Author Archives: Central

የበየዳ ወረዳ ነዋሪዎች “መንግስት የለንም” እያሉ ተቃውሞ ሲያደርጉ ዋሉ

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ቁጥራቸው ከ2500 በላይ የሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች እንዲሁም ትምህርታቸውን አቋርጠው ሰልፉን የተቀላቀሉ ተማሪዎች በርካታ ጥያቄዎችን አቅርበዋል። “ መንግስት የለንም፣ አገራችንን የሚመራ ሰው ይሰጠን፣ የህወሃት ድርጅት የሆነው ሳትኮን ኮንስትራክሽን ድርጅት በወረዳችን እየሰራ ያለው መንገድ ጥራቱን ያልጠበቀ በመሆኑ ገንዘባችን  እየተበላ ነው፣ ስራ አጥ ወጣቶች ለስደት መደረጋቸው ይብቃ፣ ወረዳችን የቱሪስት መዳረሻ ሆኖ እያለ ትኩረት ሰጥቶ ባለመሰራቱ ...

Read More »

በጀርመን አርበኞች ግንቦት7 የተሳካ የድጋፍ ማሰባሰብ ስራ ሲሰራ፣ በአውስትራሊያ ህወሃት የጠራው ስብሰባ በተቃውሞ ተቋረጠ።

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አርበኞች ግንቦት ሰባት ከትናንት በስቲያ በጀርመን ፍራንክፈርት የተሳካ ህዝባዊ ስብሰባና የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ በተገኙበት አካሂዷል። ስብሰባውን ለመቃወም የገዢው ስርዓት በኤምባሲው አማካይነት በመላ አውሮፓ የሚገኙ ደጋፊዎቹን ሰልፍ እንዲወጡ የጠራ ቢሆንም በሰልፉ ላይ ሊገኙ የቻሉት ግን አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ደጋፊዎቹ ሲሆኑ ስብሰባውን ለመታደም የተገኙ ወገኖች በጣም በርካታ ከመሆናቸው የተነሳ አዳራሹ ሞልቶ ...

Read More »

ብአዴን የደረሰበትን ወቀሳ ተከትሎ ለነባር አባሎቹ እውቅና መስጠቱን አስታወቀ

ሰኔ ፮(ስድስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ብአዴን ህዳር 11 ቀን 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ባከበረ ማግስት ፣ የብአዴን ነባር ታጋዮች “እኛ ከህውሃት አንሰን ታይተናል” ሲሉ በስብሰባ መድረኮች ላይ አሰተያየት ከሰጡ በሁዋላ ለ246 ነባር ታጋዮቹ እውቅና ለመስጠት ተገዷል። 67 ተዋጊዮቹ ከአዲስ አበባ የመጡ ሲሆን፣ 200 የሚሆኑት አባሎቹ ደግሞ ከዋግ ህምራ ሰቆጣ የመጡ ናቸው፡፡ ነባር አባሎቹ ላለፉት 25 ዓመታት ተረስተው ...

Read More »

አጣዳፊ ትውከትና ተቅማት አጣዳፊ በሽታ በአዲስ አበባ ተከሰተ

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በተለያዩ ክልሎች ተከስቶ የነበረው የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በአዲስ አበባ ከተማ መሰራጨት መጀመሩን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አርብ አስታወቀ። በዚሁ በሽታ ምልክት የታየባቸው ሁለት ህሙማን በመዲናይቱ አዲስ አበባ ከተማ የተገኙ ሲሆን፣ ግለሰቦቹ ወደ ጤና ተቋማት ገብተው ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ታውቋል። የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የበሽታው ስርጭት በአጭር ጊዜ ሊሰራጭ የሚችል በመሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ጥንቃቄን እንዲያደርጉ አሳስቧል። ...

Read More »

በሰሜን ጎንደር ዳባት የተከሰተው ተቋውሞ  እስካሁን እልባት አላገኘም

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) ሰሞኑን በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ከተማ የኤሌክትሪክ ሃይል ማሰራጫ መነሳት ጋር የተቀሰቀሰው ተቃውሞ አርብ ድረስ እልባት አለማግኘቱንና የከተማዋ አስተዳዳሪዎች ከተማዋን ለቀው ወደጎንደር ከተማ መሰደዳቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጡ። በሃይል ማሰራጫው ማሽን መነሳት ተቃውሞ ሲያቀቡ የነበሩ ነዋሪዎች የወልቃይት ጉዳይ እልባት እንዲያገኝ ሲሉ አዲስ አስተዳደራዊ ጥያቄን ማቅርብ መጀመራቸው ታውቋል። ለደህንነታቸው ሲሉ ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የዳባት ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ ...

Read More »

የተቅማጥ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሊያ ክልል በድጋሚ በወረርሽን መልክ ተቀሰቀሰ

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) በቅርቡ በድርቅ በተጎዱ አካባቢዎች ተቀሰቀሶ ለበርካታ ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረው አጣዳፊ የተቅማጥ በሽታ በኦሮሚያና ሶማሊያ ክልል በድጋሚ በወረርሽን መልክ ተቀሰቀሰ። በሁለቱ ክልሎች በሚገኝ በርካታ ዞኖች በመሰራጨት ላይ ያለው በሽታ ለመቆጣጠር ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት አፋጣኝ ርብርብ ማድረግ እንዳለባቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በድርቁ ዙሪያ ይፋ ባደረገው ሪፖርት መልክቷል። በቅርቡ በሁለቱ ክልሎች ተከስቶ በነበረው በዚሁ በሽታ 14 ሰዎች ...

Read More »

በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ የተላለፈው ውሳኔ የኢትዮጵያውያን ነጻነት ፈላጊዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ተባለ

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) በሰብዓዊ መብት ሽፋን በኤርትራ ላይ እየተላለፈ ያለው የፖለቲካ ውሳኔ፣ ከኤርትራውያን ባሻገር ኢትዮጵያውያን ለውጥ ፈላጊዎች ጭምር ኢላማ ያደረገ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል ሲሉ የኤርትራው ባለስልጣን ገለጹ። በእኛ በኩል የምንችለውን እያደረገን እንገኛለን ያሉት አቶ የማነ ገብረዓብ፣ ኢትዮጵያውያን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል። የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን መርማሪ አባላት ኤርትራን በተመለከተ ያወጡትን የሰብዓዊ መብት ረገጣ ሪፖርት በተመለከተ ከኢሳት ጋር ...

Read More »

በማላዊ ታስረው ከሚገኙት ኢትዮጵያውያን 14 ህጻናትን መታደጉን አለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት አስታወቀ

ኢሳት (ሰኔ 3 ፥ 2008) የአለም አቀፍ ስደተኞች ድርጅት በማላዊ እስር ቤቶች ለከፋ የምግብ እጥረት ከተዳረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች መካከል 14 ህጻናት መታደግ መቻሉን አስታወቀ። የማላዊ መንግስት በበኩሉ ወደሃገሪቱ በህገወጥ መንገድ ገብታችኋል ተብለው የተላለፈባቸውን የእስር ቅጣት ያጠናቀቀ ስደተኛ ኢትዮጵያውያን በገንዘብ እጥረት የተነሳ ወደሃገራቸው ሊመለሱ አለመቻሉን ገልጿል። የሃገሪቱ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት በበኩላቸው በሶስት እስር ቤቶች የሚገኙ ከ100 በላይ ስደተኛ ...

Read More »

በአልሸባብ የተገደሉ ወታደሮች  ወደ አገራቸው መጥተው በክብር  እንዲቀበሩ የሚጠይቁ አስተያየቶች እየቀረቡ ነው

ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ኢሳት ያነጋገራቸው በአገር ውስጥ የሚገኙ ሰዎች  መንግስት በሌሎች አገሮች እንደሚደረገው ሁሉ ለሟቾች ኢትዮጵያውያንም የክብር አቀባበል ሊያደርግላቸው ይገባል ይላሉ። የሞተ ሰው የለም በማለት መካድ ህዝብን ለማሞኘት መሞከረው ነው ሲሉ ያክላሉ። አልሸባብ የተባለው የሶማሊያ ታጣቂ ቡድን በአፍሪካ የሰላም አስከባሪ ቡድን በደረሰበት ተደጋጋሚ ጥቃት ከዋና ከዋና የሶማሊያ ግዛቶች ለቆ ቢወጣም፣ ተከታታይ የደፈጣ ጥቃቶችንና የቦንብ ፍንዳታዎችን ...

Read More »

በርካታ ጥራት አልባ የኮንዶሚኒየም ቤቶች በነዋሪዎች ህይወት ላይ አደጋ ደቅነዋል ተባለ

ሰኔ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ በመገንባት ላይ ያሉ በርካታ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ከጊዜ በሁዋላ በተገልጋዮች ህይወት ላይ አደጋ መደቀናቸውን የግንባታ ባለሙያዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ባለሙያዎቹ እንደሚሉት አብዛኞቹ ቤቶች የሚሰሩት አስቀድሞ ጥልቅ የሆነ የአፈር ምርመራ ሳይደረግባቸው በመሆኑ ከጊዜ በሁዋላ ጉዳት ማስከተላቸው አይቀሬ ነው። መሃንዲሶች እንደሚሉት አብዛኛውን ጊዜ የኮንዶሚኒየም ቤቶች የሚገነቡት ሜዳ እንደተገኘ እንጅ በትክክል የአፈር ምርመራ ተካሂዶባቸው ባለመሆኑ፣ ከጊዜ ...

Read More »