ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የቀድሞ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድ ቤት ይታይ በሚለው ጉዳይ ላይ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የመጨረሻ ውሳኔውን እንዲያሳውቅ ሲል የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ትእዛዝ በመስጠት ለታህሳስ 22 ቀን 2006 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። ፍ/ቤቱ ቀደም ሲል በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ጉዳዩን የመረመረው የህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ...
Read More »Author Archives: Central
በኔልሰን ማንዴላ የመታሰቢያ ዝግጅት ላይ መስማት ለተሳናቸው ትርጉም ያቀርብ የነበረው ግለሰብ የተሳሳተ መልእክት ሲያስተላልፍ ነበር ተባለ
ታህሳስ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ማክሰኞ በደቡብ አፍሪካ ስዌቶ በተደረገው የቀድሞው የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት የኔልሰን ማንዴላ መታሰቢያ ከመድረክ ይተላለፍ የነበረውን ዝግጅት በምልክት ቋንቋ መስማት ለተሳናቸው ዜጎች እንዲያስተላልፍ ተመድቦ የነበረው ሰው፤ ያሳይ የነበረው አካላዊ እንቅስቃሴና ምልክት የውሸት እንደነበር መጋለጡን ዓለማቀፍ ብዙሀን መገናኛ እየዘገቡ ነው። ድርጊቱ የደቡብ አፍሪካን መንግስትና በ ዓለማቀፍ ደረጃም መስማት የተሳናቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች ክፉኛ አስቆጥቷል። ከነ ባራክ ...
Read More »40 በ 60 እና 10 በ 90 የቤት እቅዶች መንግስትን ፈተና ውስጥ ጥለውታል
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት በውጭ አገር ለሚገኙ ኢትዮጵያውያንና ሀቅሙ ላላቸው ዜጎች የ40 በ60 እንዲሁም በአዲስ አበባ በአነስተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ዜጎች ደግሞ የ10 በዘጠና እና የ20 በ80 የቤት ልማት እዶችን ዘርግቷል። በ10/90 850 ሺ በ 20/80 ደግሞ 350 ሺ የአዲስ አበባ ነዋሪ ተመዝግቦ እድሉን በመጠባበቅ ላይ ሲሆን ከ12 ሺ በላይ በውጭ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ 40 በ60 ...
Read More »በኢትዮጵያ ለሚታየው መብራት መጥፋት መስሪያቤቶች እርስ በርስ እየተካሰሱ ነው
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ አንዳንድ አካባቢዎች እና በሰሜን የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ ከተሞች መብራት በተደጋጋሚ እየተቋረጠ ሲሆን፣ መብራት ሀይል የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተናበው ለመስራት አልቻሉም በሚል ወቀሳ አሰምቷል። በጉዳዩ ዙሪያ ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው የኢትዩጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ 40 በመቶ የሚሆነው ኤሌክትሪክ ሃይል መቆራረጥ የሚፈጠረው በሰው ሰራሺ አደጋ ነው ያሉ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ መንገድ እና ...
Read More »በአርባ ምንጭ ዙሪያ የሚገኙ መምህራን ደሞዛቸውን ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ
ታህሳስ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መምህራኑ ለኢሳት እንደተናገሩት ያለፍላጎታቸው ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን በመቃወም የተቆረጠው ገንዘብ ተመልሶ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል። ሙሉ ደሞዛችን እስካልተሰጠን ድረስ ምንም አይነት ክፍያ አንቀበለም ያሉት መምህራኑ፣ እስከ ፊታችን አርብ ሙሉ ደሞዛችን የማይሰጠን ከሆነ የስራ ማቆም አድማ እንዳርጋለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል። በደቡብ ክልል መንግስት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከመምህራኑ ደሞዝ ላይ ያለፍላጎታቸው እየተቆረጠ ...
Read More »ሰመጉ በቤንሻንጉል ጉሙዝ የሰብአዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን አስታወቀ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች አማራ ናችሁ ተብለው በተባረሩ በሺዎች በሚቆጠሩ ዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ጥሰት እና አካላዊ ጉዳት እንደተፈፀመ የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ባካሄደው ጥናት አረጋግጧል ፡፡ በክልል በተለያዩ ዞንና ወረዳዎች ውስጥ ይኖሩ የነበሩ ቁጥራቸው ከ10 ሺህ በላይ የሚገመቱ ዜጐች ለረዥም አመታት ይኖሩበት ከነበረው አካባቢያቸው የዚህ ክልል “ተወላጆች አይደላችሁም” በማለት በሀይልና በግዳጅ ቤት ንብረታቸውን ...
Read More »ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በአባይ ግድብ ዙሪያ እንደገና ጥናት እንዲካሄድ ተስማሙ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብሉምበርግ እንደዘገበው ከአራቱም አገራት የተውጣጣ ኮሚቴ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ከተቋቋመ በሁዋላ፣ በግድቡ ላይ ጥናት የሚካሂዱ ምሁራንንና ይመርጣል። ይህ ቡድን ጥናቱን ሲያጠቃልል ለሶስቱም መንግስታት የጥናት ውጤቱን ያቀርባል። ከዚህ ቀደም የተቋቋመው አንድ አለማቀፍ ቡድን በግድቡ ፕሮጀክት ላይ ተጨማሪ ጥናት እንዲካሄድ ጠይቆ ነበር። ባለፈው ወር በሚቋቋመው ኮሚቴ ላይ አለማቀፍ ተወካዮች እንዲገኙ ግብጽ ያቀረበችውን ጥያቄ ኢትዮጵአ አልተቀበለችውም ...
Read More »አቶ አማረ አረጋዊ በጸና መታመማቸው ታወቀ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የፕሬስ ታሪክ ውስጥ ለ18 ኣመታት በሕትመት ላይ የቆየው የሪፖርተር አማርኛ እና እንግሊዝኛ ጋዜጦች አሳታሚ የሆነው ሚዲያ ኤንድ ኮምኒኬሽን ሴንተር ባለቤትና የቀድሞው የህወሃት ታጋይ አቶ አማረ አረጋዊ በጠና ታመው በአዲስ አበባ በኮሪያ ሆስፒታል ሕክምናቸውን እየተከታተሉ መሆኑን የቅርብ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ አቶ አማረ ባደረባቸው ድንገተኛ ሕመም በኮሪያ ሆስፒታል ሲረዱ 10 ቀናት ያለፋቸው ሲሆን ሕመሙ ከበድ በማለቱ ...
Read More »በቼክ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ በሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሚፈጸመውን ጥቃት ተቃወሙ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያውያኑ ለኢሳት በላኩት መረጃ ሰኞ እለት ፕራግ በሚገኘው የሳውዲ ኢምባሲ ፊት ለፊት በመገኘት በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት በጩኸትና የተለያዩ መፈክሮችን በመጠቀም አውግዘዋል። ያዘጋጁትን የተቃውሞ ደብዳቤ ለኢምባሲው ተወካይ ማስረከባቸውንም አክለው ገልጸዋል።
Read More »ታላቁን የአፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የሚዘክር ዝግጅት ተካሄደ
ታህሳስ ፩(አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአለማችን ታላላቅ መሪዎች፣ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ዝግጅት የማንዴላ የትግል ጉዜ ተዘክሯል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይህን ታላቅ የታሪክ ሰው ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፤ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን አሳሪዎችንም ነጻ ያወጣ፣ሀሳብን ወደ ተግባር የለወጠ ሲሉ ማንዴላን ገልጸዋቸዋል። ከእንግዲህ እንደማንዴላ አይነት ሰው አናገኝም ያሉት ኦባማ፣ከማንዴላ ባንስም ማንዴላ ግን የተሻልኩ ሰው እንደሆን ፍላጎት ያሰደረብኝ ሰው ነው ...
Read More »