ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በተነሳው ግጭት ከፖሊስና ከመከላከያ አንዳንድ ወታደሮች ቆስለዋል። የግጭቱ መንስኤ ሁለት የመከላከያ ፖሊስ አባላት በፖሊሶች መደብደባቸው ነው። ከዚህ ቀደም አንድ ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ ፍቼ አካባቢ ሰፍሮ የሚገኘውን የመከላከያ ሰራዊት አባል ከገደለው በሁዋላ፣ በመከላከያና በፖሊስ መካከል ለወራት የዘለቀ ቁርሾ እንዲፈጠር አድርጓል። ባለፈው ቅዳሜ ሁለት የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው እየተዝናኑ በነበረበት ወቅት፣ ፖሊሶቹ ...
Read More »Author Archives: Central
ለምዕራብ አርማጮኾ ነዋሪዎች በጤና ዙሪያ ለሚሰጠው አገልግሎት ገዢው መንግስት በቂ በጀት አለመመደቡ በነዋሪው ላይ ችግር እየፈጠረ መሆኑ ተነገረ፡፡
ጥቅምት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃገሪቱ ከሚገኙ አምራች አካባቢዎች አንዱ በሆነው በየዓመቱ ከሰኔ እስከ ህዳር ወር ድረስ ከፍተኛ የሰራተኛ ቁጥር የሚያስተናግደው የምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ውስጥ በሚገኙ ቀበሌዎች የሚገኙ የጤና ተቋማት ተገቢውን አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችላቸውን በጀት የክልሉ መንግስት ባለመመደቡ በየአመቱ ተገቢውን አገልግሎት መስጠት እንዳልቻሉ የወረዳው የጤና አመራሮችና ባለሙያዎች ተናገረዋል፡፡ በምዕራብ አርማጮኾ ወረዳ ያለው ነዋሪ አርባ አምስት ሽህ አካባቢ ...
Read More »የአንጋፋው ጋዜጠኛ የአቶ ሙሉጌታ ሉሌ የቀብር ስነ-ስርአት በአሜሪካ ቨርጂኒያ ግዛት ተፈጸመ
ኢሳት ዜና (ጥቅምት 27 ፣ 2008) በዋሺንግተን ዲሲ አቅራቢያ አርሊንግተን በተካሄደው በዚህ የቀብር ስነ-ስርአትና በአሌክሳንድሪያ ከተማ በተከናወነው የጸሎት ፕሮግራም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱንም ለማየት ተችሏል ። ከአውሮፓ፣ ከካናዳና፣ ከተለያዩ የአሜሪካ ግዛት የመጡ እንዲሁም በዋሺንግተን ዲሲ ዙሪያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት የጸሎትና የቀበር ስነ-ስርአት የአቶ ሙሉጌታ ወዳጆች ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል። የአንጋፋው ጋዜጠኛና ደራሲ እንዲሁም የፖለቲካ ተንታኝ የአቶ ሙሉጌታን ሕልፈት በተመለከተ በተዘጋጀው የጸሎት ...
Read More »የሃዘን መግለጫ
መስከረም 27, 2008 አንጋፋው ጋዜጠኛ፣ ሃያሲ፣ ደራሲና፣ የፖለቲካ ተንታኝ ሙሉጌታ ሉሌ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት በመለየታቸው የኢሳት ማኔጅመንት፣ ጋዜጠኞችና፣ መላው የኢሳት ቤተሰብ ከፍተኛ ሃዘን ተሰምቶታል። አቶ ሙሉጌታ ሉሌ በተባ ብዕራቸው ሃገራዊ ፍቅርን፣ አንድነትን፣ ነፃነትንና፣ ፍቅርን የሰብኩ፥ በአንደበታቸው ስለኢትዮጵያ የመሰከሩ፣ እስከመጨረሻ እስትንፋሳቸው ድረስ ኢትዮጵያን ያገለገሉና፣ ኢትዮጵያን ተቀምተው በስደት የቀሩ ሃገራዊ ሃብት ነበሩ። የሙያ አባታችን ሙሉጌታ ሉሌ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ሬዲዮ (ኢሳት) ...
Read More »በ በቆጂ በተነሳው ተቃውሞ ብዙ ወጣቶች ታሰሩ
መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦሮምያ ክልል በ በቆጂ ከተማ ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ተቃውሞ ከ20 በላይ ወጣቶች በፖሊሶች ተደብድበው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ነዋሪዎች ደግሞ ተደብድበዋል። ግጭቱ የተከሰተው የወረዳው ባለስልጣናት ቤት አፍራሽ መኪኖችን በመላክ ህገወጥ ቤቶች ያሉዋቸውን ቤቶች ማፍረስ መጀመራቸውን ተከትሎ ሲሆን፣ ነዋሪዎች ድንጋይ በመወርወር ተቃውሞቸውን ገልጸዋል። አንድ የፖሊስ መኪናም በድንጋይ ተመታለች። ...
Read More »በሃመር ወረዳ በመንግስት ባለስልጣናትና በነዋሪዎች መካከል መተማመን ሊፈጠር አልቻለም
መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከጸጥታ እና ከደህንነት ዋስትና ማጣት ጋር በተያያዘ፣ ስራ ያቋረጡት የመንግስት ሰራተኞች፣ ከወረዳው ባለስልጣናት ጋር ተናንት የተወያዩ ቢሆንም፣ መተማመን ላይ ባለመድረሳቸው አብዛኞቹ ዛሬም ስራ ሳይጀምሩ ቀርተዋል። አንዳንድ የመንግስት ሰራተኞች በግዴታ ስራ እንዲጀምሩ ቢደረግም፣ ብዙዎቹ በአድማው ቀጥለውበታል። የሀመር ወረዳ አርብቶአደሮች በየጊዜው በሚሰነዝሩት ጥቃት የፖሊስ፣ የመከላከያና የልዩ ሃይል አባላትን ጨምሮ ነዋሪዎች ተገድለዋል። በየጊዜው የሚፈጸመው ...
Read More »በመጪው ወር የሚጠበቀው ከፍተኛ ዝናብ ተጨማሪ አደጋ ደቅኗል
መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የተከሰተውና ከ4 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ ሕዝብ ለምግብ እጥረት የዳረገው የድርቅ ችግር በቀጣይ ወራትም ሊስፋፋ እንደሚችል ከፍተኛ ስጋት ፈጥሯል። ከብሔራዊ ሚቲሮዎሎጂ ኤጀንሲ የወጡ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ከኤልኒኖ ክስተት ጋር ተያይዞ ከቀጣይ ጥቅምት ወር ጀምሮ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች እንደሚያጋጥም ዓለም አቀፍ ትንበያ መኖሩን በመጥቀስ፣ ይህ ሁኔታ ድርቁ በሌሎች አካባቢዎች ...
Read More »አንድ የቀድሞ የመኢአድ አባል በደህንነቶች በከፍተኛ ሁኔታ ተደበደበ
መስከረም ፳፰ (ኅያ ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዳንግላ ዙሪያ ነዋሪ የሆነው አቶ ደግአረገ በአካባቢው ያሉ ወጣቶችን በትጥቅ ትግል ለሚታገሉ ሃይሎች እየመለመልክ ትልካለህ በሚል አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ ተደብድቧል። ማንነታቸውን በውል ለይቶ የማያውቃቸው ሰዎች አይኑን በጨርቅ ሸፍነው ወደ ባህርዳር እንደወሰዱትና በመጨረሻም መረጃ ሲያጡ ፣ አይኑን ሸፍነው እንደለቀቁት ገልጿል።
Read More »በዲመካ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ 3ኛ ቀኑን ያዘ
መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ ማክሰኞ የተጀመረው የስራ ማቆም አድማ እስከ ዛሬ የቀጠለ ሲሆን፣ የዞኑ ባለስልጣናት ነዋሪውን ለማነጋገር ስብሰባ ጠርተዋል። የስራ ማቆም አድማው መንስኤ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ በአካባቢው በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት ስራቸውን ለመስራት ስላላስቻላቸው ነው። የመንግስት ሰራተኞች እንደሚሉት ካለፈው ሰኔ ወር ጀምሮ በወረዳው ባሉ ቀበሌዎች ተዘዋውሮ ስራ መስራት ...
Read More »በሳዑዲ በሃጂ ስነ-ስርዓት ላይ የሞቱ ኢትዮጵያውያን በሀገር አቀፍ ደረጃ አለመታሰባቸው ሙስሊሞችን አሳዝኗል
መስከረም ፳፯ (ኅያ ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ አረቢያ ሚና አካባቢ በሀጂ ስነ-ስርዓት ወቅት በተከሰት ግፊያና መጨናነቅ በደረሰ አደጋ ህይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያዊያን ቁጥራቸው ከ47 በላይ የበለጠ ቢሆንም ፣ የኢህአዴግ መንግስት ለዚህ ከባድ ሐዘን የሰጠው ትኩረት ማነስ እንዳሳዘናቸው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው በአዲስአበባ የሚኖሩ ሙስሊሞች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመጅሊሱን ወሬ በመያዝ ለሞቱት ወገኖች መጽናናትን ይመኛል ከማለት ...
Read More »