ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በላይኛው አዋሽ ተፋሰስ ከመስከረም 28 ቀን 2007 ጀምሮ በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተፈናቀሉ በሺ የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች ከእለት ዕርዳታ ባለፈ ድጋፍ እየተደረገላቸው አለመሆኑን ገለጸዋል፡፡ የአካባቢው ተወካይ እንደገለጹት መንግስት በአካባቢው የገነባው የዝናብ መከላከያ ደረጃውን የጠበቀ ባለመሆኑ ምክንያት በጎርፍ በቀላሉ መሰበሩን ጠቅሰው በዚህ ምክንያት ማሳ ላይ የነበረ ምርታቸውን ጨምሮ መኖሪያ ቤቶቻቸው በጎርፍ መወሰዱን ጠቅሰዋል፡፡ ...
Read More »Author Archives: Central
ከኤርትራ የሚወጡ ስደተኞች ቁጥር መጨመሩን የስደተኞች ኮሚሽን አስታወቀ
ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ኮሚሽንን ጠቅሶ እንደዘገበው ባለፉት 37 ቀናት ከ6 ሺ ያላነሱ ኤርትራውያን ብሄራዊ ውትድርናን በመሸሽ ተሰደዋል። ኮሚሽኑ እንደሚለው የስደተኞች ቁጥር ካለፈው ወር ጋር ሲነጸጻር በእጥፍ ጨምሯል። የኤርትራ መንግስት በበኩሉ ብሄራዊ ወትድርና ዘመቻ ያስፈለገው በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር አካባቢ ያለው ውጥረት እየጨመረ በመምጣቱ እንደሆነ ገልጿል። ሁለቱ አገሮች ከ14 አመታት በፊት ...
Read More »ግብጽ እና ሱዳን ወዳጅነታቸውን ማደሳቸውን አስታወቁ
ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲ መንግስት ከተገለበጠ በሁዋላ በሱዳንና በግብጽ መንግስታት መካከል ያለው ልዩነት ሰፍቶ እርስ በርስ እስከመነቃቀፍ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፣ ሱዳን የሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማጮች የተባለው ፓርቲ እንደምታግድ በማስታወቁዋ ሁለቱ አገራት ወደ አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እያመሩ መሆኑን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጸዋል።ሁለቱ ሃገራት በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ እንደሚሰሩም ቃል ...
Read More »የጅማ ህዝብ ባገዛዙ መማረሩን ገለጸ
ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሙክታር ከድር፣ የገንዝብ ሚኒስትሩ ሶፍያን አህመድና የኦሮምያ የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊው ከጅማ ዞን የተውጣጡ የተለያዩ ድርጅት ተወካዮችን በጊዜ አዳራሽ ሰብስበው ባነጋገሩበት ወቅት፣ ህዝቡ በአስተዳደሩ ተስፋ መቁረጡንና ለውጥ የሚፈልግ መሆኑን ተናግሯል። የምርጫ ቅስቀሳ በሚመስለው መድረክ ፣ አቶ ሙክታር ተሰብሳቢው የሚሰማውን እንዲናገር ፈቅደዋል። ነዋሪዎቹ በዞኑ ልማት የሚባል ነገር እንደሌለ፣ ከጅማ አጋሮ የተሰራው ...
Read More »በዲላ የአንድ የቤተሰብ አባላት ባልታወቀ ሁኔታ መሞታቸው ከፍተኛ ድንጋጤ ፈጠረ
ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ማክሰኞ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ኮቸሬ ከሚባል አካባቢ የመጡ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 4 ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል መግባታቸውን ተከትሎ፣ በሆስፒታሉ ውስጥ ከፍተኛ ድንጋጤ ተፈጥሮ እንደነበር ምንጮች ገልጸዋል። ድንጋጤው የተፈጠረው ሰዎቹ በኢቦላ በሽታ ተይዘዋል በሚል እምነት ነው። ዛሬ ረቡዕ ደግሞ 4ቱም ሰዎች መሞታቸውን የደረሰን መረጃ ያመለክታል። የመንግስት ባለስልጣናት ሰዎቹ በኢቦላ ሳይሆን በምግብ መመረዝ ...
Read More »በአርባምንጭ ታስረው የሚገኙ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተፈረደባቸው
ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በ2006 ዓም በአርባ ምንጭ ዩኒቨርስቲ ረብሻ አስነስታችሁዋላ በሚል ከታሰሩት መካከል 4 ተማሪዎች በ2 አመት ከ3 ወር ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላልፏል። ሁለቱ የ4ኛ 5ኛ አመት የህክምና ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ድገሞ የ3ኛ አመት የነርሲንግ ተማሪዎች ናቸው። በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የሚከተሉትን የአለባባስና የምግብ ስነስርአት መመሪያን ተግባራዊ ለማድረግ በዛሬው እለት በአዳማ ...
Read More »በቡርኪናፋሶ ኮሎኔል አይዛክ ዚዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾሙ
ኀዳር ፲(አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ብሌስ ካምፓወሬን መንግስት በመገልበጥ ጊዜያዊ መሪ መሆናቸውን ካስታወቁ በሁዋላ ስልጣናቸውን ለሲቪል አስተዳደር ያስረከቡት ሌ/ኮሎኔል አይዛክ ሲዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ቢቢሲ ዘግቧል። ጊዜያዊው ፕሬዚዳንት ሚኬል ካፋንዶ ኮሌኔሉን ጠ/ሚኒስትር አድርገው የሾሙት በስልጣን ጉዳይ ሲደረግ የነበረውን ድርድር ተከትሎ ነው። ሁለቱም መሪዎች አገሪቱን ለአንድ አመት ያክል ካስተዳደሩ በሁዋላ ምርጫ ይካሄዳል። ፕሬዚዳንቱ በምርጫው እንደማይወዳደሩ ህጉ ይከለክላቸዋል። ...
Read More »በኦሮምያ ዜጎችን ማሰሩ እንደቀጠለ ነው
ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ የሚታሰሩ ዜጎች ቁጥር መበራከት የአለምን የመገናኛ ብዙሃን ሰፊ ሽፋን ባገኘ ማግስት፣ አሁንም ዜጎችን በሰበብ አስባቡ እያሰሩ ለፍርድ አቅርቦ ማስፈረድ ቀጥሎአል። አፍሪካ ቀንድ የሰብአዊ መብት ሊግ ያወጠው ሪፖርት እንደሚያሳየው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በአምቦ ከተማ እና በሚዳ ቀኒ ወረዳ ከ20 ያላነሱ ተማሪዎች፣ መምህራንና አርሶ አደሮች ታስረዋል። እስራቱ የተፈጸመው መንግስት የአካባቢውን መሬት ለኢንቨስተሮች መስጠቱን ተከትሎ ...
Read More »በአዲስ አበባ በባክቴሪያ አማካይነት ከአንድ ሰው ወደሌላ ሰው በንክኪ የሚተላለፈው የማጅራት ገትር በሽታ ወርረሺኝ ሥጋት አሁንም መኖሩን ከአዲስአበባ ጤና ቢሮ የተገኘ መረጃ አመለከተ፡፡
ኀዳር ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማጅራት ገትር ወረርሺኝ ጋር ተያይዞ ከሳምንት በፊት ለ10 ተከታታይ ቀናት ዕድሜያቸው ከ1 እስከ 29 ኣመት ክልል ላሉ ዜጎች ክትባት የመስጠት ሒደት የተከናወነ ቢሆንም አፈጻጸሙ ከተጠበቀው ውጪ ሆኖአል፡፡ በተለይ ዕድሜያቸው ከ29 ዓመት በላይ መከተብ አያስፈልጋቸውም፣ ከተከተቡ የጎንዮሽ ችግር ያመጣባቸዋል መባሉ ግማሽ ያህል የህብረተሰብ ክፍል ቢሞትም ግድ የለንም እንደማለት ተደርጎ በመቆጠሩ የጤና ጣቢያዎች በክትባት ፈላጊዎች ...
Read More »መንግስት የ9ኙን ፓርቲዎች የአደባባይ ስብሰባ መከልከሉ ትግሉን እንደማያቆመው ፓርቲዎቹ ገለጹ
ኀዳር ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪነት 9 የፖለቲካ ድርጅቶች በጋራ የጠሩት የአደባባይ ስብሰባ በገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች እንዲበተን ከተደረገ በሁዋላ ድርጅቶቹ ባወጡት መግለጫ ” መንግሥት ከገባበት ከፍተኛ የፍርኃት ስሜት ለመውጣት ያስቀመጠው የሴራ መፍትሄ መስዋዕትነቱን ይጨምር እንደሆን እንጂ፣ ትግሉን አያቆመውም” ብለዋል። ፓርቲዎቹ ለአንድ ወር ባወጡት የስራ መርሃ ግብር መሰረት ከአራት ኪሎ እና አካባቢው ህዝብ ጋር በአደባባይ በቤልኤር ...
Read More »