ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ወሎ ዞን በቃሉ ወራዳ ጅጋ ቀበሌ ላይ ጀማል ሙሼ የተባለ የ22 ዓመት ወጣት፣ ሃምሌ 27 ቀን 2007 ዓም በሚሊሺያዎች ተገድሏል። ወጣት ጀማል ሙሼ በዩ፣ ሰይድ ሙሄ ጌሮና እንድሪስ ኡመር በተባሉ ታጣቂዎች ተገድሎ ከአካባቢው 24 ኪሎሜትር ርቆ ሊቀበር ሲል መረጃ የደረሳቸው ዘመዶቹ ቦታው ድረስ በመሄድ አስከሬኑን ወስደዋል። ወጣቱ ግንባሩ አካባቢ በጥይት ...
Read More »Author Archives: Central
በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ ላይ የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰማ
ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ኤርትራ ከሚገኘው ግንቦት ሰባት ጋር ሊቀላቀሉ ሲሉ ያዝኳቸው በሚል የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው 1ኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ 2ኛ ተከሳሽ እየሩሳሌም ተስፋው 3ኛ ተከሳሽ ፍቅረማርያም አስማማው እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ ደሴ ካህሳይ ላይ ዛሬ ነሀሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 14ኛ ወንጀል ችሎት የአቃቤ ህግ ምስክር ተሰምቷል። ተከሳሾቹ ...
Read More »አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲቀለቀቁ ፍርድ ቤቱ ወሰነ
ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አይሲስ ኢትዮጵያዊያንን በሊቢያ መግደሉን በመቃውሞ መንግስት በጠራው የሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከለቅሶ ቤት ወደ ቤተ መንግስት የተደረገውን ሰልፍ አነሳስቷል በሚል ክስ የተመሰረተበት አቶ ማሙሸት አማረ በነፃ እንዲለቀቅ የአራዳ ፍርድ ቤት አራተኛ ወንጀል ችሎት ዛሬ ነሃሴ 22 ቀን 2007 ዓ.ም. ወስኗል፡፡ አቶ ማሙሸት አማረ ሚያዝያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም በተካሄደው ሰልፍ ላይ ሁከትና ...
Read More »አርባ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ኬንያ ውስጥ ተያዙ
ነኅሴ ፳፪ (ሀያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኬንያ ሜሩ ግዛት ውስጥ በሕገወጥ የገቡ አርባ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን መያዙን የአካባቢው ፓሊስ አስታወቀ። ስደተኞቹ በሚዮኖዋ መንደር ውስጥ በሚስጥር ቤት ውስጥ ተደብቀው በአካባቢው ሕዝብ ጥቆማ ትብብር መያዛቸውን ፖሊስ ገልጿል። ስደተኞቹ ኬንያን አቋርጠው ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር የመጡ መሆናቸውን በቅርብ ጊዜም ሰማንያ ሕገወጥ ኢትዮጵያዊያን በተመሳሳይ መልኩ መያዛቸውን የጸጥታ ሰራተኞቹ አክለው ገልጸዋል ሲል የኬንያ ...
Read More »ስኳር ኮርፖሬሽን በዚህ አመት 7 ቢሊዮን ብር ኪሳራ ደረሰበት
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 22 ፣ 2007) ከአራት አመት በፊት የተቋቋመውና አስር የስኳር ፋብሪካዎች ግንባታ ለማካሄድ ሃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ ስኳር ኮርፖሬሽን በተጠናቀቀው የ 2007 አም በጀት አመት የሰባት ቢሊዮን ብር ኪሳራ እንደደረሰበት ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። የሃገሪቱ ነባር የስኳር ፋብሪካዎች እንዲያስተዳድር ሃላፊነት ተሰጥቶት የነበረው ይኸው ኮሮፖሬሽን ለስራው ማስኬጃ ከተለያዩ የመንግስትና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር ለእቃ አቅርቦት መከፈል የነበረበትን ሶስት ቢሊዮን ብር በወቅቱ ...
Read More »እስካሁን 1.2 ቢሊዮን የጨረሰው ተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ለማለቅ ተጨማሪ ብድር ያስፈልገዋል ተባለ
ኢሳት ዜና (ነሐሴ 21 ፣ 2007) ግንባታው ለ 12 አመታት ያህል ሲካሄድ የቆየውና የእዳ መጠኑ 1.2 ቢሊዮን ብር አካባቢ የደረሰው የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ተጨማሪ ብድር ካልጸደቀለት በስተቀር ስራውን በተያዘለት እቅድ መሰረት እንደማይጀምር ምንጮት ለኢሳት ገለጡ። መንግስት የተንዳሆ የስኳር ልማት ፕሮዳክሽን በአምስት አመት የልማት እቅድ መሰረት ወደማምረት ደረጃ ለማሳደግ ቢጥርም ግንባታው በተለያዩ አስተዳደራዊ ችግሮች ሊያልቅ አለመቻሉን የልማት ባንክ ምንጮች ገልጸዋል። የህንዱ ...
Read More »በህወሃት ጉባኤ የአባይ ወልዱና የደብረጺዮን ቡድን አሸናፊ ሆኖ ወጣ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነባር አመራሮቹ በመመረጥና በመምረጥ መብት በድርጅቱ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እንዲሳተፉ የፈቀደው ህወሃት፣ ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ በስራ አስፈጻሚነት ሲያገለግሉ የነበሩ አብዛኞቹን መሪዎችን በድጋሜ መርጧል። አቶ አባይ ወልዱ የድርጅቱም የግንባሩም ሊቀመንበር ሆነው ሲመረጡ፣ ዶ/ር ደብረጺዮን ገብረሚካኤል ደግሞ ምክትል ሆነው ተመርጠዋል። ቀድም ብሎ ህወሃትን ሊለቁ ነው በሚል ሲወራባቸው የቆዩት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ...
Read More »አንድ የመከላከያ አባል የነበረ በፖሊሶች ተደብድቦ አይኑ ጠፋ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሃምሌ 27 ቀን 2007 ዓም በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጫኖ ሚሌ ቀበሌ ውብዬት ጩበሮ የተባለ የመከላከያ ሰራዊት አባል ፣ መከላከያን በመልቀቅ ወደ ቤተሰቦቹ ከተመለሰ ከሁለት ወር በሁዋላ፣ ፖሊሶች አንተ ተቃዋሚዎችን ትደግፋለህ ብለው በሰደፍ ደብድበው አንድ አይኑን እንዳፈሰሱት አባቱ አቶ ጩበሮ ጩኮ ለኢሳት ተናግረዋል። ወታደሩ ወደ ቀየው ከተመለሰ በሁዋላ፣ ከአባቱ ጋር እርሻ ...
Read More »በአዲስ አበባ ወረዳ 9 17 የንግድ ድርጅቶች ታሸጉ
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ነጋዴዎች ለኢሳት እንደገለጹት፣ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናት በድንገት በመምጣት በጉለሌ ክፍለከተማ ወረዳ ዘጠኝ ቀበሌ 02 የሚገኘውን የንግድ ድርጅታቸውን አሽገውባቸዋል። “በቂ ምክንያት ሳይኖርና በቂ የማስጠንቀቂያ ጊዜ ሳይሰጠን፣ ከአንድ ወር ላላነሰ ጊዜ ስራ ፈተን ቤተሰቦቻችን ለችግር ተጋልጠዋል” በማለት የሚናገሩት ነጋዴዎች፣ ጉዳዩን ለተለያዩ ባለስልጣናት ቢያመለክቱም መፍትሄ የሚሰጣቸው አላገኙም። የወረዳው የኢህአዴግ ጽ/ቤት ወኪል የሆኑት አቶ ተክለአብ፣ ...
Read More »የተቃዋሚ አባላትን እያደኑ ማሰሩ እንደቀጠለ ነው
ነኅሴ ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ነሃሴ 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በምዕራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ አብዮት ፋና ቀበሌ ሶስት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸውን የዞኑ የፓርቲው አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ ሶስቱም የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ቤታቸው በታጣቂ ተከቦ እንዳደረ የተገለፀ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በቀበሌው ፖሊስ ጣቢያ ታስረው እንደሚገኙ ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። ታድነው የታሰሩት የሰማያዊ ...
Read More »