በእስር ላይ የሚገኙ የአየር ትራፊክ ተቆጣጠሪዎች እንዲፈቱ ባልደረቦቻቸው ጥያቄ አቀረቡ ( ኢሳት ዜና መስከረም 08 ቀን 2011 ዓ/ም ) ከነሃሴ 21 የስራ ማቆም አድማ ጋር በተያያ የታሰሩት የአየር ትራፊክ ተቆጣጣሪዎች እንዲፈቱ የድርጅቱ ሰራተኞች ለጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ በጻፉት ደብዳቤ አመልክተዋል። ሰራተኞቹ ጥያቄያቸው ፍትሃዊ ቢሆንም፣ ተገቢውን መልስ ከመስጠት ይልቅ ተገደው ወደ ስራ እንዲመለሱ መደረጉን ተቃውመው፣ ተቃውሞውን አስተባብረዋል በሚል የታሰሩት 9 ባልደረቦቻቸው ከእስር ...
Read More »Author Archives: Central
በቡራዩና አካባቢው የተፈጸመው ጥቃት የተቀነባበረ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 7/2011) በቡራዩና አካባቢው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት የተቀነባበረና በአንድ እዝ ስር ያረፈ መሆኑን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ገለጹ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ዘይኑ ጀማል ዛሬ አዲስ አበባ ላይ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ሁለ የፖለቲካ ድርጅቶች እጃቸው እንዳለበት ገልጸዋል። እነዚህ ሃይሎች በአንድ ዕዝ ስር ያቀነባበሩት ጥቃት ነው ብለዋል። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ጥቃት አቀናባሪዎቹ የፖለቲካ ድርጅቶች የትኞቹ እንደሆኑ በስም ከመግለጽ ግን ...
Read More »በቡራዩና አካባቢው የተገደሉት ሰዎች ቁጥር ከ25 ይበልጣል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 7/2011)በቡራዩ፣በአሸዋ ሜዳና በከታ በሳምንቱ መጨረሻ በንጹሃን ላይ በደረሰው ጥቃት ከ25 በላይ የሚሆኑ ሰዎች መገደላቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ይህንን ጥቃት ለመቃወም በአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ከወጡ ዜጎች መካከልም 5 ሰዎች መገደላቸውና ሌሎች መቁሰላቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል። ግድያውም መሳሪያ በነጠቁ ግለሰቦች ላይ የተፈጸመ ነው ብሏል። በቡራዩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት የተገደሉ ዜጎች ቁጥራቸው የበዛ መሆኑንም የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ ...
Read More »በአዲስ አበባ እና በአርባምንጭ ከተሞች በቡራዩና ዙሪያ ከተሞች የተፈጸሙትን ግድያዎች የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ
በአዲስ አበባ እና በአርባምንጭ ከተሞች በቡራዩና ዙሪያ ከተሞች የተፈጸሙትን ግድያዎች የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎች ተካሄዱ ( ኢሳት ዜና መስከረም 07 ቀን 2011 ዓ/ም ) በአዲስ አበባ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በሰልፈኛው ላይ በወሰዱት እርምጃ እስካሁን 5 ሰዎች መገደላቸውን የደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ። በቡራዩና በተለያዩ የአዲስ አበባ ዙሪያ ከተሞች የተደራጁ ወጣቶች በፈጸሙት ጥቃት በርካታ ዜጎች ተገድለዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም ተፈናቅለዋል። መንግስት ወንጀለኞችን በቁጥጥር ስር ...
Read More »በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ፍርድ ተላለፈባቸው
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩት ዲፕሎማት ኢትዮጵያ ውስጥ በፈጸሙት ወንጀል በሃገራቸው ፍርድ ተላለፈባቸው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ከ2014 እስከ 2017 በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር የነበሩት ኪምኩን ሁዋን ከትላንት በስቲያ ረቡዕ የአንድ አመት እስራት የተፈረደባቸው በወሲባዊ ትንኮሳና ድርጊት ወንጀለኛ ሆነው በመገኘታቸው ነው። በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር በነበሩት ወቅት ከእርዳታ ሰጪ ድርጅት ሰራተኛና ከኤምባሲው ሰራተኛ ጋር ወሲባዊ ትንኮሳ በመፈጸም የተወነጀሉት ...
Read More »የቴዲ አፍሮ የሙዚቃ ኮንሰርት ተራዘመ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በአዲስ አበባ በተፈጠረው ግጭት ምክንያት ለነገ የታቀደው የድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን የሙዚቃ ኮንሰርት መራዘሙ ታወቀ። መስከረም አምስት ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ የተዘጋጀው የሙዚቃ ኮንሰርት ከ20ሺ በላይ ትኬቶች ተሽጠው ያለቁ መሆናቸውን የገለጹት የኢሳት ምንጮች በአንድ ሳምንት እንዲራዘም መደረጉን ገልጸዋል። ከአዲስ አበባ አስተዳደር በኩል ኮንሰርቱ እንዲራዘም መጠየቁም ታውቋል። ከአንድ ዓመት በፊት ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘው ኢትዮጵያ የተሰኘው አልበም ከወጣ በኋላ የድምጻዊ ቴዎድሮስ ...
Read More »የአማራ ክልል ልኡካን ኤርትራ ገቡ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 4/2011) የአማራ ክልል ልኡካን ኤርትራ ገቡ። የአማራ ልኡካን በአስመራ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ተወያይተዋል። በአማራ ክልል አፈጉባኤ ወይዘሮ ወርቅሰሙ ማሞ የተመራው የአማራ ልኡካን ቡድን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ሊቀጳጳስ የሆኑትን አቡነ አብርሃምን የጨመረ ሲሆን የጎዞው አላማ የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሆነም ተመልክቷል። ቀደም ሲል በአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ሃላፊ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን የተመራ የልኡካን ቡድን በተመሳሳይ ...
Read More »በባህርዳር የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አቀባበል ዝግጅት ተጠናቀቀ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በባህርዳር ነገ ለሚካሄደው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አቀባበል ዝግጅቱን ማጠናቀቁን ኮሚቴው አስታወቀ። የንቅናቄው አመራሮች ዛሬ ባህርዳር መግባታቸውም ታውቋል። ከባህርዳር በተጨማሪ በተለያዩ የአማራ አካባቢዎችም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ አመራሮችና አባላትን ለመቀበል ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በጎንደር የፊታችን እሁድ ተመሳሳይ የአቀባበል መርሃ ግብር እንደሚኖር አዘጋጆቹ ገልጸዋል። የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ በ32 ከተሞች ህዝባዊ ስብሰባ እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል። ...
Read More »ሁሉም ወገኖች ለሰላም እንዲሰሩ ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) በአዲስ አበባ የተፈጠረው ግጭት እንዲቆምና ሁሉም ወገኖች ለሰላም እንዲሰሩ ተጠየቀ። የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ መግለጫ በመስጠት ወጣቶች ከእርስ በእርስ ግጭት ራሳቸውን እንዲያርቁ ጥሪ አድርገዋል። አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ከፌደራል ፖሊስ ጋር በመሆን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስና ሰማያዊ ፓርቲ በተፈጠረው ግጭት ላይ ያተኮረ መግለጫ ዛሬ መስጠታቸው ታውቋል። የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ በሰንደቅ ዓላማ መነሻነት ...
Read More »የሕወሃት ደጋፊዎች በግልጽ ቅስቀሳ ጀመሩ
(ኢሳት ዲሲ–መስከረም 4/2011) የኦሮሞ ነጻነት ግንባር /ኦነግ/ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳን ጨምሮ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ የኦነግ ልኡካንን ለመቀበል የሚደረገው ዝግጅት ወደ ግጭት እንዲያመራ የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ/ሕወሃት/ደጋፊዎች በግልጽ ቅስቀሳ መጀመራቸው ታወቀ። ጸረ ለውጥ ሃይሎች የሚያደርጉትን ይህንን እንቅስቃሴ የአዲስ አበባና የኦሮሚያ ክልል ወጣቶች በቅንጅት እንዲያከሽፉትም ጥሪ ቀርቧል። ወደ ሃገራቸው የሚገቡት የኦነግ ልኡካን አቀባበል ሰላማዊና ደማቅ ሆኖ በስነስርአት እንዲጠናቀቅ ሁለቱም ወገኖች በመቻቻልና ...
Read More »