ታላቁን የአፍሪካ የነጻነት ታጋይ ኔልሰን ማንዴላ የሚዘክር ዝግጅት ተካሄደ

(አንድ)ቀን ፳፻፮ /  ኢሳት ዜና :-የአለማችን ታላላቅ መሪዎች፣ እና ታዋቂ ሰዎች በተገኙበት በዚህ ዝግጅት የማንዴላ የትግል ጉዜ ተዘክሯል።

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ይህን ታላቅ የታሪክ ሰው ለመግለጽ አስቸጋሪ ነው ብለዋል፡፤ እስረኞችን ብቻ ሳይሆን አሳሪዎችንም ነጻ ያወጣ፣ሀሳብን ወደ ተግባር የለወጠ  ሲሉ ማንዴላን ገልጸዋቸዋል።

ከእንግዲህ እንደማንዴላ አይነት ሰው አናገኝም ያሉት ኦባማ፣ከማንዴላ ባንስም ማንዴላ ግን የተሻልኩ ሰው እንደሆን ፍላጎት ያሰደረብኝ ሰው ነው  ሲሉ አክለዋል።

ተመድ ዋና ጸሀፊ ባንኪሙን በበኩላቸው በምሳሌ ያስተማረን ከአለማችን  ታላላቅ መምህሮች መካከል አንዱ ነው ብለዋል። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን በዝግጀቱ ስታዲየም ተገኝተው ለቀድሞው መሪያቸው ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማም ማንዴላን ልዩ ሰው ፣ ደፋር እና የሚያምኑበትን በጠንካራ ሁኔታ የሚገልጹ ሰው ነበሩ ብለዋል። የማንዴላ የቀብር ስነስርአት የፊታችን እሁድ ይፈጸማል።