አልሸባብ 10 የኢትዮጵያ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ

ጥር 15 ቀን 2004 ዓ/ም

ት ዜና:-የሶማሊያ ታጣቂ ሀይል የሆነው አልሸባብ እንደገለጠው ጥቃቱን የፈጸመው በለደወይን እየተባለች በምትጠራ የሶማሊያ ግዛት ነው።

የኢትዮጵያ ጦር ባለፈው ወር ከተማዋን ከአልሸባብ በመንጠቅ የተቆጣጠራት ሲሆን፣ ለአፍሪካ ህብረት ሰራዊት ለማስረከብ በዝግጅት ላይ ነበር።

ታጣቂ ሀይሉ ጥቃቱን የፈጸመው አንድ አጥፍቶ ጠፊ የኢትዮጵያ ወታደሮች ወደ ሰፈሩበት ካምፕ በመሄድ በፈጸመው ጥቃት ነው።

የአይን እማኞች እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች የሚኖሩበት ህንጻ ክፍሎች በጥቃቱ ተደረማምሰዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ስለተገደሉት ወታደሮች የሰጠው መግለጫ የለም።