ ሀይሉ ጥቃቱን የፈጸመው አንድ አጥፍቶ ጠፊ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሰፈሩበት ካምፕ በመሄድ በፈጸመው ጥቃት ነው። የአይን እማኞች እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች የሚኖሩበት ህንጻ ክፍሎች ...

Read More »

የእስራኤል ፕሬዝዳንት ለኢትዮጵያዊያን ቤተ እስራኤላዉያን የዘፈን ግጥም ደረሱ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያዊ  ቤተ እስራኤላዉያን ላይ የደረሰዉ የዘር መድልዎ የተሰማቸዉ የእስራኤል ፕሬዝዳንት ሺሞን ፔሬዝ አንድ የዘፈን ግጥም በመድረስ እዉቁ የእስራኤል የዜማ ደራሲ እንዲያቀናብረዉ ማድረጋቸዉን አንድ የእስራኤል ጋዜጣ ገለፀ። ፕሬዝዳንቱ ግጥሙን ያዘጋጁት በቅርቡ በእየሩሳሌም በሚገኝ ትምህርት ቤት ዉስጥ ባደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያዊያን ሕፃናት እስራኤላዊ ከሆኑ የህብረተሰቡ ህፃናት ጋር ያላቸዉ የቅርብ ትስስርና ዉህደት በመመልከታቸዉ ነዉ። በተለይም የ8ኛ ክፍል ተማሪ ...

Read More »

ግዳጃቸዉን የፈፀሙ የአገር መከላከያ ሠራዊት አባላት በደል እንደደረሰባቸዉ ገለፁ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በደቡብ ክልል በአዋሳ ከተማ ከአገር መከላከያ ሠራዊት ግዳጃቸዉን ፈጽመዉ በክብር የተሰናበቱ ተራ ወታደሮች ወደ ትውልድ ስፍራቸዉ ተመልሰዉ የቤት መስሪያ ቦታ ወይንም የኮንዶሚኒየም ቤት ለመግዛት ቅድሚያ እንዲሰጣቸዉ ያቀረቡት ጥያቄ በክልሉ ባለስልጣናት ተቀባይነት ማጣቱን በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ በሰፈረ ብሶት ተገለፀ።  የክልሉ መስተዳድር፤ የክልሉ ቤቶች የልማት ኤጀንሲ፤ የቤቶች ልማት ቦርድ የወታደሮቹን ጥያቄ ዉድቅ አድርገዉ በምትኩ   የኮንዶሚኒየሙ ቤት ...

Read More »

መንግሥት በነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በከሰሳቸው ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ብይን የመስጠት ሂደቱን ለሌላ ጊዜ አሻገረ

ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ሦስተኛ ወንጀል ችሎት መንግሥት በነ አንዷለም አራጌ የክስ መዝገብ በአሸባሪነት ወንጀል በከሰሳቸው የፖለቲካ ፓርቲ የአመራር አባላት፣ ጋዜጠኞች እና ነፃ አሳቢ ዜጎች ላይ ለሁለተኛ ጊዜ ብይን የመስጠት  ሂደቱን በጊዜ አሻገረ፡፡ ዛሬ ጠዋት 3፡00 ሰዓት ላይ የነ አንዷለም አራጌን የክስ መዝገብ ተመልክቶ የጥፋተኝነት ወይም ከጥፋት ነፃ የመሆን ብይን ይሰጣል ተብሎ ...

Read More »