ነሃሴ ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የኢሳት ወኪል ከስፍራው ባደረሰን መረጃ አስከሬኑ ዛሬ ንጋት ላይ ተኝቶ ሲታከምበት ከነበረው ከናይሮቢ -ወደ አዲስ አበባ ገብቷል። እዮብ ከሳምንት በፊት ልጁን በብሽክሊሊት ትምህርት ቤት አድርሶ ከተመለሰ በሁዋላ ቤቱ መግቢያ በር ላይ ሲደርስ ድንገት ሰውነቱ አልታዘዝ ብሎት መዝለፍለፉን የገለጸችው ባለቤቱ ቲና፤ከዚያ እንደምንም የበሩን ደወል ተጭኖ መጥሪያ ካሰማ በሁዋላ መቆም አቅቶት በተደገፈው በር ሸርተት ...
Read More »Author Archives: Central
ለአቶ መለስ ሙት አመት መታሰቢያ የመንግስት ሰራተኞች በግድ እንዲገኙ ታዘዙ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ጠ/ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ ሙት ዓመት በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ጉለሌ ዕጽዋት ማዕከል በልዩ ልዩ ፕሮግራም ታስቦ እንደሚውል ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ደግሞ የተለያዩ የመንግስት ሰራተኞች ምሽትና ነገ ሻማ በማብራት እንዲዘክሩት ታዘዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች ኢቲቪ አቶ መለስ ዜናዊ ከተናገራቸው ንግግሮች መካከል እያለ ሲያቀርብ መሰንበቱ እንዳሰለቻቸው ተናግረው፣ የፓርቲው ካድሬዎች በየመስሪያ ...
Read More »በቁጫ ወረዳ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር ጨምሮአል
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በወረዳው የተነሳውን ከማንነት ጋር የተያያዘ ጥያቄ ለማፈን መንግስት የጀመረውን ዘመቻ በማጧጧፍ ለውጭ አገር ሚዲያ መረጃ ይሰጣሉ የተባሉትን የቁጫን ህዝብ በመወከል ሲከራከሩ የነበሩት መቶ አለቃ ማሴቢ ማዳልቾ፣ ባለፈው ቀድሜ ተይዘው ዛሬ ወደ አርባምንጭ ተልከዋል። በአጠቃላይ እየታደኑ ካሉት መካከል 12 አንጋፋና ታዋቂ ሰዎች ሲታሰሩ፣ 9ኙ የገቡበት አልታወቀም። በወረዳው የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስ ወደ ...
Read More »ቴሌ ኮሚኒኬሽን ከቻይናው ዜድ ቲ ኢ ጋር የ 800 ሚሊዮን ዶላር ስምምነት ተፈራረመ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ስምምነቱ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሞባይል ስርጭት ተጠቃሚ ወደ 50 ሚሊዮን ለማሳደግ የተደረገ ነው ተብሎአል። መንግስት ለዘርፉ ከመደበው 1 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ከፊሉን ለሌላው የቻይና ኩባንያ ሀዋይ መስጠቱ ታውቋል። ሁለቱም የቻይና ኩባንያዎች የመንግስትን የስልክና የሌሎች የመገናኛ መንገዶች ጠለፋ አቅም እንደሚያዳብሩለት ኢሳት ምንጮችን በመግለጽ መዘገቡ ይታወሳል። የኢህአዴግ ልሳን የሆነው ዋልታ በሰራው ዜና ...
Read More »በአዲስ አበባ በሳምንት እንድ ቀን ውሀ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች መኖራቸው ተዘገበ
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- “በሳምንት አንድ ቀን ውሃ ማግኘት ብርቅ የሆነባቸው ሰፈሮች፣ በውሃ እጦት አካባቢያቸውን በመጥፎ ጠረን የሚበክሉ የኮንዶሚኒየም መኖሪያዎች፣ ለተደጋጋሚ አቤቱታ ምላሽ ሳያገኙ በርካታ ወራት እየተቆጠሩ የሚማረሩ ነዋሪዎች የአዲስ አበባ የዘመኑ ገጽታ ሆነዋል” ሲል አዲስ አድማስ ዘገበ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ” በቂ ውሃ ስለሌለ በራሽን ለማከፋፈል እየሞከረ” መሆኑን ገልጿል። ባለስልጣኑ ” የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የአንዳንድ ሰራተኞች ...
Read More »ድምጻዊ እዮብ መኮንን ከዚህ አለም በሞት ተለየ።
ነሃሴ ፲፫(አስራ ሦስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ታዋቂው ድምጻዊ እዮብ መኮንን በብስክሌት ላይ ሆኖ ሲጓዝ በመውደቁ ሆስፒታል ከገባ በሁዋላ በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። አርቲስት እዮብ በባልደረቦቹ እርዳታ ወደ ኬንያ በመሄድ ለአጭር ቀናት በህክምና ሲረዳ ቆይቷል። ኢሳት በአርቲስት እዮብ ሞት የተሰማውን ሀዘን ለመግለጽ ይወዳል።
Read More »መንግስት የሼህ ኑሩ ይማምን ግድያና የሙስሊሙን ተቃውሞ ከአንድነት ፓርቲና ኢሳት ጋር ሊያያዝ ሞከረ
ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ትናንት ሼህ ኑሩን ማን ገደላቸው በሚል ርእስ በኢቲቪ በለቀቀው ዘጋቢ ፊልም ላይ አንድነት ፓርቲ የሼህ ኑሩን ግድያ ደግፎ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲጠራ ማድረጉን የግንቦት7 ልሳን የሆነው ኢሳት ቴሌቪዥንም አሸባሪዎችን ” አይዞአችሁ በርቱ” እያለ ድጋፍ እንደሰጣቸው አንድ ግለሰብን በማናገር አቅርቧል በዘጋቢ ፊልሙ ላይ ሶስት ተጠርጣሪ ገዳዮች ቀርበው የሚናገሩ ሲሆን፣ ፊልሙ ከአንዱ ክፍል ተቆርጦ ከሌላው ...
Read More »የኢህአዴግ አባላት ክርስቶፎር ስሚዝ በሚያረቁት ህግ ላይ የተቃውሞ ፊርማ ማሰባሰብ ጀመሩ
ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከደጋፊዎቹ የመረጃ ለውውጥ ለመረዳት እንደተቻለው ኮንግረስ ማን ክሪስ ስሚዝ በቅርቡ በኢትዮጵያ ዙሪያ የግንቦት 7 መሪ ዶ/ር ብርሀኑ ነጋን፣ ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሀላፊ ሚ/ር ያማማቶ እና ሌሎችንም ታዋቂ ሰዎች በመጋበዝ በኢትዮጵያ ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችን ማሰባሰባቸው ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ ኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን እንድታከብርና ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን እንድትገነባ፣ ኮንግረሱ የህግ ...
Read More »አትሌት ሀይሌ ገብረስላሴ የሚያዘጋጀው የታላቁ ሩጫ የንግድ ፈቃድ ተሰረዘ
ነሃሴ ፲(አስር)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ፈቃዱን የቀማው ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጪ ሲንቀሳቀስ ተገኝቷል በሚል ነው። ከታላቁ ሩጫ በተጨማሪ እስላማዊ የምርምርና የባህል ማዕከል ፣ ጎህ ቻይልድ ዩዝ ውመንስ ዴቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ፣ዋን ዩሮ ኢትዮጵያ ፣ ብራይት አፍሪካ ኢንተግሬትድ ዴቨሎፕመንት አሶሲየሽን እና ፓድ ኢትዮጵያ ሊትሬሲ ኢዱኬሽን ኤንድ ቮኬሽናል ሴንተር ናቸው። የድርጅቶቹን ሃብትና ንብረት በስማቸው በማዞር ሲጠቀሙ ፥ የፋይናንስ ምንጫቸውም ከተፈቀደው በላይ የሆኑ ...
Read More »በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በመንግስት ተወካዮች ‹በሀይማኖት መቻቻል› ዙሪያ የተጠራ የውይይት መድረክ ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠመው
ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ በአዲስ አበባ ወረዳ ሶስት አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ድላችን ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመንግስት ተወካዮች ‹በሀይማኖት መቻቻል› ዙሪያ የተጠራ የውይይት መድረክ ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠመው ተሰማ፡፡ በስብሰባው ላይ የታደሙት የእስልምናና የክርስትና እምነት ተከታዮች የመንግስት ተወካዮች እየተካሄደ ያለውን የሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ከአክራሪነትና አሸባሪነት ጋር ለማያያዝ ያደረጉትን ማብራሪያ አንድ አይነት አቋም በመያዝ መቃወማቸውን ለኢሳት የደረሱ መረጃዎች ...
Read More »