ግብጽ እና ሱዳን ወዳጅነታቸውን ማደሳቸውን አስታወቁ  

ኀዳር ፲፩(አስራ አንድ) ቀን ፳፻፯ / ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ሙሃመድ ሙርሲ መንግስት ከተገለበጠ በሁዋላ በሱዳንና በግብጽ መንግስታት መካከል ያለው ልዩነት ሰፍቶ እርስ በርስ እስከመነቃቀፍ ደርሰው የነበረ ቢሆንም፣ ሱዳን የሙርሲ ፓርቲ የሆነውን ሙስሊም ወንድማማጮች የተባለው ፓርቲ

እንደምታግድ በማስታወቁዋ ሁለቱ አገራት ወደ አዲስ የዲፕሎማሲ ግንኙነት እያመሩ መሆኑን የሱዳን መንግስት ቃል አቀባይ ገልጸዋል።ሁለቱ ሃገራት በውሃ አጠቃቀም ዙሪያ ተፈጥሮ የነበረውን ልዩነት ለማጥበብ እንደሚሰሩም ቃል አቀባዩ ገልጸዋል። በተለይ ከኢትዮጵያ ጋር እያወዛገበ ስለሚገኘው የውሃ ድርሻ፣

ሱዳን በቅርቡ ኢትዮጵያን በመደገፍ ስታንጸባርክ የቆየቸውን አቋም ሳትለውጥ እንደማትቀር ከመግለጫው ለመረዳት ይቻላል። ሁለቱ አገራት በመካከላቸው ያለውን የድንበር ውዝግብ ለመፍታትም እንደሚሰሩም አስታውቀዋል።