.የኢሳት አማርኛ ዜና

ድህነት መቀነሱን የሚያሳይ በገልለልተኛ ወገን እስካልተሰራ ድረስ ተቀባይነት የለውም ተባለ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳምንት በፊት የአቶ መለስ ዜናዊ ባለቤት በተገኙበት አንድ ጉባኤ ላይ የገንዘብ ሚኒስቴር ያስጠናው የድህነት ቅነሳ ሪፖርት ይፋ መሆኑ ይታወሳል። ጥናቱ ድህነት በኢትዮጵያ በከፍተኛ ደረጃ እየቀነሰ መሄዱን የሚያመለክት ሲሆን፣ የመንግስት የመገናኛ ብዙሀንም ዜናውን ተፈላጊው ህዝብ ዘነድ ለማዳረስ ሲደክሙ ሰንብተዋል። ይሁን እንጅ ገለልተኛ ባለሙያዎች የጥናቱን ተአማኒነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት ሀሳቦችን በመሰንዘር ላይ ናቸው። አንድ ስማቸው ...

Read More »

የአለማችን ቱጃር ቢልጌትስ ኢትዮጵያን ጎበኙ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የማይክሮሶፍት ባለቤትና ለበርካታ አመታት አለማችን ቁጥር አንድ ሀብታም ሆነው የቆዩት አሜሪካዊው ቢል ጌትስ ለመጀመሪያ ጊዜ ኢትዮጵያን የጎበኙት ቢል እና ማሊንዳ ፋውዴሽን የተባለው ድረጅታቸው የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለመጎብኘት ነው። ቢል ጌትስ ኢትዮጵያ በጤናው መስክ ያስመዘገበችውን ስራ የሚመሰገን ቢሆንም፣ ብዙ መሰራት እንዳለበትም ተናግረዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ቢል ጌትስ የአውሮፓ መንግስትታት ለታዳጊ አገሮች የሚሰጡትን እርዳታ እንዳይቀንሱ እየተማጸኑ ...

Read More »

“አርቲስቶች በዓባይ ግድብ ግንባታ ላይ አንድም ነገር መሥራት አልቻልንም” አሉ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አርቲስቶችን በመወከል  በህዳሴው ግድብ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆኖ  እንዲሳተፍ የተደረገው ሠራዊት ፍቅሬ ይህን ያለው፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ  አርቲስቶች ለዓባይ ግድብ ግንባታ ህብረተሰቡ ያለማቋረጥ እንዲረባረብ በማድረግ በኩል ስለሠሩትና እየሠሩት ስላለው ሥራ ያብራራ ዘንድ በተጠየቀበት ጊዜ ነው። ሠራዊት ለጥያቄው በሰጠው መልስ፦”አርቲስቶች በ ዓባይ ልማት ዙሪያ የተለያየ አስተዋጽኦ ለማበርከት ወንዙ ድረስ ሄደን ቃል ገብተን ...

Read More »

መምህራን የአቋም መግለጫ አወጡ ፒቲሽንም ተፈራረሙ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአዲስ አበባ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች የሚያስተምሩ መምህራን የአቋም መግለጫ በማውጣት እና ፒቲሽን በመፈረም ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት ተቃውሟቸውን በማሳወቅ ሥራቸውን በያዝ ለቀቅ ትላንት መጀመራቸውን ሪፖርተራችን ያናገራቸው መምህራን ገለጹ፡፡  የአዲስ አበባ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ትምህርት ቢሮዎች መምህራኑን በስብሰባና በማስፈራራት ሊያደርጉት የነበረው የአቋም ማስቀየሪያ ፖለቲካዊ የኢህአዴግ አሻጥር አልተሳካም በማለት መምህራኑ ለዘጋቢያችን አስረድተዋል፡፡ የየትምህርት ...

Read More »

መንግሥት በሙስሊሙ ጥያቄ ፖለቲካዊ ትርፍ ሊያገኝበት በሚችልበት መንገድ ለመፍታት እየሞከረ ነው ተባለ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በአቶ መለስ ዜናዊ የሚመራው የኢህአዴግ መንግሥት የሕዝበ ሙስሊሙን የመጅሊስ ይውረድ፣ የአህባሽ አስተምህሮ በግዳጅ ላያችን ላይ አይጫንብን እና በሃይማኖታችን ላይ የመንግሥት ጣልቃ ገብነት ይቁምልን ጥያቄን ፖለቲካዊ ትርፍ ሊያገኝበት በሚችልበት መንገድ ለመፍታት እየሞከረ እንደሆነ ምንጮች አስታወቁ፡፡  በአቶ በረከት ስምዖን የሚመራው ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት፣ በፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤትና ከደህንነት በተሰባሰበ መረጃ ቀደም ሲል በኢህአዴግ መንግሥት ...

Read More »

የተለጣፊው የኦብኮ ሊቀመንበር በፖሊሶችና በተበዳዮች ርብርብ በቁጥጥር ሥር ዋሉ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የተለጣፊው የኦሮሞ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ (ኦብኮ) ሊቀመንበር የነበሩት አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ፤ በትናንትናው ዕለት በሳንፎርድ ትምህርት ቤት አካባቢ በፖሊሶችና በተበዳዮች ርብርብ በቁጥጥር ሥር ዋሉ፡፡  አስር አለቃ ቶሎሳ ተስፋዬ፤መንግስት  በምርጫ 97 ወቅት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ በመውጣት ወደ 40 የሚጠጉ የፓርማ መቀመጫዎችን ያገኘውንና  በዶክተር መረራ ጉዲና የሚመራውን  ኦብኮ ለማፍረስ ሢንቀሳቀስ፤ በዋነኝነት የተጠቀመባቸው  የፓርቲው አባል ...

Read More »

አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በአርቲስታ ታማኝ በየነ ዙሪያ ምሬት የተሞላበት ንግግር አደረጉ

መጋቢት ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ፤ በአርቲስታ ታማኝ በየነ ዙሪያ ምሬት የተሞላበት ንግግር አደረጉ። በደቡብ አፍሪካ ጆሀንስበርግ ተገኝተው ከኢትዮጵያውያን ጋር ታላቅ ስብሰባ ለማድግ ቢያቅዱም፤ በስብሰባው 27 ሰዎች ብቻ በመገኘታቸው፤ በአንፃሩ አርቲስት ታማኝ በየነ እና ዶክተር ብርሀኑ በቴሌ ኮንፈረንስ በመሩት ስብሰባ ላይ በጆሀንስበርግ የሚኖሩ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን በመሳተፋቸው ክፉኛ ...

Read More »

በአርባምንጭ መምህራን የተቃውሞ አድማ አድርገዋል፣ 5 መምህራን የደረሱበት አልታወቀም

መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- የኢሳት የአርባምንጭ ዘጋቢ እንደገለጠው ሀይሌ ደጋጋ እየተባለ በሚጠራው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ተከትሎ ተማሪዎች የመምህራን ድምጽ ይሰማ የሚል ተቃውሞ በማሰማታቸው የፌደራል ፖሊስ በሰፍራው ደርሶ በርካታ ተማሪዎችን ደብድቧል። የፌደራል ፖሊስ እርምጃውን የወሰደው ተማሪዎች የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ከግቢ ለመውጣት ሲዘጋጁ በነበረበት ወቅት ሲሆን፣ ተማሪዎች በፌደራል እርምጃ በመበሳጨት በድንጋይ ለመከላከል ሞክረዋል። ...

Read More »

የዋልድባ ገዳም ምእመናን በገዳሙ ዙሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ለማድረግ ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል

መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- በዋልድባ ገዳም ዙሪያ የሚካሄደው የስኳር ልማት ለገዳሙ ህልውና አደጋ ደቅኗል ያሉ ምእመናን በገዳሙ ዙሪያ ከፍተኛ ተቃውሞ ለማድረግ ዝግጅታቸውን ቀጥለዋል። የተቃውሞው መጠን ያሰጋው መንግስት ሰሞኑን በአካባቢው ያሉ ከ300 በላይ የኢህአዴግ ካድሬዎችን ሰብስቦ ተቃዋሚዎች ከፍተኛ የሆነ የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ መክፈታቸውን ገልጦ፣ የዋልድባ ገዳምን ሰበብ አድርገው የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚሞክሩትን እንዲቆጣጠሩ መመሪያ ተሰጥቷቸዋል። ይሁን እንጅ አንድ በስብስባው ...

Read More »

አንዱአለም አራጌና ሌሎች እስረኞች የመከላከያ መስክሮቻቸውን በማቅረብ ላይ ናቸው

መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ/ም ኢሳት ዜና:- ትናንት እና ዛሬ በሶስተኛ ወንጀል ችሎት ጠባብ አዳራሽ በተካሄደው የመከላከያ ምስክሮችን የመስማት ሂደት ተከሳሾች በመከላከያ ምስክርነት ያቀረቡዋቸው ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ዶ/ር ሀይሉ አርአያ እና አቶ ሙለቱ ጣሴ ቀርበው መመስከራቸው ታውቋል። ችሎቱ በጠባብ አዳራሽ የተካሄደ በመሆኑ በጣም ጥቂት ሰዎች ብቻ በመታደማቸውን ለማወቅ ተችሎአል። ይህ በእንዲህ እንዳለ በሱዳን በስደተኝነት ከሚኖርበት አገር ታፍኖ ተወስዶ በእስር ላይ ...

Read More »