ጥር ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ድርጅቱ ባወጣው የ2014 አለማቀፍ የሰብአዊ መብት አያያዝ ሪፖርት ላይ እንደጠቀሰው መንግስት ጋዜጠኞችን፣ ጸሃፊዎችን እና የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊዎችን እንደፈለገ ያስራል፣ በሰላም ተቃውሞአቸውን ለመግለጽ በወጡ ዜጎች ላይ ፖሊስ የሃይል እርምጃ ይወስዳል፤ እንዲሁም ለማፈኛነት እየዋሉ ያሉትን በአለማቀፍ ማህበረሰብ ዘንድ የተወገዙትን አዋጆችን ለመለወጥ ምንም ምልክት አላሳየም ብሎአል። ባለፈው አመት የኢትዮጵያ መንግስት ማንኛውንም ተቃውሞ ለማፈን መሞከሩን ...
Read More »Author Archives: Central
ሄሊኮፕተር በመያዝ ወደ ሶስተኛ አገር የጠፉት የአየር ሃይል ባልደረቦች በመልካም ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ገለጹ
ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ባለፈው ወር ሄሊኮፕተር ይዘው የጠፉት ሻምበል ሳሙኤል ግደይ፣ መቶ አለቃ ቢልልኝ ደሳለኝ እና ቴክኒሻን ጸጋ ብርሃን ግደይ በተረጋጋ እና በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለኢሳት ገልጸዋል። ፓይለቶቹ በሚገኙበት ሶስተኛ አገር ውስጥ ሆነው ከኢሳት ጋር ግንኙነት የመሰረቱ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደረገው የነጻነት ትግል አስተዋጽኦ ለማድረግ መዘጋጃታቸውን ተናግረዋል። ሶስታችንም በአንድ ላይ የምንመደብበትን ጊዜ ስንጠብቅ ቆይተን ...
Read More »ዞን ዘጠኝ በሚል ስም የሚጠሩት ወጣት ጸሃፊዎች ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው ጥር 20 ቀን 2007 ዓ.ም ለ16ኛ ጊዜ በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡት ጸሃፊዎች፣ ፍርድ ቤቱ ቀደም ብሎ ተሻሻለ የተባለውን ክስ አይቶ ብይን ሰጥቷል፡፡ የፌደራል አቃቤ ህግ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ ከአንዱ ነጥብ በስተቀር ሦስቱን መቀበሉን ፍርድ ቤቱ ገልጿል። በክሱ ላይ ‹ቡድን› በሚል የተጠቀሰው ነጥብ ተከሳሾቹ በህቡ ...
Read More »አንድነት በመጪው እሁድ የጠራው ሰልፍ ውጥረት ፈጥራል
ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአንድነት ፓርቲ ለእሁድ ጥር 24 በደሴ ለሚያካሄደው ሰልፍ ከከተማው አስተዳዳር እውቅና ያገኘ ሲሆን ፤ የአዲስ አበባው ግን እያወዛገበ ይገኛል። ከፓርቲው ጽህፈት ቤት የወጣው መረጃ እንደሚያሳየው በደሴ ሰልፉ አራዳ አከባቢ ከሚገኘው የአንድነት ቢሮ ተነስቶ ሆጤ አደባባይ ይጠናቀቃል። ከ2: 00 ሰ ዓት እስከ 7:00 ሰዓት በሚቆየው በዚህ ሰልፍ ፤የደሴና የአከባቢዋ ህዝብ በነቂስ በመውጣት ምርጫ ...
Read More »ሼክ ሙሃመድ አላሙዲን ከባለስልጣናት ጋር ባላቸው ቀረቤታ የህዝብ ሃብት የሆኑ ኩባንያዎችን ወደ ግል እንዲያዞሩ ረድቷቸዋል ተባለ
ጥር ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕራይቬታይዜሽንና የመንግስት ልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ ኤጀንሲ የመንግስት ልማት ድርጅቶችን መሸጥ ከጀመረበት ከ1997 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ድረስ ባሉት ጊዜያት ከሸጣቸው 370 ድርጅቶች መካከል ሼህ አልአሙዲ ወደ 30 የሚጠጉትንና እጅግ አትራፊ የሆኑ ድርጅቶችን በርካሽ ዋጋ መሰብሰብ መቻላቸው ስርአቱ ለተዘፈቀበት ሙስና ማሳያ መሆኑን ጉዳዩን በቅርብ የሚከታተሉ ወገኖች ገልጸዋል። ሼሁ የለገደንቢን ወርቅ ማዕድን በአሁኑ ወቅት ሚድሮክ ...
Read More »አንድነት ፓርቲ በድጋሜ የተቃውሞ ሰልፍ ጠራ
ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ህወሃት /ኢህአዴግ ጥር 17/2007 ዓም በአንድነት አመራሮችና አባላት ላይ ያደረሰውን አሰቃቂ ድብደባ ለማውገዝ እንዲሁም ፓርቲውን ለመቀማት የሚደረገውን ጥረት ለማውገዝ ለጥር 24 በአዲስ አበባና በሌሎች የተለያዩ የክልል ከተሞች ላይ ሰልፍ ለማድረግ ማቀዱን ገልጸሏል። አምባገነኑ የህወሀት/ኢህአዴግ መንግስት የዘንድሮውን ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ጭምር በማበላሸት ጠንክራ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ከምርጫው ውጪ እንዲሆኑ ለማድረግ ላይ ...
Read More »በእስራት ላይ የሚገኙት የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በድጋሜ ተቀጠሩ
ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለአራተኛ ጊዜ 28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተሰጠባቸው፡፡ የሰማያዊ፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ዛሬ ጥር 19 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ለአራተኛ ጊዜ የቀረቡ ቢሆንም፤ ፖሊስ ፦‹‹ምስክሮችን ማደራጀት ይቀረኛል›› በማለት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው በጠየቀው መሰረት ...
Read More »ሃይቅ ከተማ የሚገኘው የቴክኒክና ሙያ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ በእሳት ወደመ
ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በተሁለደሬ ወረዳ ሀይቅ ከተማ የሚገኘው የሙያና ቴክኒክ ትምህርት ቤት ሰኞ ጥር 18፣ 2007 ዓም ሙሉ በሙሉ በቃጠሎ መውደሙን ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። ቃጠሎው የተነሳው ከምሽት 1:30 አካባቢ ሲሆን ለ2 ሰአታት ያክል መቆየቱንና የተማሪዎችን መረጃ ላፕቶፖ ኮምፒዩተሮች፣ ዴስክ ቶፖች እና የተለያዩ የሰርቬ ጂፒኤሶችን ማውደሙ ተውቋል። ከኮምቦልቻ ከተማ የተነሳው የእሳት አደጋ ...
Read More »ጎጃምን ከጎንደር የሚያገናኘው የአባይ ድልድይ ትክ የሚሰራበት የቆይታ ጊዜ በመርዘሙ አደጋ ያደርሳል በሚል ስጋት ላይ መሆናቸውን የባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
ጥር ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከ1949 ዓ.ም ጀምሮ ነዋሪ የሆኑት አስተያየት ሰጪ ሲናገሩ ድልድዩ ሲሰራ አለሁ የመሰረት ዲንጋዩ ሲቀመጥ ነበርኩ ካሉ በኋላ ከ25 እስከ 30 ዓመት እንደሚያገለግል በይፋ ተነግሮ እንደተሰራ ከዚህ ዓመት በላይ ከቆየ አደጋ ለያደርስ እንደሚችል በወቅቱ በነበሩ የግንባታ ባለሙያዎች እንደተነገረ በማስታወስ ገልጸው ምንም አይነት የተሰራ አዲስ ነገር ሳይኖር ከ50 ዓመታት በላይ መቆየቱ ስጋት እንዳሳደረባቸው ...
Read More »ወደ ኤርትራ በማቅናት ላለፉት ሶስት ሳምንታት በኤርትራ ድንበር የሚገኙ የኢትዮጰያ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን እንቅስቃሴ ሲቃኙ የቆዩት የኢሳት ጋዜጠኞች ትናንት እሁድ ተመለሱ።
ጥር ፲፰(አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እና ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም የኢህዴግን መንግስት በትጥቅ ትግል ለመፋለም ብረት ያነሱ የኢትዮጰያ ተቃዋሚዎችን እንቅስቃሴ በዓይን ለማየት እንዲሁም ስለ ኢትዮጰያና ኤርትራ የወደፊት ግንኙነት የኤርትራ ባለስልጣናትን ቃለ ምልልስ ለማድረግ ወደ ኤርትራ ያቀኑት ከሶስት ሳምንታት በፊት መሆኑ ይታወቃል። ፋሲልና መሳይ ባለፉት ሶስት ሳምንታት የኤርትራ ቆይታቸው የሄዱበትን ዓላማ በሚገባ ማሳካታቸውን ጋዜጠኛ ፋሲል ገልጿል። በኤርትራ ...
Read More »