z-Advert

የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 12/2010) የወለጋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው መውጣታቸው ተገለጸ። የአካዳሚክና የደህንነት ጥያቄዎችን በማቅረብ ምላሽ ሲጠብቁ የነበሩት ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው የወጡ ሲሆን አብዛኞቹ ወደየቤተሰቦቻቸው መመለስ መጀመራቸው ታውቋል። በተለይም በዩኒቨርሲቲው ግቢ የተደራጀው የህወሀት የስለላ መዋቅር ለደህንነት ስጋት መሆኑ ተጠቅሷል። ሰሞኑን በተመሳሳይ ከቡሌ ሆራና ከመቱ ዩኒቨርስቲዎች አብዛኞቹ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው ከግቢያቸው መውጣቸው የሚታወስ ነው። በወለጋ ዩኒቨርስቲ ነቀምት ካምፓስ የሚገኙ ተማሪዎች በደህንነት ...

Read More »

የ10ኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑ ቁጥራቸው ያልታወቀ ወታደሮች ከነመሳሪያቸው ተሰወሩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 12/2010)በደቡብ ኢትዮጵያ ሞያሌ አካባቢ የሰፈረው 10ኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑ ቁጥራቸው ያልታወቀ ወታደሮች ከነመሳሪያቸው ትላንት መሰወራቸው ታወቀ። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የተሰወሩበትን ወታደሮች ለማግኘት ዛሬ ረፋድ ላይ የተጀመረው ፍለጋ መጠናከሩና ኬንያ ድንበር መድረሱም ተመልክቷል። በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የ10ኛ ክፍለ ጦር 1ኛ ብርጌድ ውስጥ ከሚገኙ ሶስት ሻለቃዎች ከአንዱ የተውጣጡትና ለጊዜው ቁጥራቸው ያልታወቀው ወታደሮች ለአሰሳ የወጡት ትላንት ሰኞ ህዳር 11/2010 ከሰአት ...

Read More »

የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን እንዲለቁ እስከ ሰኞ እኩለቀን ቀነ ገደብ ተቀመጠ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010)የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ስልጣናቸውን እንዲለቁ እስከ ሰኞ እኩለቀን ቀነ ገደብ መጣሉ ታወቀ። ፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ኤፍ እሁድ ባደረገው ስብሰባ ሙጋቤን ከፓርቲው መሪነት ሲያስወግድ ባለቤታቸውን ደግሞ ማባረሩ ታውቋል። እስከ ዛሬ ሰኞ ድረስ ስልጣናቸውን እንዲለቁ በፓርቲያቸው የጊዜ ገደብ የተሰጣቸው የዚምባቡዌው ፕሬዝዳንት ሮበርት ገብርኤል ሙጋቤ ትላንት እሁድ በቴሌቪዥን ቀርበው በያዙት ስልጣን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል። ፓርቲያቸው ዛኑ ፒ ኤፍ በሚቀጥለው የአውሮፓውያኑ ወር የሚያደርገውን ጉባኤ ...

Read More »

አቶ በረከት ስምኦን ሁሉም ብሔረሰብ የራሱን ክልል እያስተዳደረ የሚገኝበት የእኩልነት ስርአት ገንብተናል አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010) በጎንደር ከተማ በተካሄደው የአማራና የትግራይ ተወላጆች የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት አቶ በረከት ስምኦን ሁሉም ብሔረሰብ የራሱን ክልል እያስተዳደረ የሚገኝበት የእኩልነት ስርአት ገንብተናል ሲሉ ተነገሩ። በዚሁ መድረክ ኢሳትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተወግዘዋል። የአማራ ተወላጆች ልጆቻቸው ለተቃውሞ አደባባይ እንዳይወጡ ይሰበስቡ ዘንድም ጥሪ ቀርቦላቸዋል። “አብሮነታችን ለሰላማችን” በሚል መሪ ቃል በጎንደር ባለፈው ቅዳሜ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ጽሁፍ ያቀረቡት አቶ በረከት ስምኦን ...

Read More »

የብአዴን ነባር ታጋዮች በንቅናቄው 37ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ሳይገኙ ቀሩ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010) የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ብአዴን ነባር ታጋዮች በንቅናቄው 37ኛ ዓመት ክብረበዓል ላይ ሳይገኙ መቅረታቸው ተገለጸ። በግብርና ስራ የተሰማሩና በኑሮ የተጎሳቆሉት የቀድሞ የንቅናቄው ታጋዮች ዛሬ የታወስንበት ምክንያት ሊገለጽልን ይገባል የማለት ተቃውሞ ማቅረባቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ብአዴን የተመሰረተበትን 37ኛ ዓመት ሲያከብር በመርሃግብር ከያዛቸው መርሃ ግብሮች አንዱ ለንቅናቄው ነባር ታጋዮች እውቅናና የምስክር ወረቀት መስጠት ነበር። ይሁንንና የትም ወድቀው የቀሩና ብዙዎች ...

Read More »

የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግቢያቸውን ለቀው ወጡ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010)የቡሌ ሆራ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዛሬ ግቢውን ለቀው መውጣታቸው ታወቀ። ለአንድ ሳምንት ትምህርት አቁመው ጥያቄያቸው እስኪመለስ ቢጠብቁም ምላሽ ባለማግኘታቸው ግቢውን ሙሉ በሙሉ ለቀው ለመውጣት ተገደዋል። በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ የታጠቁ የልዩ ሃይል አባላት ወደ ግቢው ዘልቀው በመግባት ተማሪዎችን እየደበደቡ መሆናቸውም ታውቋል። በመቱ ዩኒቨርሲቲ ግቢውን ለቀው የወጡ ተማሪዎች አልተመለሱም። በግቢው የቀሩትም ትምህርት አለመጀመራቸው ታውቋል። ከአንድ ሳምንት በላይ ትምህርት አቋርጠው የቆዩ የቡሌ ሆራ ...

Read More »

ሜቴክ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ ነው

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010)ሜቴክ በአቶ አርከበ እቁባይ ትዕዛዝ ከኦሮሚያ ክልል በህገወጥ መንገድ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ እንደሆነ በፓርላማ ተገለጸ። ጥሬ ሐብቱ እየተበዘበዘበት ያለው ህዝብም ተቃውሞውን በማሰማት ላይ ነው። በሕወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የሚመራው የኢትዮጵያ ብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን /ሜቴክ/በሕግ ከተቋቋመበትና ከተሰጠው ስልጣን ውጪ ከኦሮሚያ የድንጋይ ከሰል በማውጣት እየሸጠ መሆኑ የፓርላማ ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንዳሳሰባቸው ተናግረዋል። የመንግስት ልማት ድርጅቶች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ...

Read More »

የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም አሉ

(ኢሳት ዜና–ሕዳር 11/2010) በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 4ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ የቀረቡት የወልቃይት አማራ የማንነት አስመላሽ ኮሚቴ አባላት በግራ ዳኛው መዳኘት አንፈልግም ሲሉ ተቃውሞአቸውን አሰሙ። ሌሎች በችሎቱ የነበሩ ተከሳሾችም የመንግስትን አቋሚ በሚያንጸባርቁትና የሕወሃት የፖለቲካ አራማጅ በሆኑት ዘርአይ ወልደሰንበት አንዳኝም በማለት ድምጻቸውን አሰምተዋል። የህግ ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ከተከሳሾቹ የተነሳው ጥያቄ ትክክል መሆኑንና እንደዚህ አይነት አቋም ያለው ዳኛ ተከሳሾቹ ቅሬታ ...

Read More »