Author Archives: Central

በምእራብ አርማጭሆና በመተማ የአንድነት ፓርቲ አደራጆች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ታፍነው ተወሰዱ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአዲስ አበባ የተላኩ የፌደራል ፖሊስ አባላትና ደህንነቶች፣ ወደ ፓርቲው መሪዎች ቤት ከንጋቱ አስራ አንድ ሰአት ላይ በመሄድ፣ መኖሪያ ቤቶቻቸውን ሰብረው በመግባትና አንዳንዶችንም ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ በመደብደብ አፍነው ወዳልታወቀ ቦታ ወስደዋቸዋል። የመተማ ወረዳ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ በላይነህ ሲሳይ፣ የምእራብ አርማጭሆ ወረዳ ሰብሳቢ አቶ አንጋው ተገኝ እንዲሁም የስራ አስፈጻሚ አባላት የሆኑት አባይ ዘውዱና እንግዳው ...

Read More »

ዘጠኝ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት ትብብር የመጀመሪያ የትግል ስትራቴጂውን ይፋ አደረገ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ትብብር የመሰረቱ 9 ተቃዋሚ ፓርቲዎች ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል ለአንድ ወር የሚቆይ የመጀመሪያ ዙር የህዝባዊ ትግል ፕሮግራሙን ጥቅምት 25/2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት ይፋ አድርገዋል። ‹‹ነጻነት በሌለበት ፍትሃዊ ምርጫ የማይታሰብ በመሆኑ የተዘጋውን በር ለመክፈት የ‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ› በሚል የዝግጅት መርሃ ግብር አዘጋጅቷል። ‹‹ምርጫ ቦርድ ለገዥው ፓርቲ ያለውን ወገናዊነትና ጉዳይ አስፈጻሚነት ፍንትው ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የቅማንት ተወላጆች ያነሱትን ጥያቄ ተከትሎ በተጠራ የስራ ማቆም አድማ በዞኑ የሚገኙ ከ80 በላይ ትምህርት ቤቶች ካለፈው አርብ ጀምሮ የተዘጉ ሲሆን፣ መንግስት እስከ መስከረም 30 መልስ የማይሰጥ ከሆነ፣ ተቃውሞው ግብር ባለመክፈል እንደሚቀጥል አስተባባሪዎቹ ለኢሳት ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም በርካታ አስተባባሪዎች ተይዘው የታሰሩ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን መንግስት ለጥያቄው እስከ መስከረም መጨረሻ መልስ እንደሚሰጥ አስታውቆ ነበር። ...

Read More »

ከፍተኛው ፍርድ ቤት በ16 የኦሮሞ ተወላጅ ተማሪዎች ላይ ውሳኔ አስተላለፈ

ጥቅምት ፳፬(ሃያ አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፍርድ ቤቱ ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተያያዘ ተይዘው በነበሩት ተማሪዎች ላይ ከ1 እስከ 5 በሚደርስ እስር እንዲቀጡ ውሳኔ አሳልፏል። በሌላ ዜና ደግሞ በአዳማ ቤታቸው የሚፈርስባቸው ሰዎች ባስነሱት ተቃውሞ ፖሊሶች ተጎዱ። የአከባቢው ነዋሪዎች እንደገለጹት  ከከተማ አስተዳደሩ ቤት አፍራሽ ግብረ ሀይል  ህገወጥ የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ወደ ስፍራው ቢንቀሳቀስም ወደ 1 ሺ የሚጠጋ ...

Read More »

የመኢአድ አባላት እየታደኑ በመታሰር ላይ ናቸው

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጪውን ምርጫ ተንተርሶ በሚመስል መልኩ በምስራቅና ምእራብ ጎጃም አመራሮችና አባላት መታሰራቸውን ድርጅቱ አስታወቀ በተመሳሳይ ዜና ደግሞ የወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ ሰብሳቢ አቶ ማሞ ገሞ እና የዞኑ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ወኖ በዳሳ ጥቅምት 22 ቀን 2007 ዓ.ም በወላይታ ሶዶ ከተማ በአንድ ሆቴል ውስጥ እያሉ በከተማው የፖሊስ አዛዥ መመሪያ በመንግስት ሀይሎች “እኛ ሀገር ...

Read More »

ለሁለት ወራት ደሞዝ ያልተከፈላቸው የኢትዮ-ድሪም ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዝ ተከፈላቸው

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሆለታ ገነት የሚገኘው የሼከ አላሙዲ ንብረት የሆነው “ኢትዮ ድሪም” የአበባ እና የእንጆሪ ሰራተኞች ጥቅምት 21 እና  22 ከፍያ ተፈጽሞላቸዋል። ሰራተኞች ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው ለኢሳት ባስተዋቁ በቀናት ውስጥ እንደተከፈላቸው ቢገልጹም፣ አሁንም ከሰራተኞች ማመላለሻ መኪናና ከጤና ጋር የተያያዙ ችግሮችን እያነሱ ነው።  ድርጀቱ ለሰራተኛ ማመላለሻ  /ሰርቪስ/ እና ለምርት ማጓጓዣ የተከራያቸው መኪኖች የአገልግሎት ክፍያ ሳያገኙ ከ7 ወራት ...

Read More »

እንባጮ ተብሎ የሚጠራው አደገኛ መጤ አረም በጣና ሃይቅ ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን የአካባቢው አርሶ አደሮችና ባለሙዎች ተናገሩ፡፡

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መጤ አረሙ ከሸፈነው መሬት ሁለት ሺህ ሄክታር በሩዝ ማሳ ላይ ሲሆን ቀሪው በኃይቁና በዙሪያው በሚገኙ ውሃ አዘል መሬት ላይ መሆኑን ተገልጿል፡፡ አረሙ በደንቢያ፣ በጎንደር ዙሪያ፣ በሊቦ ከምከም፣ በፎገራና በደራ ወረዳ በሚገኙ 16 ቀበሌዎች በፍጥነት እየተዛመተ እንደሆነም ታውቋል።አረሙን ለማጥፋት ሲሞከርም በሦስት ሳምንታት ራሱን መልሶ የሚተካ መሆኑና በውሃው ላይ በመንሳፈፍ በንፋስ ሃይል እየተገፋ የሚራባ ...

Read More »

ግንቦት7 በጣሊያን ከሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ጋር የተሳካ ስብሰባ ማካሄዱን ገለጸ

ጥቅምት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ድርጀቱ እሁድ እለት በሮም ባካሄደው ስበሰባ ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተው ድርጅቱን ወክለው ከተገኙት ከአቶ አበበ ቦጋለ ጋር ውይይት አድርገዋል። የፖለቲካ ድርጅቶች በጣሊያን ስብሰባ ሲያደርጉ ባይታይም፣ ግንቦት7 ያካሄደው ስብሰባ ግን የተሳካ እንደነበር ያዘጋጅ ኮሚቴው ሰብሳቢ ሮዛ ተስፋየ ለኢሳት ተናግራለች። በውይይቱ ላይ የተገኙት አብዛኞቹ ኢትዮጵያውያን ግንቦት7 ከኤርትራ ጋር ስላለው ግንኙነት ጥያቄዎችን ያነሱ እንደነበር አዘጋጆቹ ...

Read More »

መንግስት በ10 ፖለቲከኞችና ላይ ክስ መሰረተ

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል አቃቢ ህግ በ10 ተከሳሾች ላይ የሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን አብዛኞቹ ተከሳሾች ከግንቦት7 እና ከደሚት ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለዋል። የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት  ጥቅምት 21/2007 ዓ.ም  ሲሰየም ተከሳሾች በመቶዎች የሚቆጠሩ ገጾች ያሉዋቸው ክሶች ደርሷቸዋል። የግንቦት7 አመራር ነው የተባለው ዘላለም ውርቅአገኘሁ፣ አንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ የፓርቲው ...

Read More »

በምስራቅ የአገሪቱ ክፍል በርካታ የኢንተርኔት ቤቶች ተዘጉ

ጥቅምት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሃረርና የድሬዳዋ ወኪሎች እንደዘገቡት ከጥቅምት 17 ጀምሮ ከአዲስ አበባ የመጡ የፌደራል የጸረ ሽብር ግብረ ሃይል አባላት መሆናቸውን የገለጹ እንዲሁም የፌደራል ፖሊሶች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ የኢንትርኔት ቤት ባለቤቶችን ይዘው በማሰር ወደ ማእከላዊ እስር ቤት ወስደዋቸዋል። ድርጅቶቻቸውና ቤቶቻቸው የተፈተሹባቸው ሲሆን፣ ንብረቶቻቸውም ተጭነው ተወስደዋል። በሀረር በገሊል ህንጻ ላይ የሚገኘው የአሜን ፕሮዳክሽን ባለቤት አቶ ገብረ ሂወት ተገኝ፣ ...

Read More »