“አርቲስቶች በዓባይ ግድብ ግንባታ ላይ አንድም ነገር መሥራት አልቻልንም” አሉ

መጋቢት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አርቲስቶችን በመወከል  በህዳሴው ግድብ የብሔራዊ ምክር ቤት አባል ሆኖ  እንዲሳተፍ የተደረገው ሠራዊት ፍቅሬ ይህን ያለው፤ ሰሞኑን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ቀርቦ  አርቲስቶች ለዓባይ ግድብ ግንባታ ህብረተሰቡ ያለማቋረጥ እንዲረባረብ በማድረግ በኩል ስለሠሩትና እየሠሩት ስላለው ሥራ ያብራራ ዘንድ በተጠየቀበት ጊዜ ነው።

ሠራዊት ለጥያቄው በሰጠው መልስ፦”አርቲስቶች በ ዓባይ ልማት ዙሪያ የተለያየ አስተዋጽኦ ለማበርከት ወንዙ ድረስ ሄደን ቃል ገብተን ነበር፤እስካሁን ግን ምንም የሠራነው ሥራ የለም” ብሏል።

የህዳሴው ግድብ መሰረቱ እንደተጣለ በተነገረ ማግስት በኢህአዴግ ጽህፈት ቤት ሀላፊ በ አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ በህዳሴው ምክር ቤት አባል በአቶ ሠራዊት ፍቅሬ እና  በሙሉዓለም ታደሰ  የልዑክ ቡድን መሪነት  በርካታ አርቲስቶች ግንባታው ይካሄድበታል ወደተባለው ስፍራ በቱሪስት አውቶቡስ በመጓዝ፤በዓባይ ላይ ፎክረውና ዝተው መምጣታቸው አይዘነጋም።

ዓባይን ለመገደብና ድህነትን በታሪክነት ለማስቀረት በሚደረገው ትግል በሙያቸው ከፊት ተርታ ተሰልፈው አስፈላጊውን ሁሉ ለማድረግ አቶ ሠራዊት ፍቅሬና  ሙሉዓለም ታደሰ አርቲስቶቹን ወክለው ቃል ሲገቡ፤ የሚባክን ጊዜ እንደሌለና በቶሎ ወደ ተግባር ለመግባት መዘጋጀታቸውን ገልጸው ነበር።

ይሁንና “የግድቡ ሥራ ተጀምሯል” ከተባለ አንድ ዓመት እየተቃረበ ባለበት ጊዜ ነው  ሰሞኑን  በኢቲቪ የቀረበውረ ሠራዊት ፦” ቃል ብንገባም፤ ምንም የሠራነው ሥራ የለም” ያለው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide