Author Archives: Central

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ተደብድበው ታሰሩ

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ትናንት ምሽት የፌደራል ፖሊስ አባላት 6 ኪሎ ግቢ በመግባት 2 ተማሪዎችን ማሰራቸውን ተከትሎ የታሰሩት ተማሪዎች እንዲፈቱ በሰልፍ የጠየቁ ተማሪዎች በፖሊሶች ተደብድበዋል። ዩኒቨርስቲው ከጠዋት ጀምሮ በፖሊሶች ተከቦ ያረፈደ ሲሆን፣ ከቀኑ 7 ሰዓት ተኩል አካባቢ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው በመግባት በርካታ ተማሪዎችን እየደበደቡ ወስደው አስረዋል። ከአራት ኪሎ ግቢ እስከ ስድስት ኪሎ ግቢ ባለው ...

Read More »

መንግስት በልማት ስም እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የአየር ላይ ካርታ እያስነሳ ነው

ታኀሳስ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህንነት ምንጮቻችን እንደገለጹት መንግስት እጅግ ሰፊ መሬት ለሱዳን ለመስጠት የጀመረውን እንቅስቃሴ አጠናክሮ ቀጠሎአል። 99 በመቶ የሚሆነው ቦታ በአንድ ብሄር ተወላጆች የተያዘው የብሄራዊ ደህንነት መስሪያ ቤት ኢንሳ፣ ተላልፎ የሚሰጠውን መሬት የአየር ላይ ፎቶግራፍ እያነሳ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። የደህንነት ኤጀንሲው ፎቶ የማስነሳቱን ስራ የሚሰራው ትልቅ ለሆነ የመስኖ ልማት ፕሮጀክት በሚል ሰበብ ሲሆን፣ ዋናው ...

Read More »

በሱሉልታ እና በሌሎችም ከተሞች ህዝባዊ ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ዋሉ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከአዲስ አበባ 26 ኪሜ ርቅት ላይ በምትገኘዋ ሱሉልታ ሁሉም የህብረተሰብ ከፍል የተሳተፈበት ከባድ ህዝባዊ ተቃውሞ ተካሄዷል። የጸጥታ ሃይሎች በወታደራዊ ሄሊኮፕተሮች ታጅበው ቅኝት ሲያደርጉ ውለዋል። በህዝቡ ላይ ፍርሃት ለመልቀቅ የተደረገው ጥረትም ሳይሳካ ቀርቷል። ከአዲስ አበባ ወደ ጎጃም እና ጎንደር የሚወስደው መንገድ ለተሽከርካሪ ዝግ ሆሮ አርፍዷል። የጸጥታ ሃይሎች በርካታ ወጣቶችን ይዘው አስረዋል። ተመሳሳይ ...

Read More »

የኢትዮጵያ ወጣቶች ጥሪ አቀረቡ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው ወጣቶች እንደገለጹት በተለያዩ አካባቢዎች የሚገኙ ወጣቶች ትግሉን በመቀላቀል ነጻነታቸውን ሊያስከብሩ ይገባል። መንግስት ህዝብን ከህዝብ ለማጋጨት የሚያደርገውን ጥረት ወጣቱ በንቃት ሊከታተለው እንደሚገባም ወጣቶቹ ጥሪ አቅርበዋል። የተለያዩ ወጣቶች የሰጡዋቸውን አስተያየቶች በወጣቶች ዝግጅት ላይ እንደምናቀርብ እንገልጻለን።

Read More »

በሶማሊያ አንድ የኢትዮጵያ የደኅንነት ሹም ተገደለ

ታኀሳስ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የደህነት ሹሙ በሶማሊላንድ ራስገዝ ሃርጌሳ ከተማ ውስጥ ዋቃዮ ጋልቤድ አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች በተተኮሰ ጥይት ተመቶ መገደሉ ታውቋል። እስካሁን ለግለሰቡ ሞት ኃላፊነቱን የወሰደ አካል አለመኖሩንም ራዲዮ ኩሊሜይን ጠቅሶ አይኤችኤስ ዘግቧል።

Read More »

በኦሮምያ ዛሬም ተቃውሞው ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- መንግስት ከባድ ማስጠንቀቂያ በሰጠ ማግስት በተለያዩ የኦሮምያ አካባቢዎች መንግስትን የሚቃወሙ ህዝባዊ አመጾች ተካሂደዋል። ህዝባዊ አመጾቹ በሃረርጌ አሰቦት፣ በምእራብ ወለጋ ባቡ ገምበሌና ነጆ፣ በሆድሮጉድሩ በጋጨቲ እንዲሁም በአሰላ የተካሄዱ ሲሆን፣ በቡራዩ ፣ አምቦና አወዳይ ከተሞች የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከፍተኛ ሁኔታ ተሰማርተው ቅኝት እያደረጉና የሚጠረጥሩት ወጣት እየያዙ እያሰሩ ነው። ታህሳስ 5 በአወዳይ የነበረውን ተቃውሞ ...

Read More »

አርበኞች ግንቦት7 ከመንግስት ወታደሮች ጋር ተከታታይ ውጊያ እያደረገ እንደሆነ አስታወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የንቅናቄው ከፍተኛ የአመራር አባል የሆነው እንደገለጸው የንቅናቄው ሰራዊት ዋልድባ አካባቢ የነበረውን ወታደራዊ ቀለበት በመስበር በአድርቃይ ላይ በነበረው የመከላከያ ሰራዊት ላይ ከፍተኛ ጥቃት ፈጽሞ ከ29 በላይ ወታደሮችን ገድሏል። ጦርነቱ አሁንም ቀጥሎአል። በግንባር የተሰለፉ 6 አብሪዎች ወይም በቅኝት ስራ ላይ ተሰማርተው የነበሩ አባሎቻቸው ከፍተኛ ውጊያ አድርገው ጥይታቸው ማለቁን ተከትሎ በወያኔ እጅ ወድቀዋል ሲል ...

Read More »

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በመከላከያ ምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት አሳወቀ

ታኀሳስ ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቅአገኘሁ የክስ መዝገብ በመከላከያ ምስክርነት የተጠቀሰውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን በምስክርነት እንደማያቀርበው የቃሊቲ ማረሚያ ቤት ለልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በደብዳቤ አሳውቋል። ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የ18 አመት ፅኑ እስራት የተፈረደበት በመሆኑና ከአሁን ቀደም ምስክር ሆኖ ከማረሚያ ቤቱ ወጥቶ መስክሮ ስለማያውቅ ለምስክርነት ለማቅረብ እንቸገራለን የሚል ደብዳቤ ማረሚያ ቤቱ ታህሳስ 4 ቀን 2008 ...

Read More »

ገዢው ፓርቲ በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስደውን እርምጃ አጠናክሮ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኦሮምያ የተነሳውን ህዝባዊ አመጽ ተከትሎ የገዢው ፓርቲ ወታደሮች በንጹሃን ዜጎች ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው የቀጠሉ ሲሆን፣ ዛሬ ማክሰኞ ብቻ ከ11 ያላነሱ ሰዎች ተገድለዋል። የዛሬውን ጨምሮ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ በገዢው ፓርቲ የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ከ50 በላይ መሆኑን መረጃዎች አመልክተዋል። በጊንጪ በወታደሮች የተገደለውን ሰይፉ ቱራን ለመቅበር የወጡ ነዋሪዎች፣ ባስነሱት ተቃውሞ በጋሌሳ ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር የመንግስት ሹመኞች የለኮሱት ግጭት ደም አፋሳሽ ሆነ ቀጥሎአል

ታኀሳስ ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የመንግስት ታጣቂ ሃይሎች ሆን ብለው በቀሰቀሱት ግጭት የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት እየተቀጠፈና በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም እየተፈናቀሉ ነው። ኢሳት ያነጋገራቸው ተፈናቃዮች እንደሚሉት ጥቃቱን የሚፈጽሙት በአካባቢያቸው የሚያውቋቸው የመንግስት ሚሊሺያዎችና አስተዳዳሪዎች ናቸው። አንድ ባሏ ፊቷ ላይ የተገደለባት ሴት ድርጊቱ ሆን ተብሎ በመንግስት አቀናባሪነት መፈጸሙን ገልጻለች። ታጣቂዎቹ ባል ወይም ሚስት አማራ ከሆኑ ...

Read More »