Author Archives: Central

ቻይና የጃፓኑ መሪ ኢትዮጵያን በመጎብኘታቸው ተቃውሞዋን ገለጸች።

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሶሸትድ ፕሬስ እንደዘገበው የቻይና የአፍሪካ ህብረት ተወካይ የሆኑ አንድ ባለስልጣን ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ ያሉትን የጃፓኑን ጠ/ሚ ሽንዞ አቤን ችግር ፈጠሪ ብለዋቸዋል። በአይቮሪኮስት፣ ሞዛምቢክና ኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የመጡት ጠ/ሚ አቤ ለአፍሪካ አገራት ከፍተኛ የእርዳታ ገንዘብ ለመለገስ ቃል በመግባት የቻይናን ተጽእኖ ለመቋቋም ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን ጋዜጣው ዘግቧል። .በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደርና ...

Read More »

በኢትዮጵያ ትላላቅ ከተሞች የሚታየው የውሀ እጥረት እንደቀጠለ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ ዋና ከተማ አዲስ አበባ ያለው የውሀ አቅርቦት አሳሳቢ እየሆነ ባለበት ሰአት በመቀሌና በአዳማ የሚታየው ከፍተኛ የውሀ እጥረት ነዋሪዎችን በእጅጉ እያስመረረ ነው። በመቀሌ አንዳንድ አካባቢዎች ካለፉት 4 ወራት ጀምሮ ውሀ ተቋርጧል። በአዳማም እንዲሁ አንዳንድ አካባቢዎች ለረጅም ቀናት ውሃ በመቋረጤ ነዋሪዎች ምሬታቸውን እየገለጹ ነው ። መንግስት የአገሪቱ የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋን 61 በመቶ ...

Read More »

በደቡብ ሱዳን የሚካሄደው አስከፊ ጦርነት እንደቀጠለ ነው

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች በአዲስ አበባ የሰላም ድርድር እያደረጉ ቢሆንም፣ ጦርነቱ ግን በመሬት ላይ እየተካሄደ መሆኑን የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ። ከቀናት በፊት በነዳጅ ሀብቱ የበለጸገው አፐር-ናይል ስቴት የተበላውን ግዛት ዋና ከተማ ማላካልን መቆጣጠራቸውን  የመንግስት ሃይሎች ቢያስታውቁም፣ የአማጽያኑ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር ከተማዋን መልሰው መቆጣጠራቸውን አስታውቀዋል። የአማጽያኑ የድል ወሬ እንደተሰማ መንግስት ጦርነት የተካሄደ በሆንም፣ ከተማዋ ...

Read More »

የግብጽ ህዝብ ለአዲሱ ህገ መንግስት ድምጽ ሰጠ

ጥር ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡት የግብጹ መሪ ሙሀመድ ሙርሲ በወታደሮችና በተቃዋሚዎች ድጋፍ ከስልጣን ከተወገዱ በሁዋላ የሽግግር መንግስቱ አዲስ ህገመንግስት በማርቀቅ ድምጽ እንዲሰጥበት አድርጓል። ባለፉት ሁለት ቀናት በተሰጠው ድምጽ አብዛኛው ህዝብ አዲሱን ህገመንግስት ይደግፋል ተብሎ ይጠበቃል። በአዲሱ ህገመንግስት አንድ ፕሬዚዳንት ለ2 ጊዜ ብቻ የሚመረጥ ሲሆን ፓርላማውም ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን የማንሳት መብት ተሰጥቶታል። ህገመንግስቱ እስልምና የአገሪቱ ብሄራዊ ...

Read More »

ኢህአዴግ የአብዮታዊ ዲሞክራሲ መመሪያን መተውን አስታወቀ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ አማካሪ የሆኑት አቶ በረከት ስምዖን በቅርቡ ከሚኒስትሮች እና ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይትና ግምገማ ላይ ” ህዝቡን ለመምራት የሚነደፉ ንድፈ ሀሳቦች ( ቲዮሪዎች) በየጊዜው ካልተሻሻሉ የሚዝጉ በመሆናቸው አብዮታዊ ዲሞክራሲ በልማታዊ ዲሞክራሲ እንዲተካ ተደርጓል ብለዋል። የኢህአዴግ መንግስት ይበልጥ የሚገለጸው በአብዮታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ሳይሆን በልማታዊ ዲሞክራሲ አስተሳሰብ ነው ...

Read More »

መንግስት የግል መጽሄቶች የህትመት ቁጥር መጨመር ስጋት ላይ እንደጣለው ታወቀ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስታዊዎቹ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እና በአሁኑ ወቅት በመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ስር በአንድ መመሪያነት የሚሰራውና በአዋጅ በፈረሰ ስም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እየተባለ የሚጠራው ድርጅቶች በጋራ አጥንተናል ባሉትና ሰባት ያህል መጽሄቶች ሕግና ስርዓትን በመተላለፍ እየሰሩ መሆኑን የሚያውጀው ጥናት መነሻ የመጽሄቶቹ ቁጥር መጨመር ገዢውን ፓርቲ ስጋት ላይ በመጣሉ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። ለጉዳዩ ቅርበት ...

Read More »

የኢትዮጵያ የድንበር ኮሚሽን ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ ደብዳቤ ላከ

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኮሚሽኑ በደብዳቤው የኢህአዴግ መንግስት ሰፊ የሆነውን የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፎ ለመስጠት የሚያደርገውን እንቅስቃሴ የመንግስትታቱ ዋና ጸሀፊ እንዲያዩት ጠይቋል። ገዢው ፓርቲ በሱዳን ውስጥ ተቃዋሚዎች የመደራጃ ቦታ እንዳያገኙ በሚል ከሱዳን ጋር ተቀባይነት የሌለው የድንበር ውል እያደረገ መሆኑንም ኮሚሽኑ ገልጿል። የአፍሪካ ቀንድ በዚህ መሬት የተነሳ ለሌላ ግጭት ሊዳረግ እንደሚችል ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል። በዚህ ዜና ዙሪያ ...

Read More »

የአፍሪካው ልዑል የተሰኘውን መጽኃፍ በሬዲዩ ፋና መተረኩ ተቃውሞ ገጠመው

ጥር ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት በመተረክ ላይ ባለው በታጋይ መዝሙር ፈንቴ ተርጓሚኒት  በአቶ ዳንኤል ግዛው ጸኃፊነት የቀረበው መጽሀፍ  በአማራ ህዝብ  ላይ  ጥላቻ እንዲፈጠር እያደረገ ነው በማለት የብአዴን አባላት ተቃውመውታል። አባላቱ በብር ሸለቆ በመካሄድ ላይ ባለው ስልጠና ላይ  እንደተናገሩት ሬዲዩ ፋና ታሪካዊ ስህተት እየፈጸመ ነው ፡፡ “የህውሃት ድብቅ አላማ እውን እየሆነ ነው” ያሉት ፤ ...

Read More »

ኢህአዴግ ከምርጫ 2007 በሁዋላ ረብሻ ሊነሳ ይችላል አለ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢትዮጵያን ላለፉት 23 ዓመታት የገዛው ኢህአዴግ መጪውን ምርጫ ተከትሎ በአዲስ አበባና በዋና ዋና የአገሪቱ ከተሞች ረብሻዎች ሊነሱ እንደሚችሉ ፓርቲው ድምዳሜ ላኢ መድረሱን አስታውቋል። የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት በኢትዮጵያ መንግስት አሸባሪ ተብለው የተፈረጁት በተለይ ግንቦት7 እና ኦነግ ምርጫውን ተከትሎ በምርጫ 97 የታየውን አይነት የህዝብ አመጽ ለማስነሳት እየሰሩ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ የደረሰው ኢህአዴግ፣ ...

Read More »

በኦሮምያ ክልል ወረቀቶችን በትነዋል የተባሉ ተማሪዎች ታሰሩ

ጥር ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአፍሪካ ቀንድ የሂውማን ራይትስ ሊግ ለኢሳት በላከው መግለጫ ከነሐሴ እስከ ታህሳስ ባለው ጊዜ ውስጥ የኦሮሞ ህዝብ ፌደራሊስት ኮንግረስ አባላት ናቸው የተባሉ 45 ሰዎች በጉጂ ዞን በነገሌ እስር ቤት ውስጥ ያለፍርድ ቤት ትእዛዝ ታስረው ይገኛሉ። ከታሰሩት መካከልም የሁለተኛ ደረጃ፣ የኮሌጅና የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችና መምህራን ይገኙበታል። በጉጂ ወረዳ በሀርኬሎ ከተማ የሚኖሩ 8 የኮሌጅ ተማሪዎች የጉጂ ...

Read More »