ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆነው ሊሾሙ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 12/2011) ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆነው እንደሚሾሙ ተገለጸ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወይዘሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሀላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚንስትር አብይ የሚቀርበውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ ድምፅ ይሰጣል ተብሏል።

ወይዘሪት ብርቱካን ከሰባት አመታት ስደት በኋላ መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ በቅርቡ ወደ ሃገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል።

ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደ አዲስ ለሚደራጀው ብሔራዊ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ኃላፊ እንዲሆኑ መታጨታቸው ሲነገር ቆይቷል ።

ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ  ስያሜውንና አጠቃላይ አደረጃጀቱን በማሻሻል ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ሆኖ ይቋቋማል ተብሎ ይጠበቃል።

ይህንኑ አገር አቀፍ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ለመምራት፣ ዕጩ ሆነው በመንግሥት መጠራታቸውን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ሲገልጹ ነበር።

እናም ወይዘሪት ብርቱካን ሚደቅሳ በነገው ዕለት የሀገሪቱ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ሆነው እንደሚሾሙ ታወቋል።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በሚያደርገው ስብሰባ ወይዘሪት ብርቱካንን የምርጫ ቦርዱ ሃላፊ እንዲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ የሚቀርበውን ሀሳብ መነሻ በማድረግ ድምፅ ይሰጣል ተብሏል።

ወይዘሪ ብርቱካን ከሰባት አመታት ስደት በኋላ መንግስት ባደረገላቸው ጥሪ በቅርቡ ወደሃገር ቤት መመለሳቸው ይታወሳል።

በምርጫ ቦርድ አደረጃጀት ላይ የማሻሻያ ሐሳቦችን የያዘ ረቂቅ ለውይይት ይቀርባል ተብሎም ይጠበቃል።

የተቋሙ አደረጃጀት በኮሚሽን ደረጃ እንዲሆንና መጠሪያውም የምርጫ ኮሚሽን እንዲሆን አማራጭ የማሻሻያ ሐሳብ ለውይይት እንደሚቀርብ ሪፖርተር ዘግቧል።

በተያያዘ ዜና መንግሥት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ለማጠናከር ባስቀመጠው ዕቅድ መሠረት፣ ተቋሙን የሚመራ ጠንካራና በዘርፉ ልምድ ያለው ባለሙያ በማፈላለግ ላይ እንደነበር ተገልጿል።

በዚህ መሠረት በ1997 ዓ.ም. ምርጫ ወቅት አክሽን ኤድ የተባለው የሲቪክ ማኅበር ባልደረባ፣ በአሁኑ ወቅት ደግሞ ሂውማን ራይትስ ዋች ለተባለው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የአፍሪካ ዳይሬክተር ሆነው በማገልገል ላይ የሚገኙት አቶ ዳንኤል በቀለ ሊሾሙ እንደሚችሉ ዘገባው አመልክቷል።

አቶ ዳንኤል በቀለ በምርጫ 97 ጊዜ ለሰብአዊ መብት በመከራከራቸው ለእስር ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል።