(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆነው እንደሚሾሙ ተገለጸ። የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወይዘሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚቀርበውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ ድምፅ ይሰጣል ተብሏል። ወይዘሪት ብርቱካን ከሰባት አመታት ስደት በኋላ መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል። ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደ አዲስ ለሚደራጀው ብሔራዊ ...
Read More »Author Archives: Central
በሜቴክ ሳቢያ የ36 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ አስከተለ
(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 12/2011)የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በአፋር ክልል እገነባዋለሁ በማለት የተንቀሳቀሰበት የእንፋሎት ሃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በሜቴክ ሳቢያ የ36 ሚሊየን ዶላር ኪሳራ ማስከተሉ ተገለጸ። በጄኔራል ክንፈ ዳኘው ይመራ የነበረው ሜቴክ ከኮንትራት ስምምነቱ ውጪ ከውጭ ያስገባቸው መሳሪያዎች አሮጌዎችና ያልተሟሉ በመሆናቸው ለፕሮጀክቱ መክሸፍና ለተከተለው ኪሳራ ምክንያት እንደሆነም መረዳት ተችሏል። 137 ሜጋ ዋት ያመነጫል የተባለው የሃይል ማመንጫ ፕሮጀክትም መክሸፉ ተመልክቷል። ሒደቱን በቅርብ ሲከታተሉ የነበሩ ...
Read More »ጄኔራል ሰዓረ መኮንን ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ አርአያነታችንን እናስመስክር አሉ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 11/2011) በኢትዮጵያ አሁን የተገኘው ለውጥ በሁሉም ህዝብ ትግል የመጣ በመሆኑ እኛም ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ አርአያነታችንን ማስመስከር ይገባናል ሲሉ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ገለጹ። የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን በአንድ የውይይት መድረክ ላይ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የሁሉንም ሕዝብ ተሳትፎ የጠየቀ በመሆኑ ሰራዊቱም የዚህ ለውጥ ተጠቃሚ እና ደጋፊ ነው ። በለውጡ የሰራዊቱን ኑሮ ከማሻሻል ጀምሮ ...
Read More »በትግራይ የታሰሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የድረሱልን ጥሪ አሰሙ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 11/2011)በትግራይ በተለያዩ ድብቅ እስር ቤቶች የታሰሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት መንግስትና ህዝብ እንዲደርስላቸው ጥሪ አቀረቡ። በድብቅ በተላለፈውና የ65 የመከላከያ ሰራዊት አባላት ስም ዝርዝር የሚገኝበት ወረቀት ላይ እንደመለከተው ከፌደራል መንግስቱ እውቅና ውጪ የታሰሩት እነዚህ ወታደሮች ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየተፈጸመባቸው ነው። የሰሜን እዝ አባለት የሆኑት እነዚህ ወታደሮች ከተራ ወታደር እስከ ሻለቃ ባሻ የሚደርስ ማዕረግ እንዳለቸው ለማወቅ ተችሏል። ኩያ ይባላል። በትግራይ ...
Read More »የታሰሩና የሚፈለጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ንብረት እንዲታገድ ትዕዛዝ ወጣ
(ኢሳት ዲሲ–ጥቅምት 11/2011) በከባድ ሌብነትና በከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ ተጠርጥረው በታሰሩና በሚፈለጉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ንብረት እንዲታገድ ትዕዛዝ ወጣ። የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በአዲስ አበባ ለ10ሩም ክፍለ ከተሞች በጻፈው ደብዳቤ የ413 ሰዎች ቤትና ንብረት ታግዶ እንዲቆም አሳስቧል። ከ48 ሰአት በኋላ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንደሚወጣም ተመልክቷል። በአዲስ አበባ ለአስሩም ክፍለ ከተሞች ከፌደራል ፖሊስ ከተጻፈው ደብዳቤ መረዳት እንደተቻለው የቀድሞው የብሄራዊ መረጃና ደህንነት ሃላፊ የአቶ ...
Read More »የሞያሌው ግጭት ጋብ ማለቱ ተሰማ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 7/2011) ለአንድ ሳምንት የዘለቀው የሞያሌው ግጭት ጋብ ማለቱ ተገለጸ። በእስከአሁኑ ግጭት 19 ሰዎች መገደላቸው ተገልጿል። በሶማሌ ገሪና በኦሮሚያ ቦረና ተወላጆች መካከል የተፈጠረው ግጭት በአካባቢው ያለውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ እንዳስቆመው የደረሰን መረጃ አመልክቷል። በግጭቱ መነሻነት ላይ ሁለቱ ክልሎች እየተወዛገቡ ናቸው። ግጭቱ የጎሳ ሳይሆን የይዞታ ይገባኛል ጥያቄ የፈጠረው እንደሆነም እየተነገረ ነው። የትምህርት መማሪያ ክፍሎችና የጤና ማዕከል በግጭቱ ምክንያት መቃጠላቸውም ታውቋል። ...
Read More »አቶ ያሬድ ዘሪሁን በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በከባድ የሌብነት ወንጀል ተጠረጠሩ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 7/2011) የቀድሞው የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ምክትል ሃላፊ የነበሩት አቶ ያሬድ ዘሪሁን በከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰትና በከባድ የሌብነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ፖሊስ ገለፀ። ከባድ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙት ከቀደሞው የብሄራዊ መረጃ እና ደህንነት ዋና ሃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ጋር በመሆን እንደሆነም ፖሊስ ገልጿል። እስረኞችን ለመወንጀል ሲሉ ሰዎች እያደራጁ ወደ ኤርትራ እየላኩ ህገወጥ መሳሪያ በማስገባት ሕዝብ ሲያሸብሩ መቆየታቸውም ተመልክቷል። ተጠርጣሪው ...
Read More »ግጭቶችንና በማንነት ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን በዘላቂነት የሚፈታ ኮሚሽን ሊቋቋም ነው
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 7/2011) በኢትዮጵያ በክልሎች መካከል የሚነሱ ግጭቶችንና በማንነት ዙሪያ የሚነሱ ጉዳዮችን በዘላቂነት መፍታት በሚያስችል መልኩ ኮሚሽን እንዲቋቋም የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ። በተመሳሳይ የብሄራዊ እርቅና ሰላም ኮሚሽን እንዲቁቁምም የሚኒስትሮች ምክር ቤት በመወሰን ሁለቱንም ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መመራቱን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አስታውቋል። የብሔራዊ እርቀ ሰላም ኮሚሽን በማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶችን አጣርቶ እልባት ለመስጠት የሚቋቋም ነው። ተግባሩም እውነት እና ፍትህን ...
Read More »በቤንሻንጉል በነዋሪዎች ላይ ጥቃት እየደረሰ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 7/2011)ቤንሻንጉል ክልል ካማሽ ዞን ያሶ ወረዳ በሚገኙ 9 ቀበሌዎች በሚገኙ ነዋሪዎች ላይ ከማክሰኞ ጀምሮ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገለጹ። በነዋሪዎቹ ላይ ጥቃት የደረሰው ማንነታቸውን መሰረት በማድረግ ከአካባቢው ውጡልን በሚል ነው። በጥቃቱ ቁጥሩ ያልታወቀ ሰው ሲገደል በንብረት ላይም ጉዳት ደርሷል ተብሏል። በቤንሻንጉል በተለይ በአማራና በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጥቃት መካሄዱን የአካባቢው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል ። በተለይ ደግሞ በሴቶች ...
Read More »ለፍርድ የማቅረቡ ዘመቻ ይደገፋል ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ህዳር 6/2011) በዜጎች ላይ የሰብአዊ መብት ሲፈጽሙ በነበሩ ባለስልጣናት ላይ መንግስት የጀመረውን ለፍርድ የማቅረብ ዘመቻ እንደሚደግፈው ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ ገለጸ። የጥቃቱ ሰለባዎችን በተመለከተ የሰበሰባቸውን መረጃዎች ለሕግ አስከባሪ አካላት እንደሚሰጥም አስታውቋል። የፍርድ ሔደቱ ከበቀል የጸዳ እንዲሆንም ጥሪ አቅርቧል። ከተመሰረተ ሩብ ክፍለ ዘመን ያስቀጠረውና በኢትዮጵያ የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በመመዝገብና በማጋለጥ የሚታወቀው የሰብአዊ መብቶች ጉባኤ የወቅቱን የመንግስት መግለጫ በተመለከተ መግለጫ ያወጣው ...
Read More »