.የኢሳት አማርኛ ዜና

የተለያዩ የፖለቲካ እና የሲቪክ ድርጅቶች የጋራ የትግል ሸንጎ መሰረቱ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የተለያዩ የፖለቲካ እና ሲቪክ ማህበራትን በማካተት ከግንቦት10 እስከ 13 በካናዳዋ ዋና ከተማ ኦታዋ በተደረገው ጉባኤ ፣ በአሁኑ ወቅት በስልጣን ላይ የሚገኘውን የህወሀት/ ኢህአዴግን መንግስት ለመታገልና የኢትዮጵያን ህዝብ የስልጣን ባለቤት ለማድረግ ላለፉት 2 አመታት በተደረገው ጥረት ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ” የተባለ ህብረት መመመስረቱን ባወጣው መግለጫ ላይ ጠቅሷል። ህብረቱን ከፖለቲካ ድርጅቶች የኢትዮጵያ ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚገኙ የጋዜጦችና የመጽሔቶች አሳታሚዎች ኢፕአማ የተሰኘ ማህበር ለማቋቋም ከስምምነት ላይ ደረሱ

ግንቦት ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኢትዮጵያ የሚገኙ የጋዜጦችና የመጽሔቶች አሳታሚዎች የመንግሥትን ኢፍትሃዊ ጫና ለመቋቋም “የኢትዮጵያ ፕሬስ አሳታሚዎች ማህበር” (ኢፕአማ) የተሰኘ  ማህበር ለማቋቋም በመሠረታዊ ሃሳቡ ላይ ትናንት ከሥምምነት ላይ መድረሳቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡ ትናንት ረቡዕ ግንቦት 15 ቀን 2004 ዓ.ም በአቶ አማረ አረጋዊ “ሆርን ኦፍ አፍሪካ ፕረስ ኢንስቲቲዩት” ቢሮ የተሰባሰቡት አሳታሚዎች በቅርቡ በብርሃንና ሰላም እና ቦሌ ማተሚያ ቤት የወጣውን ...

Read More »

የአንድ ለአምስት ፖለቲካዊ አደረጃጀት ወደ መንግስት መ/ቤቶች እየዘለቀ ነው

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል የገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ሠራተኞቹን አንድ ለአምስት በሚል አደረጃጀት በማዋቀር በሥራ ሰዓት ጭምር ስብሰባዎችን በማካሄድ ሠራተኛው እርስ በርስ እንዳይተማመን የማድረግ አሠራር ተግባራዊ በማድረጉ በሥራ ዋስትናቸው ላይ ከፍተኛ አደጋ መጋረጡን አንዳንድ ሠራተኞች አስታውቀዋል፡፡ ባለሥልጣኑ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የልማት ሠራዊት ለመገንባት በሚል ሠራተኛው አንድ ለአምስት እንዲደራጅና በየዕለቱ ከ30 ደቂቃ ላላነሰ ግዜ በቀኑ ውስጥ ባጋጠሙ ...

Read More »

ከሊዝ አዋጁ ጋር ተያይዞ በአዲስ አበባ የማዘጋጃ ቤት ገቢ በግማሸ አሸቆለቆለ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በ2004 ዓ.ም  10 ወራት ከማዘጋጃ ቤት ያገኘው ገቢ በግማሸ ማሸቆልቆሉን የኢሳት ምንጮች ገለጸዋል፡፡ አስተዳደሩ በተለይ በዋንኛነት ከሊዝና ከስም ዝውውር ጋር በተያያዘ ከሐምሌ 1 ቀን 2003 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ባሉት 10  ወራት 726 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ለማግኘት ያቀደ ቢሆንም ማሳካት የቻለው 363 ነጥብ 3 ...

Read More »

የአሜሪካ የምክር ቤት አባላት የመለስ መንግስት የፕሬስ ነጻነትን ጨምሮ የዜጎችን መብት እንዲያከብር ጠየቁ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የቀድሞው የአፍሪካ ጉዳዮች ሊቀመንበርና አሁን ሽብርተኝነትን፣ አውዳሚ የጦር መሳሪያን እና ንግድን የሚመለከቱ ጉዳዮችን የሚመለከተውን ኮሚቴ የሚመሩት  ኤድዋርድ ሮይሲ ለአቶ መለስ ዜናዊ በጻፉት ደብዳቤ ፣ በእስር ላይ ስለሚገኙት ጋዜጠኞችና የፖለቲካ እስረኞች እንዲሁም በአገሪቱ ውስጥ ስላለው የፕሬስ አፈና ያላቸውን ስጋት ገልጠዋል። ያለ ፕሬስ ጠንካራ የሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርአት መገንባት እንደማይቻል የገለጡት ሮይስ፣ በአገር ደህንነትና ሽብርተኝነትን ...

Read More »

ሚኒስትሩን የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትሩን ስብሰባ ላይ የዘለፈችው ሙስሊም ወጣት፤ በደህንነቶች በደረሰባት አሰቃቂ ድብደባ ህይወቷ ማለፉ ተነገረ። ይህ አሳዛኝ ዜና ይፋ የሆነው፤የብዙሀኑ ሙስሊም አስተባባሪ  አካል የሆነው “ድምፃችን ይሰማ” ኮሚቴ ፦አሳዛኝ የግፍ ዜና”በሚል ርዕስ ያሰራጨው መረጃ  ነው። በቅርቡ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስቴር የሙስሊሞችን ጥያቄ በተመለከተ ከየክፍለ-ከተማው ሰዎችን በመምረጥ ስብሰባ አካሂዶ እንደነበር ያወሳው ኮሚቴው፤በዚሁ ስብሰባ ላይ ከኮልፌ ...

Read More »

አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አይወክሉንም ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያን ተቃውሞ አሰሙ

ግንቦት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “በኢትዮጵያ -የደቡብ ሱዳን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሚስተር  አሮፕ ዴንግ ኩኦል እኛን አይወክሉንም” ሲሉ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ደቡብ ሱዳናውያን  ተቃውሞ አሰሙ። ደቡብ ሱዳናውያኑ የአምባሳደር አሮፕን ሹመት የማይቀበሉት  ከአገራቸው ብሔራዊ ጥቅም አኳያ ብቻ ሳይሆን፤የቪየና ኮንቬንሽን የዲፕሎማቲክ ግንኙነት ስምምነትን የጣሰ በመሆኑም ጭምር በመሆኑ ነው ማለታቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል። የአምባሳደሩ ሹመት የቪየናን ኮንቬንሽን እንደሚጥስ ከተጠቀሱት ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በዋልድባ ከፍተኛ ሰራዊት በማሰማራት አካባቢውን ማረስ መጀመሩ ህዝቡን አስቆጣ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ዋልድባ አካባቢ የሚገኙ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ባለፉት ስድስት ቀናት በርካታ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ወደ አካባቢው በመሄድ የሰፈሩ ሲሆን፣ የመከላከያ ሰራዊቱን መስፈር ተከትሎ  አካባቢው መታረስ መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል። የአካባቢው ህዝብ መከላከያ ሰራዊቱ ጋር ተፋጦ የሚገኝ ቢሆንም እስካሁን ድረስ የተፈጠረ ግጭት የለም። አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ ሰው  የአካባቢው ህዝብ በመንግስት ድርጊት በእጅጉ ማዘኑን ገልጠው፣ ...

Read More »

ሚኒሰትሩ የጋምቤላ ችግር የእርስ በርስ ሽኩቻ ውጤት ነው አሉ

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከግንቦት 10 እስከ 12 የፌደራል ከፍተኛ ባለስልጣናት በተገኙበት በጋምቤላ በተደረገው  ስብሰባ ላይ የፌደራል ጉዳዮች ሚኒሰትር የሆኑት አቶ ሺፈራው ተክለማርያም  ” የክልሉ ችግር የእርስ በርስ የስልጣን ችኩቻ የወለደው ነው ” ብለዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በጋምቤላ ሰላም በመጥፋቱ በርካታ ነዋሪዎች ቤት ንብረታቸውን እየጣሉ ወደ ደቡብ ሱዳን ተሰደዋል፤ የክልሉን ጸጥታ የማስጠበቅ ስራ ለፌደራል ፖሊስና ለመከላከያ ...

Read More »

በመተከል ለረጅም አመታት የቆዩ ህዝቦች ከአካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እየተደረገ ነው

ግንቦት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በመተከል ዞን -ዳንጉር ወረዳ ውስጥ ለእርሻ ሥራ ሄደው  ለረጅም አመታት የቆዩ የአማራና የአገው ብሔር ተወላጆች በክልሉ ካድሬዎች ለጅምላ እስራት ከመዳረጋቸውም በላይ ካለምንም ቅድመ ሁኔታ አካባቢውን ለቀው እንዲሄዱ እየተደረገ መሆኑን ፍኖተ-ነጻነት ዘገበ። በተጠቀሰው አካባቢ  የአማራና የአገው ተወላጆች ለጅምላ እስራት መዳረጋቸውን ተከትሎ የወረዳው የሃይማኖት አባት ሰዎቹ የታሰሩበት እስር ቤት ድረስ በመሄድ፦ “ወዶ አማራና አገው ...

Read More »